TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.9K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ዒድ ሙባረክ ! 1446ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል ነገ አርብ (በጁምዓ እለት) ተከብሮ ይውላል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ መልካም የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል እንዲሆን ከልብ ይመኛል። #TikvahEthiopiaFamily❤️ @tikvahethiopia
#AddisAbaba

ከለሊቱ 10:00 ሠዓት ጀምሮ መንገዶች ይዘጋሉ።

በነገው ዕለት የሚከበረው 1446ኛው የኢድ አል አድሀ (አረፋ) በዓልን ምክንያት በማድረግ የኢድ ሶላት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ የሚዘጉ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሰረት፡-

- ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ  የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል አደባባይ ላይ 

- ከኦሎምፒያ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኦሎምፒያ  አደባባይ ላይ

- ከጋዜቦ አደባባይ ወደ ደንበል የሚወስደው መንገድ ጋዜቦ አደባባይ ላይ

- ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ አጎና ሲኒማ መስቀለኛ ላይ

- ከጎፋ በአዲሱ መንገድ ወደ  ለገሃር መብራት የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክ መስቀለኛ ላይ

- ከቡልጋሪያ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ የሚወስደው መንገድ  ላንድ ማርክ ሆስፒታል አካባቢ

- ከሳር ቤት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ የሚወስደው መንገድ አፍሪካ ህብረት ትራክ መብራቱ መስቀለኛ ላይ

- ከጦር ኃይሎች በልደታ ከፍተኛ ፍ/ቤት ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ከፍተኛ ፍ/ቤትአደባባይ አካባቢ

- ከኑር ህንፃ ወደ ባልቻ ሆስፒታል የሚወስደው መንገድ ኑር ህንፃ መስቀለኛ ላይ

- ከፈረሰኛ መብራት ወደ ጨፌ ሜዳ የሚወስደው መንገድ ጨፌ ሜዳ ትራፊክ መብራት አጠገብ

- ከበርበሬ በረንዳ ወደ አምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ የሚወስደው መንገድ በርበሬ በረንዳ አካባቢ

- ከተ/ሃይማኖት በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ወደ ጎማ ቁጠባ  ተ/ሃይማኖት አደባባይ

- ከሰንጋ ተራ 40/60 ኮንደሚኒየም ወደ ሠንጋ ተራ መብራት ሰንጋ ተራ 40/60 መስቀለኛ አካባቢ

- ከጌጃ ሰፈር  በአምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ የሚሄዱ አሽከርካሪዎች ጎማ ቁጠባ አካባቢ

- ከተ/ሃይማኖት አደባባይ ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ ተ/ሃይማኖት አደባባይ አካባቢ

- ከሜትሮሎጂ መታጠፊያ ወደ ድሮ EBC የሚወስደው መንገድ ሜትሮሎጂ መታጠፊያ

- ከጎላ  ቅዱስ ሚካኤል መስቀለኛ ወደ ኢሚግሬሽን የሚወስደው መንገድ ኢምግሬሽን መስቀለኛ አካባቢ

- ከፒያሳ በቸርችል ጎዳና ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ አካባቢ

- ከንግድ ማተሚያ ቤት ወደ ፍልውሃ ንግድ ማተሚያ መስቀለኛ መንገዱ አካባቢ

- ከፓርላማ መብራት ወደ ውጭ ጉዳይ ፓርላማ መብራት ላይ

- ከኮንሰን መታጠፊያ ወደ ውጭ ጉዳይ የሚወስደው መንገድ ኮንሰን መታጠፊያ አካባቢ

- ከሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ የሚወስደው መንገድ ሴቶች አደባባይ ላይ ከለሊቱ 10:00 ሠዓት ጀምሮ ይዘጋል።

በተመሳሳይ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ዓለም ባንክ መስቀለኛ አካባቢ ከሚከበረው በዓል ጋር ተያይዞ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ይደረጋሉ፡፡

በዚህም መሰረት፡-

° ከዩኒሳ አደባባይ ወደ በላይ አብ መኪና መገጣጠሚያ የሚወስደው መንገድ

° ከቱሉዲምቱ - ወደ ጨፌ ይርጋ አደባባይ እስከ ዓለም ባንክ መስቀለኛ የሚወስደው መንገድ

° ከፌሮ ድልድይ እስከ ዩኒሳ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ከሌሊቱ 10፡00 ሠዓት ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናል፡፡

ህብረተሰቡም ከፖሊስ የሚሰጠውን መረጃ ተገንዝቦ የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚጠቁሙት አማራጭ መንገዶች እንዲጠቀም እና ለትራፊክ ፖሊስ አባላት ትዕዛዝ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።

#AddisAbabaPolice

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
1.97K😡190🕊53🥰49😭31🤔24💔23👏22🙏22😱14😢2
" የ3 ዓመት ህጻንን ጨምሮ 9 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል " - ፖሊስ

በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 በተለምዶ አባሳሙኤል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ዛሬ ረፋድ በግምት 3 ሰዓት ገደማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ9 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ከሟቾቹ መካከል የ3 ዓመት ዕድሜ ያለው ሕጻን የሚገኝበት ሲሆን፤ በ8 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ፖሊስ ገልጿል።

