TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia🇪🇹 የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅ እንደሚሻሻል ተገልጿል። ዛሬ 48ኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ተካሂዶ የአዋጁ መሻሻል ላይ ውሳኔ አሳልፏል። ምክር ቤቱ " ቀደም ሲል ሲሰራበት የነበረው የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅ አሁን ከምንገኝበት ሀገራዊ እና አለም አቀፋዊ የኢኮኖሚ ሁኔታ አንጻር ሲታይ በርካታ ክፍተቶች ያሉበት ነው " ብሏል። " የአዋጁን ድንጋጌዎች በማሻሻል የታክስ ስርአቱ…
#Ethiopia🇪🇹

" አሁን የ2,000 ብር ደሞዝ የለም በሌለ ነገር ከዚያ በታች ያለው ነጻ ነው ብንል ታክስ መቀነስ አይደለም ! " - የምክር ቤት አባል

በገቢ ግብር ማሻሽያ አዋጅ ላይ ዝቅተኛ  የግብር ከፋይ መነሻ ደመወዝ 5,000 ብር እንዲሆን በምክር ቤት ተጠየቀ፡፡

ይህ ጥያቄ የተጠየቀው የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ዛሬ  ከሰዓት በጠራው ልዩ መደበኛ ስብሰባ ላይ ነው፡፡

አሁን በስራ ላይ ያለው የገቢ ግብር አዋጅ ከዘመኑ የኢኮኖሚ ሁኔታ አብሮ እንደማይሄድ እና ከዲጂታል ኢኮኖሚ ጋር እንደማይጣጣም በአዋጁ ላይ በቀረበው አጭር ማብራርያ ተመላክቷል፡፡

የማሻሽያ አዋጁን በተመለከተ ሃሳብ የሰጡት የምክርቤት አባሉ አቶ ባርጠማ ፍቃዱ ምን አሉ ?

- በአዋጁ አንቅጽ 11 ላይ የቀድሞው ተሰርዞ አዲስ ሃሳብ ገብቷል። ከዚህ በፊት ተቀጣሪ ከደሞዘ የሚከፍለው ግብር ከ600 ብር በላይ ጀምሮ ነው። ተሻሽሎ በቀረበው አዋጅ ግን ከ600 ብር ወደ 2,000 ብር አድጓል።

- በመሰረቱ 2 ሺ ብር አሁን በአገራችን የሚቀጠር ሰው የለም።

- ከዚህ ቀደም በመንግስት ተቋም ጽዳት ፣የጉልበት ስራ እና የመሳሰሉ ስራዎች ነበሩ ከ600 ብር እስከ 1,000 ብር ደሞዝ አሁን ባለው ሁኔታ ከ4,500 ብር በላይ ነው ቅጥር ያለው።

- አሁን የ2,000 ብር ደሞዝ የለም በሌለ ነገር ከዚያ በታች ያለው ነጻ ነው ብንል ታክስ መቀነስ አይደለም።

- ቢያንስ እንኳን ዝቅተኛ ተቀጣሪው ከግብር ነጻ ቢሆን ጥሩ ነው።

- ግብር ከፋይዉም ከ5,000 በላይ ያለው ስራተኛ ቢሆን።

- የ35 በመቶ ግብር እንዲከፍል የተቀመጠው ከ14ሺ 100 በላይ ነው። ይህም ከወቅቱ ገበያ አንጻር ሲታይ ምንም ነው፤ በዚህ ላይ 35 በመቶ ግብር ሲቆረጥበት ደግሞ በጣም አስቸጋሪ ስለሆነ ወደ 20 ሺ በላይ ከፍ ቢል።

- በስራ ላይ ባለው አዋጅ #መነሻ_ግብር 10 በመቶ ነው። ተሻሽሎ በቀረበው ረቂቅ አዋጁ ግን 15 በመቶ ብሎ ነው የሚጀምረው ይህም ወደ ቀድሞው ወደ 10 በመቶ ቢመለስ ሲሉ ጥሩ ነው።

የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን በስራ ላይ ባለው አዋጅ ላይ ያለው ከፍተኛ ግብር የሚከፈልበት ደሞዝ በተሸሻለው አዋጅ የዝቅተኛ ግብር መነሻ እንዲሆን መጠየቁ ይታወሳል።

ኮንፌደሬሽኑ የሰራተኛውን ኑሮ ያገናዘበ የገቢ ግብር ማሻሽያ እንዲደረግም ጠይቆ ነበር፡፡

ዝቅተኛ ገቢ ያለው የህበረተሰብ ክፍል ፦
- የሚያርፍበትን የግብር ጫና መቀነስ፤
- የግብር መሰረትን ማስፋት፤
- የግብር ስርአቱ ላይ የሚታዩ የፍትሃዊነት ችግሮችን መቅረፍ፤
- የአነስተኛ የንግድ እንቅስቃሴዎች የግብር አከፋፈል ስርአት ቀላል እንዲሆን ማድረግ፤
- ከአዋጁ አላማዎች ውስጥ ጥቂቶቹ ናቸው ተብሏል፡፡

ም/ቤቱ እነዚህን እና ሌሎች ከአባላት የተነሱ ሃሳቦች ታክለውበት ረቂቅ አዋጁ ለፕላን በጀት እና ፋይናንስ ጉዳይዎች ቋሚ ኮሚቴ በሙሉ ድምጽ መርቶታል፡፡

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ነው።

#ShegerFM

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
1.85K👏245🙏64😡60😢43🕊23😭22🤔20😱19🥰7