TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
🔈#የጤናባለሙያዎችድምጽ

" አስተዳደራዊ በደል በድሬዳዋ ጤና ቢሮ ተፈፅሞብኛል " - የሳቢያን ሆስፒታል ሀኪም ዶክተር ሀብታሙ አለሙ

➡️ " በሆስፒታሉ ከተቀጠረ ጀምሮ እስካሁን ድረስ የቀረበበት የዲስፕሊን ጉድለት የለም " - የሳቢያን ሆስፒታል የዲሲፕሊን ኮሚቴ


በድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ሳቢያን ሆስፒታል የጠቅላላ ህክምና ሃኪም የሆኑት ዶክተር ሀብታሙ አለሙ በሀገር አቀፍ ደረጃ የህክምና ባለሙያዎች ያቀረቡትን ቅሬታ በመደገፋቸው በቢሮው አስተዳደራዊ በደል ተፈፅሞብኛል በማለት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተውና ለባለሞያው የተጻፈው ደብዳቤ " ለስራ በተመደበበት ክፍል የሙያ ስነምግባርን በተፃረረ መልኩ በእናቶች እና በህፃናት ክፍል ወላድ እናቶችን በተደጋጋሚ ማመናጨቅ፣ መሳደብ እና ያለአግባብ ማመላለስ እና ማስጠንቀቂያ ቢሰጥም ባለመታረሙ ወደ ገኦዳ ጉዱንፈታ ጤና ጣቢያ አዘዋውረናል " የሚል ነው።

የጤና ባለሙያው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ?

" በሀገር አቀፍ ደረጃ የህክምና ባለሙያዎች የደመወዝ ጭማሪ ይደረግልን ተብሎ ቅሬታ ሲያቀርቡ ለምን ሃሳቡን ደገፍክ ብለው የድሬዳዋ ከተማ ጤና ቢሮ ሃላፊ እና ምክትል ደውለው ለምን ይሄን አደረክ አሉኝ፣ እኔም ጥያቄው እንደሀገር ነው የቀረበው፣ እንደ ድሬዳዋ አይደለም፣ ይሄ ደግሞ የመብት ጥያቄ ነው ብየ መለስኩኝ ።

የሃላፋዎች ምላሽም በድሬዳዋ ከተማ አንደዚህ መንቀሳቀስ አትችሉም፣ የከተማችንን ስም ያቆሽሽብናል፣ ስለዚህ የህክምና ባለሙያው ዝም ነው ማለት ያለበት አሉኝ።

በነጋታው ከሰዓት የዝውውር ደብዳቤ እና የዲስፕሊን ጉድለት አለብህ ብለው ከሃላፊዎች ሲሰጠኝ የጤና ቢሮ ሃላፊዋን ዶክተር ፅጌሬዳን ለማናገር ቢሮ ስሄድ ባለማግኜቴ ስልክ በመደወል ሳናግሯቸው ቅድሚያ ስሜን አጥፍተሀል እና ፌስቡክ ላይ ይቅርታ ብለህ ፃፍ ከዚያ ውጭ አላናግርህም አሉኝ " ሲሉ አስረድተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በዚህ ላይ ስማቸው የተጠቀሰው የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ጽጌረዳ ክፍሌ እንዲሁም ምክትል ኃላፊ አቶ ዩሱፍ ሰይድ ለማነጋገር በተደጋጋሚ ስልካቸው ላይ ቢደውልም ምላሽ ማግኘት አልቻልም።

በጉዳዩ ላይ የሳቢያን ሆስፒታል የዲሲፕሊን ኮሚቴ ምን አለ ?

ዶ/ር ሀብታሙ " እንደ ሆስፒታል በዲስፕሊን ተፅፎብኝ የሚያውቅ ደብዳቤ የለም " ማለታቸውን ተከትሎ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሳቢያን ሆስፒታል የዲሲፕሊን ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑትን ዶክተር አባይነህን ጠይቋል።

በምላሻቸውም " በሆስፒታሉ ከተቀጠረ ጀምሮ እስካሁን ድረስ የቀረበበት የዲስፕሊን ጉድለት ክስ #የለም " ሲሉ ማረጋገጫ ሰጥተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህንን መረጃ እያዘጋጀ በነበረበት ወቅት የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ ሲስተር መስከረም አሰፋ በኃላፊነት ቦታቸው ላይ እንደሌሉ ሰምቷል።

ሲስተር መስከረም ይኽ መረጃ እስከተዘጋጀበት ጊዜ ከሥራ እረፍት እንዲያደርጉ እንጂ ዝውውርም ሆነ እድገት እንዳልተሰጣቸው ለማረጋገጥ ችለናል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከደመወዝ ጥያቄው ጋር በተገናኘ እንዲሁም በዚህ መረጃ ላይ ለቀረቡት ቅሬታዎች የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ሃላፊዎችን ለማናገር ያደረግው ጥረት ባለመሳካቱ ምላሻቸውን ማካተት ሳይቻል ቀርቷል።

