TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63K photos
1.61K videos
216 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" የ3 ዓመት ህጻንን ጨምሮ 9 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል " - ፖሊስ

በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 በተለምዶ አባሳሙኤል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ዛሬ ረፋድ በግምት 3 ሰዓት ገደማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ9 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ከሟቾቹ መካከል የ3 ዓመት ዕድሜ ያለው ሕጻን የሚገኝበት ሲሆን፤ በ8 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ፖሊስ ገልጿል።

አደጋው ሊከሰት የቻለው ከሃይሌ ጋርመንት ወደ ዩኒሳ አደባባይ ይጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-78979 ኢት የሆነ የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት አውቶቡስ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-04273 ኢት ከሆነ ሌላ ከባድ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ እና መንገድ ስቶ ወደ ተቃራኒ አቅጣጫ በመግባቱ ነው፡፡

አውቶቡሱ ወደ ተቃራኒ አቅጣጫ ከገባ በኋላ ከዩኒሳ አደባባይ ወደ ሃይሌ ጋርመንት ሲጓዝ ከነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-77970 ኦሮ ከሆነ ዶልፊን ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ በዶልፊኑ ውስጥ ከነበሩት ተሳፋሪዎች መካከል አሽከርካሪውን ጨምሮ የዘጠኝ ሰዎች ሕይወት ማለፉን ፖሊስ አስረድቷል።

ከሟቹቹ መካከል የ3 ዓመት ሕጻን ይገኝበታል።

በሌሎች 8 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል።

ከዚህ በተጨማሪ በአካባቢው ላይ የቆመ እና በጉዞ ላይ የነበረ ሌሎች ሁለት ተሽከርካሪዎች በአውቶቡሱ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

የአደጋው መንስኤ እየተጣራ እንደሚገኝ ፖሊስ ገልጿል።

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
😭1.87K686💔107😢89🕊45🙏22😡13🤔7🥰3👏2😱1
#ለጥንቃቄ

" ' አሟታል ' ፣ ' ነፍሰ ጡር ናት ' ፣ ' መስኮት ክፈት ' ፣ ' ተባበራት ' ፣ ' ትራፊክ መጣ ዝቅ በል ' በማለት በማዋከብ ' ከታክሲው ውረጂ/ ውረድ ' ሌላም ምክንያቶችን በመናገር ገፍትረው የሚያመልጡ ስለሆነ ጥንቃቄ አድርጉ ! " -ፖሊስ

የአዲስ አበባ ፖሊስ CMC አካባቢ የማታለል (#ሿሿ) ወንጀል ላይ የተሰማሩ 9 ተጠርጣሪዎችን በተበዳይ ጥቆማ መያዙን አሳውቋል።

እነዚህ ግለሰቦች የግል ተበዳይን " የት ነህ ? " በማለት ከCMC ጋስትሞል ይጭናሉ።

የተወሰነ ርቀት እንደተጓዙ CMC የጋራ መኖሪያ ቤቶች (5 መቶ አፖርታማ) ጋር ሲደርሱ ግን " ትራፊክ አለ ውረድ " ብለው የተሽከርካሪውን በር ከፍተው ገፍትረው ጥለው ይሰወራሉ።

የግል ተበዳይም ጉዳዩን ለCMC አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ማመልከታቸውን ተከትሎ ፖሊስ ተጠርጣሪዎችን ወማደን ይገባል።

በዚህም በአራዳ ክፍለ ከተማ ፒያሳ አካባቢ ሹፌርና ረዳት እንዲሁም ተሳፋሪ በመምሰል ወንጀሉን የሚፈፅሙ 9 ተጠርጣሪዎችን ለወንጀል መፈጸሚያ  ከሚገለገሉበት የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 ኦ/ሮ 78652 ተሽከርካሪ ጋር መያዙን ፖሊስ ገልጿል።
                                                   
በግለሰቦቹ ላይ አስፈላጊውን ማስረጃ በማሰባሰብ ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑን አሳውቋል።