አደጋው ሊከሰት የቻለው ከሃይሌ ጋርመንት ወደ ዩኒሳ አደባባይ ይጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-78979 ኢት የሆነ የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት አውቶቡስ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-04273 ኢት ከሆነ ሌላ ከባድ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ እና መንገድ ስቶ ወደ ተቃራኒ አቅጣጫ በመግባቱ ነው፡፡

አውቶቡሱ ወደ ተቃራኒ አቅጣጫ ከገባ በኋላ ከዩኒሳ አደባባይ ወደ ሃይሌ ጋርመንት ሲጓዝ ከነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-77970 ኦሮ ከሆነ ዶልፊን ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ በዶልፊኑ ውስጥ ከነበሩት ተሳፋሪዎች መካከል አሽከርካሪውን ጨምሮ የዘጠኝ ሰዎች ሕይወት ማለፉን ፖሊስ አስረድቷል።

ከሟቹቹ መካከል የ3 ዓመት ሕጻን ይገኝበታል።

በሌሎች 8 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል።

ከዚህ በተጨማሪ በአካባቢው ላይ የቆመ እና በጉዞ ላይ የነበረ ሌሎች ሁለት ተሽከርካሪዎች በአውቶቡሱ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

የአደጋው መንስኤ እየተጣራ እንደሚገኝ ፖሊስ ገልጿል።

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
😭1.87K685💔107😢89🕊45🙏22😡13🤔7🥰3👏2😱1
#ለጥንቃቄ

" ' አሟታል ' ፣ ' ነፍሰ ጡር ናት ' ፣ ' መስኮት ክፈት ' ፣ ' ተባበራት ' ፣ ' ትራፊክ መጣ ዝቅ በል ' በማለት በማዋከብ ' ከታክሲው ውረጂ/ ውረድ ' ሌላም ምክንያቶችን በመናገር ገፍትረው የሚያመልጡ ስለሆነ ጥንቃቄ አድርጉ ! " -ፖሊስ

የአዲስ አበባ ፖሊስ CMC አካባቢ የማታለል (#ሿሿ) ወንጀል ላይ የተሰማሩ 9 ተጠርጣሪዎችን በተበዳይ ጥቆማ መያዙን አሳውቋል።

እነዚህ ግለሰቦች የግል ተበዳይን " የት ነህ ? " በማለት ከCMC ጋስትሞል ይጭናሉ።

የተወሰነ ርቀት እንደተጓዙ CMC የጋራ መኖሪያ ቤቶች (5 መቶ አፖርታማ) ጋር ሲደርሱ ግን " ትራፊክ አለ ውረድ " ብለው የተሽከርካሪውን በር ከፍተው ገፍትረው ጥለው ይሰወራሉ።

የግል ተበዳይም ጉዳዩን ለCMC አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ማመልከታቸውን ተከትሎ ፖሊስ ተጠርጣሪዎችን ወማደን ይገባል።

በዚህም በአራዳ ክፍለ ከተማ ፒያሳ አካባቢ ሹፌርና ረዳት እንዲሁም ተሳፋሪ በመምሰል ወንጀሉን የሚፈፅሙ 9 ተጠርጣሪዎችን ለወንጀል መፈጸሚያ  ከሚገለገሉበት የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 ኦ/ሮ 78652 ተሽከርካሪ ጋር መያዙን ፖሊስ ገልጿል።
                                                   
በግለሰቦቹ ላይ አስፈላጊውን ማስረጃ በማሰባሰብ ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑን አሳውቋል።

ተመሳሳይ የማታለል ወይም የሿሿ ወንጀል የተፈፀመበት ማንኛውም ግለሰብ CMC አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ቀርቦ ወንጀል ፈፃሚዎቹን በመለየትና በመምረጥ ማስረጃ  መስጠት የሚችል መሆኑ ተገልጿል።

የሿሿ የወንጀል ተግባር ላይ የተሰማሩ ሰዎች በተሽከርካሪዎቻቸው ውስጥ ወንድና ሴት በመጫን ፦
- " አሟታል "
- " ነፍሰ ጡር ናት "
- " መስኮት ክፈት "
- " ተባበራት "
- " ትራፊክ መጣ ዝቅ በል " በማለት በማዋከብ " ከታክሲው ውረድ " ሌላም ምክንያቶችን በመናገር ገፍትረው የሚያመልጡ በመሆኑ ህብረተሰቡ ለወንጀል ፈፃሚዎች ሰለባ ላለመሆን ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ፖሊስ አሳስቧል።

የወንጀል ድርጊቱ ከተፈፀመበትም የሰሌዳ ቁጥር የመያዝ ልምዱን ሊያጎለብት እንደሚገባ አስገንዘቧል።

⚠️ ትራንስፖርት ስትጠቀሙ የምትጠቀሙበትን ተሽከርካሪ ታርጋ ቁጥር መያዝ እንዳትዘነጉ።

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
1.13K🙏146👏59🤔25😢14😭11🕊8😱2