TIKVAH-ETHIOPIA
ደሴ ከተማ በሚገኘው ቦሩ ሜዳ አጠቃላይ ሆስፒታል ለአንድ ሳምንት ታስረው የነበሩ 3 የጤና ባለሙያዎች ትላንትና ከእስር መለቀቃቸውን ታስሮ የነበረ አንድ የጤና ባለሙያና ጏደኞቻቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
በሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ ውስጥ ቅሬታቸውን ለማሰማት ባለፈው ሳምንት ሰኞ ግንቦት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ከወጡት የህክምና ባለሙያዎች ውስጥ 10 የሚሆኑት በፀጥታ ሀይሎች ተወስደው እንደነበርና 7ቱ/ወዲያው ሲለቀቁ 3ቱ ግን እስከ ትላንት ከቀኑ 6: 00 ድረስ ታስረው ቆይተዋል።
ትላንት ከ6:00 ሰዓት በኃላ ግን ከእስር መለቀቃቸውን ታስሮ የነበረ አንድ ሀኪም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል።
ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀን ይህው የህክምና ባለሙያ በ8 ቀናት የእስር ቆይታቸው ከሌሎች የህግ ታሳሪዎች የተለየ እንክብካቤ ሲደረግላቸው መቆየቱን ገልፆ ቤተሰቦቻቸውንና ሌሎች ጠያቂዎቻቸውን ያለ ምንም ገደብ በነፃነት እንዲያገኙ መደረጉን ገልጿል።
ቀን ቀን በጣቢያው ግቢ እንደሚውሉና ማታ ማታ ከኮማንደሩ ቢሮ ውስጥ ፍራሽ አንጥፈው እንዲተኙ በመፈቀዱ እዚያው መሰንበታቸውን አክሎ ገልጿል።
ከሌሎች ታሳሪዎች ለምን እነሱ ተለይተው ሳምንት ቆዩ ?
መርማሪዎቹ የጤና ባለሙያዎቹን በክልሉ ታጥቀው የሚንቀሳሰቁ ታጣቂ ኃይሎችን " ትደግፋላችሁ ይህም ጥቆማ ከውስጥ ነው የደረሰን " በማለት በታሰሩ ማግስቱ ይነግሯቸዋል።
የጤና ባለሙያዎቹም " እኛም አልደገፍንም " ቢሉም " እስኪጣራ ቆዩ " በማለት ነው ይህን ያህል ቀን ሊያቆይዋቸው የቻሉት።
ጤና ባለሙያዎቹ ሲለቀቁ " ምንም አልተገኘባችሁም " ብለው እንደለቀቋቸው ተናግረዋል።
በሌላ በኩን ትላንት በደሴ ከተማ ከዞን እና ከክልል የመጡ አመራሮች የጤና ባለሙያውን ሰብስበው እንደዋሉና " ጏደኞቻቸሁ ተለቀዋል ወደ ስራ ተመለሱ " የሚል ጥሪ አቅርበው እንደነበር በዚህም የተመለሱ እንዳሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ባሕር ዳር
#TikvahEthiopiaFamilyBahirdar
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👏215😡138❤45😭15🤔12🙏11🕊8😢4😱2
TIKVAH-ETHIOPIA
ኢሰመኮ የጤና ባለሙያዎች እያደረጉት ስላለው የሥራ ማቆም አድማ ምን አለ ? " ጉዳዩ በውይይት እንዲፈታ የሚያደርገው ጥረት ይቀጥላል " - ኢሰመኮ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከግንቦት 5 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የጤና ባለሙያዎች በጤና ተቋማት ውስጥ በማድረግ ላይ የሚገኙት የሥራ ማቆም አድማ እንዲሁም ይህንን ተከትሎ በመንግሥት እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች…
" ሙሉ በሙሉ ስራ አቁመዋል፤ ሌሎች ዉስን የጤና ባለሙያዎች ብቻ በሆስታሉ አሉ፤ ስራ ቆሟል ማለት ይችላል" - የወላይታ ሶዶ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል ሰራተኞች
➡️ " ከሬዝደንት ሐኪሞች በስተቀር ሌሎች የጤና ባለሙያዎች በስራ ላይ ናቸዉ " - የሆስፒታሉ ኤክስክዩትቭ ዳይሬክተር