ተመሳሳይ የማታለል ወይም የሿሿ ወንጀል የተፈፀመበት ማንኛውም ግለሰብ CMC አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ቀርቦ ወንጀል ፈፃሚዎቹን በመለየትና በመምረጥ ማስረጃ  መስጠት የሚችል መሆኑ ተገልጿል።

የሿሿ የወንጀል ተግባር ላይ የተሰማሩ ሰዎች በተሽከርካሪዎቻቸው ውስጥ ወንድና ሴት በመጫን ፦
- " አሟታል "
- " ነፍሰ ጡር ናት "
- " መስኮት ክፈት "
- " ተባበራት "
- " ትራፊክ መጣ ዝቅ በል " በማለት በማዋከብ " ከታክሲው ውረድ " ሌላም ምክንያቶችን በመናገር ገፍትረው የሚያመልጡ በመሆኑ ህብረተሰቡ ለወንጀል ፈፃሚዎች ሰለባ ላለመሆን ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ፖሊስ አሳስቧል።

የወንጀል ድርጊቱ ከተፈፀመበትም የሰሌዳ ቁጥር የመያዝ ልምዱን ሊያጎለብት እንደሚገባ አስገንዘቧል።

⚠️ ትራንስፖርት ስትጠቀሙ የምትጠቀሙበትን ተሽከርካሪ ታርጋ ቁጥር መያዝ እንዳትዘነጉ።

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
1.18K🙏149👏59🤔27😢15😭11🕊9😱2
" በአንዳንድ ታዳጊ ወጣቶች ላይ የሚስተዋለው ባህሪ የነገ ተስፋቸውን ሊያጨልም የሚችል የሙችል በመሆኑ ሊታረምና በወላጆች ዘንድም ከፍተኛ ጥንቃቄና ትኩረት ሊደረግበት ይገባል !! " - ፖሊስ

" ታግተናል " በማለት ወላጆቻቸውን 500 ሺህ ብር የጠየቁ ታዳጊዎቸ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል።

የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታው ኳስ ሜዳ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ነው።

አጋችና ታጋች በመምሰል የማታለል ወንጀሉን የፈፀሙት አራቱ ተጠርጣሪዎች ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ሁለት ወንዶችና ሁለት ሴቶች ናቸው።

ልጆቹ ለሁለት ቀናት ከቤተሰቦቻቸው ወጥተው ሲዝናኑ ቆይተው ገንዘብ ሲያጥራቸው በመመካከር ለቤተሰብ ስልክ ይደውላሉ።

ወንዶቹ አጋች ሴቶቹ ደግሞ ታጋቾች በመሆን ለሴቶቹ ቤተሰቦች በደወሉት ስልክ 5 መቶ ሺ ብር የጠየቁ ሲሆን የሴት ወላጆች አቅራቢያቸው ወደሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ቀርበው ጥቆማ ሠጥተዋል።

ፖሊስም መረጃዎችን በማሰባሰብ አራቱንም ተጠርጣሪዎች ካሉበት ቦታ በቁጥጥር ስር ሊያውላቸው ችሏል፡፡

የታዳጊዎቹ ቤተሰቦች በወቅቱ ሴት ልጆቻቸው መታገታቸውን ሲሰሙ ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ገብተው እንደነበር ተናግረው ፖሊስ ላከናወነው ተግባር ምስጋና አቅርበዋል፡፡

" በልጆች አስተዳደግ ዙርያ የቤተሰብ ኃላፊነት ከፍተኛ ነው " ያለው ፖሊስ " በአንዳንድ ታዳጊ ወጣቶች ላይ የሚስተዋለው ባህሪ የነገ ተስፋቸውን ሊያጨልም የሚችል በመሆኑ ሊታረምና በወላጆች ዘንድም ከፍተኛ ጥንቃቄና ትኩረት ሊደረግበት ይገባል " ሲል ገልጿል።

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
403😡99🤔74😭44👏31💔21🕊11🙏10😢9😱8🥰5