TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" የጤና ጉዳይ ለነገ የሚባል ስላልሆነ እንጂ በግል ጤና ተቋማት ክፍያዉ ከአቅማችን በላይ ነዉ " - ተገልጋዮች
ከሰሞነኛዉ የጤና ባለሙያዎች ጥያቄ ጋር ተያይዞ ሐኪሞች ስራ ካቁሙባቸዉ ተቋማት አንዱ የሆነዉ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አሁንም ድረስ ሙሉ አገልግሎት እየሰጠ አለመሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ በቦታው በመገኘት አረጋግጧል።
በሆስፒታሉ አቅራቢያ እና በሀዋሳ ከተማ ባሉ ሌሎች የግል ሆስታሎችና የሕክምና ተቋማት ተዘዋውሮ ባደረገው ምልከታ በአንፃራዊነት የተገልጋይ ቁጥር መጨመሩን ማጣራት ችሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገረቻቸው ተገልጋዮች እንደገለፁት አስቀድመው ወደ ኮምፕርሄንሲቭ ሆስፒታሉ አገልግሎት ፈልገዉ መምጣታቸውን ተናግረው ነገር ግን አገልግሎት ማግኘት ባለመቻላቸው ወደ ግል ጤና ተቋማት ለመሄድ መገደዳቸውን አስታውቀዋል።
" የጤና ጉዳይ ለነገ ስለማይባል እንጂ የግል ጤና ተቋማት ክፍያ ከአቅማች በላይ ሆኖ ገና ሕክምናዉ ሳያልቅ ካሰብነዉ በላይ ወጪ አዉጥተናል " ያሉን አንድ አስተያየት ሰጪ " ሪፈራል ሆስፒታሉ ወደ መደበኛ አገልግቱ በአጭር ጊዜ ዉስጥ ካልተመለሰ ተገልጋይ በከፍተኛ ሁኔታ ይጉላላል " ሲሉ አክለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸዉ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕረሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ማኔጅንግ ዳይሬክተር አቶ ዝናዉ ሳርምሶ ሆስፒታሉ ወደ አገልግሎት እየተመለሰ መሆኑን ተናግረዉ ወጥተዉ የነበሩ ሐኪሞች እየተመለሱ መሆኑንም ተናግረዋል።
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕረሄንሲቭ ሪፈራል ሆስፒታል ሬዝደንት እና ኢንተርን ሐኪሞች በበኩላቸው ለጤና ባለሙያ ጥያቄዎች ተገቢው ምላሽ እስካልተሰጠ ወደ ስራ እንደማይመለሱና " የባለሥልጣናት ዘመዶችና በዉጤት ማነስ እንዲሁም በስነምግባር ችግር ከሆስፒታሉ የተባረሩ ሐኪሞችን በመመለስ ሆስፒታሉ አገልግሎት እየሰጠ እንደሆነ ለማስመሰል የሚደረጉ ሙከራዎችም ተገቢነት የላቸውም " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤827😭148👏49🙏24😡10🕊8💔6🥰4🤔4😢4