የወላይታ ሶዶ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል የጤና ባለሙያዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፤ ከጤና ባለሙያዎች ሀገራዊ ጥያቄዎች ጋር በተያያዘ ከሰሞኑ መንጠባጠቦች የነበረበዉ የሆስፒታሉ አገልግሎት ከትላንት ጀምሮ አጠቃላይ የሬዝዴንት ስራ በማቆማቸው አገልግሎት ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ መቋረጡን አስረድተዋል።
ሆስፒታሉ ከፍተኛ ቁጥር ላለው ማህበረሰብ በየቀኑ አገልግሎት ይሰጥ እንደነበር የገለፁት አንድ ስማቸዉ እንዳይገለፅ የፈለጉ የጤና ባለሙያ ከትላንት ማክሰኞ ጀምሮ ግን የስፔሻሊቲ ሃኪሞች ስራ በማቆማቸዉ ተገልጋዮች እየመጡ እየተመለሱ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገርናቸው የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር ወኪል ወልዴ " ከሬዝዴንቶች በስተቀር ሆስፒታሉ አገልግሎት እየሰጠ ነዉ " ብለዋል።
" ኢንተርን ሐኪሞች በሆስፒታሉ አስቀድሞዉኑ የሉም " ያሉት ዳይሬክተሩ " ሬዝዴንት ሃኪሞችም ወደ ስራቸዉ እንዲመለሱ ዩኒቨርሲቲዉ በማስታወቂያ ጠርቷል " ሲሉ ገልፀዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👏455❤81😡38😭14🕊12🙏6🤔5🥰4😱4
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" የጤና ጉዳይ ለነገ የሚባል ስላልሆነ እንጂ በግል ጤና ተቋማት ክፍያዉ ከአቅማችን በላይ ነዉ " - ተገልጋዮች
ከሰሞነኛዉ የጤና ባለሙያዎች ጥያቄ ጋር ተያይዞ ሐኪሞች ስራ ካቁሙባቸዉ ተቋማት አንዱ የሆነዉ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አሁንም ድረስ ሙሉ አገልግሎት እየሰጠ አለመሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ በቦታው በመገኘት አረጋግጧል።
በሆስፒታሉ አቅራቢያ እና በሀዋሳ ከተማ ባሉ ሌሎች የግል ሆስታሎችና የሕክምና ተቋማት ተዘዋውሮ ባደረገው ምልከታ በአንፃራዊነት የተገልጋይ ቁጥር መጨመሩን ማጣራት ችሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገረቻቸው ተገልጋዮች እንደገለፁት አስቀድመው ወደ ኮምፕርሄንሲቭ ሆስፒታሉ አገልግሎት ፈልገዉ መምጣታቸውን ተናግረው ነገር ግን አገልግሎት ማግኘት ባለመቻላቸው ወደ ግል ጤና ተቋማት ለመሄድ መገደዳቸውን አስታውቀዋል።
" የጤና ጉዳይ ለነገ ስለማይባል እንጂ የግል ጤና ተቋማት ክፍያ ከአቅማች በላይ ሆኖ ገና ሕክምናዉ ሳያልቅ ካሰብነዉ በላይ ወጪ አዉጥተናል " ያሉን አንድ አስተያየት ሰጪ " ሪፈራል ሆስፒታሉ ወደ መደበኛ አገልግቱ በአጭር ጊዜ ዉስጥ ካልተመለሰ ተገልጋይ በከፍተኛ ሁኔታ ይጉላላል " ሲሉ አክለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸዉ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕረሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ማኔጅንግ ዳይሬክተር አቶ ዝናዉ ሳርምሶ ሆስፒታሉ ወደ አገልግሎት እየተመለሰ መሆኑን ተናግረዉ ወጥተዉ የነበሩ ሐኪሞች እየተመለሱ መሆኑንም ተናግረዋል።
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕረሄንሲቭ ሪፈራል ሆስፒታል ሬዝደንት እና ኢንተርን ሐኪሞች በበኩላቸው ለጤና ባለሙያ ጥያቄዎች ተገቢው ምላሽ እስካልተሰጠ ወደ ስራ እንደማይመለሱና " የባለሥልጣናት ዘመዶችና በዉጤት ማነስ እንዲሁም በስነምግባር ችግር ከሆስፒታሉ የተባረሩ ሐኪሞችን በመመለስ ሆስፒታሉ አገልግሎት እየሰጠ እንደሆነ ለማስመሰል የሚደረጉ ሙከራዎችም ተገቢነት የላቸውም " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤827😭148👏49🙏24😡10🕊8💔6🥰4🤔4😢4