በጉዳዩ ላይ ቢሮውም ሆነ ማንኛውም አካል ምላሽ እና ማብራሪያ ለመስጠት ፈቃደኛ ከሆነ ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኑን ይገልጻል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😭911😡166128💔33🤔23😢20🥰10🕊10👏8🙏8😱5
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈#የጤናባለሙያዎችድምጽ " አስተዳደራዊ በደል በድሬዳዋ ጤና ቢሮ ተፈፅሞብኛል " - የሳቢያን ሆስፒታል ሀኪም ዶክተር ሀብታሙ አለሙ ➡️ " በሆስፒታሉ ከተቀጠረ ጀምሮ እስካሁን ድረስ የቀረበበት የዲስፕሊን ጉድለት የለም " - የሳቢያን ሆስፒታል የዲሲፕሊን ኮሚቴ በድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ሳቢያን ሆስፒታል የጠቅላላ ህክምና ሃኪም የሆኑት ዶክተር ሀብታሙ አለሙ በሀገር አቀፍ ደረጃ የህክምና ባለሙያዎች…
🔈#የጤናባለሙያዎችድምጽ

“ መጀመሪያ እየሰራሁ ወደነበረበት ሳቢያን ሆስፒታል ተመልሸ ስራዬን እንድቀጥል ይደረግልኝ ” - የጠቅላላ ሀኪሙ ዶ/ር ሀብታሙ አለሙ
 
“ የዝውውር ዓላማ ክፍት ቦታ ሲኖር ሥራንና ሠራተኞቸን ማገናኘት ነው እንጂ ዝውውር የቅጣት ውጤት አይደለም ” - ማኀበሩ

በድሬዳዋ ሳቢያን ጠቅላላ ሆስፒታል የጠቅላላ ሀኪም ዶክተር ሀብታሙ አለሙ ደረሰብኝ ላሉት በደል ፍትህ እንዲያሰጣቸው በኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማኀበር በኩል በደብዳቤ አቤት ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው የአቤቱታ ደብዳቤያቸው ምን ይላል ?

በጠቅላላ ሀኪምነት ከአዲስ  አበባ ዩኒቨርሲቲ ከተመረቁ በኋላ ወዳስተማረቻቸውና ያሳደገቻቸው ድሬዳዋ ከተማ ለሦስት ወራት የነፃ አገልግሎት እንደሰጡ ይገልጻል።

በኋላም በአስተዳደሩ በወጣ ማስታወቂያ ወድድር አልፈው በ2016 ዓ/ም በሆስፒታሉ በትጋትና ከፍተኛ ፍቅር ህብዝን ሲያገለግሉ እንደነበር ያስረዳል።

ከሰሞኑን እንደ ሀገር በተጀመሩ የጤና ባለሙያዎች የመብት ጥያቄዎች ሰላማዊ እንቅስቃሴ በፅሑፍ ያላቸውን ተሰሚነት በመጠቀም ሌሎችን በማንቃት ሲሳተፉ የጤና ቢሮው ኃላፊዎች ከዚህ እንዲታቀቡ ቢያስጠነቅቋቸውም የመብት ጥያቄ ማንሳት እንደማያቆሙ ማሳወቃቸውን ይጠቅሳል።

ይህን ባሳወቁ ማግስትም (ማክሰኞ ሚያዚያ 14/2017 ዓ/ም) በተፃፈላቸው ደብዳቤ ጥፋት እንዳለባቸው ተገልጾ የሥራ ቦታ እንዲቀይሩ መደረጋደቸውን ያትታል።

ሀኪሙ ይህንኑ እርምጃ፣ “ ህገ ወጥና ስርዓቱን ያልተከተለ በቂም በቀል የተጻፈ ደብዴቤ አግባብ አለመሆኑ እና የሥም ማጥፋት መሆኑን ” ገልጸው፣ ውሳኔው ተቀልብሶ ሲሰሩበት ወደነበረው ሳቢያን ሆስፒታል እንዲመለሱ እንዲደረግላቸው የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማኀበርን በደብዳቤ ጠይቀዋል።

ማኀበሩ ለድሬዳዋ ጤና ቢሮ የጻፈው ደብዳቤስ ምን ይላል ?

ሀኪሙ ወደ ሌላ ጣቢያ እንዲዘዋወሩ መደረጋቸውን ገልጾ፣ “በፌደራል መንግስት ሠራተኞች አዋጅ መሠረት የዝውውር ዋና ዓላማ ክፍት ቦታ ሲኖር ሥራንና ሠራተኞቸን ማገናኘት ነው እንጂ ዝውውር የቅጣት ውጤት አይደለም” ብሏል።

ይሁን እንጂ ለሠራተኛው የውስጥ ዝውውር ምክንያቱ " የዲስፕሊን ችግር " መባሉን ጠቅሶ፣ በሀኪሙ ላይ በመረጃ የተደገፈ የዲሲፕሊን ግድፈት ባለመኖሩ ወደ ስራ ቦታቸው እንዲመለሱ ሲል ቢሮውን ጠይቋል።

(የሀኪሙና የማኅበሩ ደብዳቤዎች ከላይ ተያይዘዋል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
912😭196🙏83👏67🕊19🤔12😢11💔8😱7😡4🥰3