TIKVAH-ETHIOPIA
#USA #CHINA ቻይና አንዳንድ የአሜሪካ ምርቶችን ከጣለችው የ125% ታክስ ነፃ አደረገች። ቻይና ከአሜሪካ ወደ ሃገሯ የሚገቡ አንዳንድ ምርቶች ከጣለችው የ125% ታሪፍ ነፃ ማድረጓ እና ድርጅቶች ከታክስ ነፃ መሆን አለባቸው ብለው የሚያስቧቸውን ወሳኝ ዕቃዎች ለይተው እንዲለዩ መጠየቋን ሮይተርስ ከምንጮች አረጋግጦ ዘግቧል። የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለታይም መፅሄት በሰጡት ቃለ መጠይቅ…
#ቻይና #አሜሪካ #ታሪፍ
አሜሪካ እና ቻይና በምርቶቻቸው ላይ ጥለውት የነበረውን ታሪፍ ለመቀነስ ተስማሙ።
ሁለቱ የግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤቶች በተደጋጋሚ የአፀፋ ታሪፎችን እርስ በራሳቸው ሲጣጣሉ የነበረ ሲሆን በጄኔቫ ከተደረገ ውይይት በኋላ የአፀፋ ታሪፎቹን በ115% ለመቀነስ ተስማምተዋል።
አሜሪካ በቻይና ምርቶች ላይ ጥላ የነበረውን የ145% ታሪፍ በመቀነስ ወደ 30% ያወረደች ሲሆን ቻይና በአሜሪካ ምርቶች ላይ ጥላ የነበረውን የ125% ታሪፍ ወደ 10% ቀንሳለች።
አዲሱ የታሪፍ ቅነሳም ለሚቀጥሉት 90 ቀናት በስራ ላይ ይቆያል ተብሏል።
የአሜሪካ የግምጃ ቤት ሃላፊው ስኮት ቤሰንት የታሪፍ አፀፋዎቹ ሁለቱም ሃገራት የማይፈልጉት ነው በማለት ሃገራቱ አብረው መነገድ እንደሚፈልጉ ገልፀዋል።
ቤሰንት አዲሱ ስምምነት አንዳንድ ሴክተሮች ላይ የተጣሉ ታሪፎችን እንደማይመለከት የገለፁ ሲሆን አሜሪካ በመድሃኒት፣ ሴሚ ኮንዳክተር እና ብረት ላይ አሁንም ስትራቴጂካዊ የንግድ ሚዛንን ማስጠበቋን ትቀጥላለች ብለዋል።
በተጨማሪ ቻይና ከታሪፍ በተጨማሪ ውድ ማዕድናት ወደ አሜሪካ እንዳይላኩ ያስቀመጠችውን እገዳ ጨምሮ ሌሎች ከታሪፍ ውጪ የሆኑ የንግድ እገዳዎችን ታነሳለች ተብሏል።
የጄኔቫው ውይይት በሁለቱ ሃገራት ከፍተኛ አመራሮች መካከል ከትራምፕ ወደ ስልጣን መመለስ በኋላ የተደረገ የመጀመሪያ ውይይት ሲሆን በጊዜያዊነት ቢሆንም ሃገራቱ ከገቡበት የንግድ ጦርነት ፋታ እንዲወስዱ አድርጓል።
ሁለቱ ሃገራት ወደ ንግድ ጦርነቱ ከገቡ በኋላ የ600 ቢሊየን ዶላር የንግድ እንቅስቃሴ መቆሙ ከመነገሩ በተጨማሪ የሁለቱንም ሃገራት ኢኮኖሚ በክፉኛ ተጎድቷል።
ቻይናና አሜሪካ ይህ የመጀመሪያው ንግግር መሆኑን ያስታወቁ ሲሆን በንግድ እና ኢኮኖሚ ጉዳዮች ዙሪያ በቀጣይ በቻይና አሊያም በአሜሪካ ወይም በአማራጭነት በሶስተኛ ሃገር ውይይቶች እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።
የመረጃው ምንጮች ሲኤንኤን እና ሮይተርስ ናቸው።
@tikvahethiopia

👏479❤106🤔42🕊37🥰26🙏12😡10😭9😢4💔4😱1