TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.9K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ነዋሪዎች እየተካሄደ ነው ስላሉት አፈሳ ምን አሉ ? በተለያዩ ከተሞች ወጣቶች በግዳጅ በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች እየተያዙ እየተወሰዱ መሆኑን ነዋሪዎች ቅሬታ አቅርበዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸው በባህር ዳር፣ አዴትና ሞጣ እንዲሁም ጋይንት አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች " በ20ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ ያሉ ወጣቶችን የመከላከያና የአድማ ብተና መለዮ የለበሱ የመንግስት የፀጥታ አካላት ወጣቶችን እያፈሱ እስር…
የመከላከያ እና የኢሰመኮ ምላሽ ምንድነው ?

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮረኔል ጌትነት አዳነ ከቀናት በፊት በወቅታዊ የጸጥታ ጉዳይ ላይ ለመከላከያ ቴሌቪዥን በሰጡት መግለጫ ላይ የሰራዊት ምልመላን አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

" የመከላከያ ሰራዊት ህገ-መንግስታዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት በተፈጥሮም ሆነ በሰው ሰራሽ ነገር የሚወጣን ሰው ለመተካት እንዲሁም ሚዛን የጠበቀ የኃይል አሰላለፍ ታሳቢ ያደረገ የሰራዊት ዝግጅት ያስፈልጋል " ሲሉ የምልመላ አስፈላጊነትን ጠቅሰዋል።

ኮ/ል ጌትነት፥ " ተቋሙ በሚያወጣው መደበኛ የምልመላ መስፈርት ወጣቶችን ወደ ሰራዊቱ መቀላቀል በየትም ዓለም አቀፋዊ አሰራር ያለ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

ዳይሬክተሩ የምልመላ መስፈርቶች ብለው ካቀረቧቸው በዋናነት ፦
- ህገ-መንግስቱን የተቀበሉ፤
- ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ፤
- ሀገራቸውን ለማገልገል ሙሉ ፈቃደኛ የሆኑ፤
- ከማንኛውም ፖለቲካ ድርጅቶች ወገኝተኝነት ነጻ የሆኑ፤
- ስልጠናውን ከወሰዱ በኋላ 7 ዓመት ለማገልገል ውል የሚገቡ፤
- ከወንጀል ነጻ የሆኑ፤
- የሚወጡትን አካላዊ መስፈርቶች የሚያሟሉ የሚሉት በጥቂቱ የሚጠቀሱት ናቸው።

የምልመላ አሰራሩን በተመለከተ ዳይሬክተሩ ምን አሉ ?

የምልመላ ሂደቱ በወረዳ እና በቀበሌ ያሉ የፀጥታ እና የመስተዳድር አካላት በኮሚቴ ሆነው የሚያከናውኑት ነው ሲሉ አፈጻጸሙን በተመለከተም ለመከላከያ ሪፖርት የሚቀርብበት መሆኑን አንስተዋል።

ምልመላው የብሔር ሚዛናዊ ተዋጽኦ ያካተተ መሆን ስላለበትም ከብሔራዊ ስታስቲክስ ቢሮ በተወሰደ ቁጥራዊ የክልሎች መረጃ መሰረት መከላከያ ለክልሎች ኮታ እንደሚሰጥ ነው የተናገሩት።

አፈጻጸምን በተመለከተ ኮ/ል ጌትነት " እንደ አቅሙ ነው " በሚል የገለጹ ሲሆን ከወረዳ እና ቀበሌ የተደረገው ምዝገባ እንዲሁ የሚወሰድ ሳይሆን በዞን ደረጃ እንዲሁም ማሰልጠኛ ሲደርሱ የማጣራት ሥራ እንደሚሰራም አንስተዋል።

በዚህም የክልሎች ተወካዮች ባሉበት ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ተሰይሞ በፈቃዱ መምጣቱን ብቻ ሳይሆን ከተቀነሰም የተቀነስኩበት አግባብ ትክክል አይደለም ብሎ ቅሬታ ማቅረብ እንደሚቻል ነው ያነሱት።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በጉዳዩ ላይ ምን አለ ?

በየአካባቢው የሚስተዋሉ የወጣቶች አፈሳ ስለመኖሩ ቅሬታ ደርሷቸው እንደሆነ ከሪፖርተር ጋዜጣ ጥያቄ የቀረበላቸው ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ ተከታዩን ምላሽ ሰጥተዋል።

" ክትትሉ አልቆ የወጣ የተጠናቀቀ ዶክመንት የለንም። ሚዲያ ላይ የምንሰማው ነገር ስላለ ይሄን ይዘ [ከቀናት በፊት] ከሀገር ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለሞያዎች ጋር ተወያይተናል።

በእነሱ በኩል የምልመላ መስፈርቱ ላይ፤ የምልመላ አካሄዱ ላይ ምንም ችግር የለም ችግር ያለው ምንአልባት ታች አከባቢ የአስተዳደር አካላት ምልመላውን ሲያካሄዱ የሚፈጸሙ ትክክል ያልሆኑ አካሄዶች ካሉ በጋራ ለመስራት ተስማምተን ነው የተለያየነው " ሲሉ ገልጸዋል።

ኢሰመኮ ይህ ድርጊት ስለመፈጸሙ መረጃው ኖሮት ነው ውይይቱን ያደረገው ?

ዋና ኮሚሽነሩ በዚህ ጉዳይ ላይ በሰጡት ቃል ኮሚሽኑ ዓለም አቀፍ መስፈርቶችን በመከተል አስገዳጅ ወታደራዊ ምልመላ እየተካሄደ መሆን አለመሆኑን እያጣራ እንደሚገኝ እና ሥራው ሲጠናቀቅ ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

በዚህም ኮሚሽኑ ዓለም አቀፍ ስታንደርዱን ጠብቆ የቀረበ ዶክመንት ወይም Standard of Proof ጨርሶ መደምደሚያ ላይ አለመድረሱን ጠቁመው ይህ ሲጠናቀቅ በየአራት ወሩ በሚወጣው ሪፖርት አካተው እንደሚያወጡ ተናግረዋል።

ውይይቱን በተመለከተ ግን ኮሚሽነሩ " ሚዲያ ላይ የምንሰማው ነገር ስላለ እሱን ይዘን ነው ከመከላከያ ሚኒስቴር ባለሞያዎች ጋር የተወያየነው " ሲሉ ውይይቱ በግል ተነሳሽነት ጭምር የተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

#FDREDefenseForce #EHRC

@tikvahethiopia
😡57881😭70🙏21💔17👏9🕊9🤔8🥰4😢4😱1