TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.61K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ጋምቤላ

“ አውቶብሱ እየተጓዘ የሙርሌ ታጣቂዎች ከመንገድ አድፍጠው ተኩስ ከፍተውበት አራት ወንዶች፣ ሁለት ሴቶች መኪናው ውስጥ እንዳሉ ተገድለዋል ” - ክልሉ

ከዲማ ወደ
ጋምቤላ ከተማ ከ30 በላይ ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ አውቶብስ የሙርሌ ታጣቂዎች በከፈቱበት ተኩስ ንጹሐን መገደላቸውን የጋምቤላ ክልል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኦጁሉ ጊሎ በሰጡን ቃል፣ የመርሌ ጎሳ ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ 6 ተሳፋሪዎች መገደላቸውን ገልጸዋል።

ጥቃቱ የተፈጸመው እሁድ ግንቦት 17 ቀን 2017 ዓ/ም እንደሆነ፣ አውቶብሱ እየተጓዘ የሙርሌ ታጣቂዎች መንገድ ላይ ደፈጣ ይዘው ተኩስ እንደከፈቱበት፣ የጸጥታ አካላት አሁንም ክትትል እያደረጉ እንደሆነ አስረድተዋል።

“ አራት ወንዶች፣ ሁለት ሴቶች ከመኪናው እንዳሉ ተገድለዋል ” ሲሉ ገልጸዋል።

ከሟቾች ባሻገር በጥቃቱ የቆሰሉ እንዳሉ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የጠየቃቸው ሲሆን፣ እስካሁን የደረሳቸው መረጃ የሟቾቹ እንደሆነ ተናግረዋል።

በአጋጣሚ በአውቶብሱ ተሳፍሮ የነበረ አንድ የክልሉ ቀበሌ ሚሊሻ በአንድ የሙርሌ ታጣቂ ላይ የአጸፋ እርምጃ ወስዶበት ታጣቂው እንደተገደለ የሚመለከት መረጃም እንደደረሳቸው አስረድተዋል።

“ ታጣቂዎቹ ከብት መዝረፍ፣ ህፃናት መውሰድ የለመደባቸው ትሬንድ ነው። እሁድ ባሱ የተመታበት ቦታ ብዙ ጊዜ የወረዳው ከፍተኛ አካላት ትኩረት የሚያደርበት ነው። ግን የትላንቱ ክስተት በአጋጣሚ ከባድ ነበር ” ብለዋል።

ከዚህ ቀደም በሙርሌ ታጣቂዎች ተገደለ የሚባለው አንድ፣ ሁለት ሰዎችን እንደነበር ያስታወሱት አቶ ኦጁሉ፣ “ የትላንቱ ጥቃት ትንሽ የሚያሳዝን ነው። ሆኖም ግን እዛ አካባቢ የጸጥታ አካላት አሁንም ቁጥጥር በአግባቡ ይሰራሉ ” ነው ያሉት።

ክልሉ ከወር በፊት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል፣ “ በተለይ እስከ ሚያዚያ መጨረሻ ድረስ ታጣቂዎቹ የሚፈታተኑንበት ወቅት ነው። ኩሬዎች ስለሚደርቁ ለእነርሱ መምጣት አመቺ ይሆናል። አሁን ትንሽ፣ ትንሽ ምልክቶችን እያየን ነው። እየመጡ ነው ” ብሎ ነበር።

“ በተለይ ታጣቂዎቹ የሚገቡባቸው በሮች ላይ የሁላችንም የጋራ ጥረት ያስፈልጋል። ይሄን ሁሉን ድንበር በሰራዊት ለማስጠቅ በጣም አስቸጋሪ ነው ሰፊ ቦርደር ነው ” ሲል አስገንዝቦም ነበር።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
😭885205😡91🤔53💔43🕊34😢32👏27🙏23🥰22😱14
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ጋምቤላ

" አራት ሴቶች በደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ታፍነዉ ተወስደዋል " - የጋምቤላ ክልል ፖሊስ

➡️ " በአንድ ዓመት ብቻ 16 ሕፃናት እና በመቶዎች የሚቆጠሩ ከብቶች በታጣቂ ቡድኑ ተወስደዋል ! "


የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ኦጉላ ኡጁሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት በትናትናው ዕለት ከቀኑ 7 ሰዓት አከባቢ በአኝዋክ ብሔረሰብ ዞን በጎጊ ወረዳ ተዶ በሚጠራዉ አከባቢ የሙርሌ ታጣቂዎች አራት ሴቶችን አፍነዉ መዉሰዳቸዉን ተናግረዋል።

" ሙርሌ" የተሰኘዉ የደቡብ ሱዳን ታጣቂ ቡድኑ ከ14 እስከ 27 ዓመት ዕድሜ ክልል ዉስጥ ያሉ አራት ሴቶችን ወደ ፒኝውዶ ከተማ በመጓዝ ላይ እያሉ ተኩስ በመክፈት አፍኖ እንደወሰዳቸዉ የገለፁት ኮሚሽነሩ አስቀድሞ በአከባቢዉ የነበሩ የጎግ ወረዳ ፖሊስ አባላትና ሚሊሻዎችን በኋላም የፌዴራል ፖሊስ፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የፀጥታ መዋቅር የጋራ ግብረ ሃይል ታፍነዉ የተወሰዱትን ለማስመለስ ቡድኑን እየተከታተሉ መሆናቸዉንም አስታዉቀዋል።

በደቡብ ሱዳን የሚንቀሳቀሰው የሙርሌ ታጣቂ ቡድን ከጋምቤላ ክልል የተለያዩ አከባቢዎች በተደጋጋሚ ሰዎችን እያፈነ እንደሚወስድ የተናገሩት ኮሚሽነር ኦጉሉ በፀጥታ ሃይሎች ኦፕሬሽን ከተመለሱት በስተቀር አብዛኞቹን እንደሚገድልና ሱዳን ወስዶ ለጉልበት ስራ እንደሚሸጣቸዉም መረጃዎች እንደሚደርሷቸዉ ገልፀዋል።

ኮሚሽነሩ አክለዉም በ2017 ዓ/ም ብቻ 16 ሕፃናት እና በመቶዎች የሚቆጠሩ ከብቶች በነዚህ የታጠቁ ቡድኖች ተዘርፈዋል ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
679😢338😭114😡97💔44🕊30🙏20🤔19😱18🥰7👏1