TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ስምምነቱን ተከትሎ ተሽከርካሪዎቹ ተለቀዋል " - የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ፅ/ቤት

ወደ ትግራይ ክልል ሲጓዙ አፋር ላይ ለቀናት ክልከላ የተደረገባቸው ተሽከርካሪዎች እንዲለቀቁ ተወሰነ።

ውሳኔውን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል ጋር መወያየታቸውን ተከትሎ ነው ተግባራዊ የሆነው።

ፕሬዚዳንት ሌ/ጄነራል ታደሰ ግንቦት 23/ 2017 ዓ/ም ከኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ጋር ውይይት አድርገዋል።

በዚህም ከግንቦት 18 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ በአፋር በኩል ወደ ትግራይ ሲጓዙ ክልከላ የተደረገባቸው የጭነት ተሽከርካሪዎች የተከለከሉበት ምክንያት የጫኑት የንግድ እቃ ከትግራይ አልፎ በኮንትሮባንድ መልክ ወደ #ኤርትራ ሊሻገር ይችላል ከሚል ጥርጣሬ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ተገልጿል።

ሁለቱም ኃላፊዎች በውይይታቸው የመረጃው እውነትነቱ ምን ድረስ እንደሆነ የሚያጣራ ከፌደራል ፖሊስ እና ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የተውጣጣ ኮሚቴ ጉዳዩን እንዲመረምረው ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

የኮሚቴው የምርመራ ውጤት መሰረት በማድረግ የቁጥጥር ስርአት እንዲዘረጋ እና ተጠያቂነት እንዲሰፍን ይህን የማከናወን ተግባርና ኃላፊነት ደግሞ በዋናነት የጋራ ኮሚቴው እንዲሆን ተወስኗል።

ስምምነቱን ተከትሎ ተሽከርካሪዎቹ ተለቀዋል።

በቀጣይም ተመሳሳይ ችግር እንዳያጋጥም ኃላፊዎቹ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤታ ያሰራጨው መረጃ አመልክቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
1.18K🕊90😡77🙏50😢31🤔23🥰13💔8👏6