#ሰሌዳ
በኢትዮጵያ የተሽከርካሪ ሰሌዳ (ታርጋ) ለውጥ ለማድረግ የሚያስችል መመሪያ ጸድቋል።
መመሪያው የተሸከርካሪ የመለያ ቁጥር ሰሌዳ ዓይነቶችና ምልክቶች መወሰኛ እና የአገልግሎት አሰጣጥ መመሪያ ቁጥር 1050/2017 ነው።
የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አማካሪ ከድልማግስት ኢብራሂም፤ " የሰሌዳ ለውጡ ዋና ምክንያት ኢትዮጵያ የተቀበለቻቸውን ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ታሳቢ ያደረገ ሰሌዳ እንዲኖር ለማስቻል ነው " ብለዋል።
ከዚህ ቀደም በነበረው የተሽከርካሪ መለያ ቁጥር ሰሌዳ ፦
- የአመራረት እና አሰረጫጨት ችግር፣
- የአወጋገድ ችግር፣
- የአሰራር ክፍተት፣
- የሀብት ብክነት፣
- በሲስተም የተደገፈ ስራ አለመኖር ችግር እንደነበር ጠቁመዋል።
ከዚህ በፊት ከነበረው አሰራር ጋር ተያይዞ የዕለት የተላላፊ እና የቋሚ መለያ ቁጥር ሰሌዳ አገልግሎት አሰጣጥ ለፎርጅሪ ለብልሹ አሰራር ለበርከታ ወንጀሎች የተጋለጠ በመሆኑ ይህ መመሪያ ችግሩን ይቀርፋል ሲሉ አስረድተዋል።
" መመሪያው በመላ ሀገሪቱ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን፤ በተመዘገቡና ለምዝገባ በሚቀርቡ ተሽከርካሪዎች፣ በተሽከርካሪ አምራች /አስመጪ/ገጣጣሚ ድርጅቶች፣ በተሽከርካሪ መዝጋቢ አካላት እንዲሁም በኢትዮጵያ በሚገኙ እና አህጉር አቀፍ ተቋማት እና በግለሰቦች ላይ ተፈጻሚ ይሆናል " ብለዋል።
የተሽከርካሪ መለያ ቁጥር ሰሌዳ ዓይነቶች እና ምልክቶች ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን መሰረት በማድረግ፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ የመለያ ቁጥር ሰሌዳ አገልግሎት ይዘት በዓይነት እና በመጠን ወጥ እንዲሆን ለማድረግ፣ የመለያ ቁጥር ሰሌዳ ምርት ስርጭት አወጋገድ የተሸከርካሪ መረጃ አያያዝ ቁጥጥሩ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ለማድርግ የመመሪያው ዓላማ መሆኑ ተብራርቷል፡፡ #ኤፍኤምሲ
@tikvahethiopia

😡447❤370👏118🤔69🙏44😢28😭24🕊23🥰16😱16💔7
TIKVAH-ETHIOPIA
የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆኗል። የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና መቼ ይሰጣል ? ➡️ በወረቀት ፈተናቸውን የሚወስዱ ተፈታኞች ፦ ሰኔ 23 ፣ ሰኔ 24 እና ሰኔ 25/2017 ዓ/ም ➡️ በበየነ መረብ (ኦንላይን) /ፈተናቸውን የሚወስዱ የ1ኛ ዙር ተፈታኞች ፦ ሰኔ 23 ፣ ሰኔ 24 እና ሰኔ 25/2017 ዓ/ም ➡️ በበየነ መረብ (ኦንላይን) /ፈተናቸውን የሚወስዱ የ2ኛ ዙር…
#NationalExam
በዘንድሮ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና 608 ሺህ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።
ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ/ም የሚሰጠው አገር አቀፍ ፈተና ላይ 608 ሺህ ተማሪዎች ይቀመጣሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው።
ፈተናው በወረቀት እና በበየነ መረብ ይሰጣል።
ፈተናውን በወረቀት የሚወስዱ ተማሪዎች እንደ ቀደሙት ዓመታት ሁሉ ሙሉ በሙሉ ወደ ዩኒቨርሲቲዎች ገብተው ይወስዳሉ።
ፈተናውን በበይነ መረብ የሚወስዱት ደግሞ ፦
- በዩኒቨርሲቲዎች፣
- በመንግስት እና በግል ትምህርት ቤቶች፣
- በጤና እና መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጆች
- በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ውስጥ ባሉ ኮምፒዩተሮች ይፈተናሉ። ተማሪዎቹ ግቢ ማደር ሳይጠበቅባቸው ከቤታቸው እየተመላለሱ ነው ፈተናውን የሚወስዱት።
በበይነ መረብ የሚሰጠው ፈተና በሁለት ዙር ሲሆን ይህም የሆነው በበይነ መረብ የመፈተን አቅምን እና የተፈታኝ ተማሪዎችን ቁጥር ለመጨመር እንዲሁም ያለውን የመሰረተ ልማት አቅም ለማሳደግ እንደሆነ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ለኤፍ ኤም ሲ በሰጠው ቃል አስረድቷል።
#Ethiopia #NationalExam #Grade12 #ኤፍኤምሲ

🤔351❤196😡117😭93🙏76👏37🕊32💔32🥰22😢10😱7
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
በሰላም ተጠናቋል !
እጅግ ከፍተኛ ምዕመን የተገኘበት ዓመታዊው የቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል በሰላምና በድምቀት ተከብሮ መጠናቀቁን የፀጥታ ኮማንድ ፖስት አሳውቋል።
ኮማንድ ፖስቱ የትራፊክ አደጋን ጨምሮ ምንም ዓይነት ያጋጠመ ችግር እንዳልነበረ ገልጿል። #ኤፍኤምሲ

6❤3.34K🙏549🥰80👏65🕊64😡61🤔23😭23😢18💔8😱3