TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.2K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
🕊#Peace

" ለችግሮቻችን መፍትሄ ከጠመንጃ ይልቅ የጠረጴዛ ውይይት እናስቀድም "  - የሰላም ሚኒስቴር ሚንስትር 

➡️ " በአሁኑ ሰዓት ትልቅ የህልውና አደጋ ለተጋረጠበት የትግራይ ህዝብ ስለ ዴሞክራሲና ልማት ማውራት ቅንጦት ነው " - የጠቅላይ ሚንስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚንስትር 


በአዲስ አበባ ከተማ " ሰላም ፣ ዲሞክራሲ እና ልማት በትግራይ እድሎችና ፈተናዎች " በሚል ርእስ የውይይት መድረክ ተካሂዶ ነበር።

የውይይት መድረኩ CENTRE FOR RESPONSIBLE AND PEACEFUL POLITICS (CRPP) የተባለ ተቋም ከአዲስ አበባ ዪኒሸርስቲ በመተባበር ነው ያዘጋጁት።

የውይይት መድረኩ ላይ ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉት የሰላም ሚንስቴር ሚንስትር አቶ መሐመድ እድሪስ " ከመነጋገር እናተርፋለን " ብለዋል።

" ሃሳብ ነው ሃገርን የሚገነባው ስለሆነም ለሃሳብ ክብርና ልዕልና እንስጥ ፤ ጠመንጃንና ጦርነትን እንጠየፍ የትግራይ የፓለቲካ ምህዳር ለወጣቶች እድልና ቅድሚያ ይስጥ " ሲሉ ተናግረዋል።

" ' አንዋጋም ይበቃል ' ማለት ታላቅ ድፍረት ይጠይቃል ከተቻለ ግን ውጤቱ እጅግ አመርቂና ፍሬውም ጣፋጭ ነው። ስለሆነም እርስ በርስ መዋጋት ይብቃ ፤ ሳንገዳደል አሸናፊ የምንሆንበት ሰላማዊ መንገድ እናስቀድም የመገዳደል የመተላለቅ ታሪክ ልንዘጋው ይገባል " ሲሉ ተደምጠዋል።

የጠቅላይ ሚንስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚንስትር አቶ ጌታቸው ረዳ፥ " የትግራይ ህዝብ አሁንም ከህልውና አደጋ አልወጣም " ብለዋል።

" ችግሮቻችን በውጭ ምክንያቶች እያሳሰበን ከመኖር ውስጣችን በደምብ በመፈተሽ የተወሳሰቡ ችግሮቻችን መፍታት እንችላለን " ሲሉ ገልጸዋል።

" ትግራይ ጥቂት አመራሮች ማረምና ማንሳት አቅተዋት በከባድ ፈተና ተዘፍቃ ትገኛለች ፤ ይህንን ከባድ ፈተና ለመወጣትና ለማለፍ ወጣቶችን ወደ መሪነት ማምጣት ይጠበቅበታል " ብለዋል።

" በአሁኑ ሰዓት ትልቅ የህልው አደጋ ለተጋረጠበት የትግራይ ህዝብ ስለ ዴሞክራሲና ልማት ማውራት ቅንጦት ነው " በማለት አክለዋል።

ለአንድ ቀን በተካሄደው የውይይት መድረክ " ሰላምና ደህንነት ፣ ዲሞክራሲ ግንባታ ፈተና እና እድል " የሚሉና ሌሎች የመወያያ ፅሁፎች ቀርበዋል።

በመድረኩ ከትግራይ የተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ፣ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ፣ ስቪክ ማህበራት እንዲሁም በአዲስ አበባ የሚኖሩ ታዋቂ ሙሁራንን ፓለቲከኞች ተገኝተው ነበር።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamilyMK

@tikvahethiopia            
612😡104🕊50🙏20🤔13😱9😭9🥰7👏7😢2
🕊#Peace

" የትግራይ ፓለቲከኞች ሃላፊነት ከጎደለው የመተላለቅ እንቅስቃሴ ተቆጠቡ " - ጉባኤው

" በትግራይ የእርስ በርስ መተላለቅ የሚጋብዝ ፕሮጀክት የተወገዘና ተቀባይነት የሌለው ነው " አለ የትግራይ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ።

ጉባኤው የትግራይ ፓለቲከኞች ሃላፊነት ከጎደለው የመተላለቅ እንቅስቃሴ እንዲቆጠቡ ሲል በፅኑ ተማፅኗል።

" ህዝብን በማሳተፍ ለሰላም ፣ ለፍቅር ለፍትህና ለአንድነት እሰራለሁ " ሲል ያሳወቀው ጉባኤው " በመሪዎች መካከል የተፈጠረው ተግባብቶ ያለመስራት ችግር ህዝቡ ለስደት፣ ለመፈናቀልና ለሞት የዳረገ የሚወገዝ ተግባር ነው " ብሏል።

" ገና ከጦርነት ባለገገመች ትግራይ ትግራዋይ ከትግራዋይ ለመተላለቅ ያለመ ፕሮጀክት ተደግሷል " ያለው  ጉባኤው " ይህ አደገኛ ፕሮጀክት ለትግራይ ህዝብ ታሪክ የማይመይጥን ነው " ብሎታል።

በአገር ውስጥና በመላ ዓለም የሚገኝ ትግራዋይ ሆደ ሰፊና አስተዋይ እንዲሆን መክሮ " በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ በጋራ እንቁም " ሲል ጥሪ አቅርቧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
1.31K🕊231💔49🤔43😡40🙏27👏25😭25😱13🥰9😢1
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ🇪🇹 የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ፥ " በአገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች የሚደረግ ምክክርና እርቀ ሰላም ፍሬው ጣፋጭ ነው " አሉ። ትናንት ሀምሌ 10/2017 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ ያቀኑት የትግራይ የሃይማኖት አባቶችና የአገር ሸማግሌዎች ዛሬ ሀምሌ 11/2017 ዓ.ም ከኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) መክረዋል። የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ…
#Peace🕊

የትግራይ ክልል አመራሮችና ፓለቲከኞች አሁንም በፍፁም ትዕግስትና ቻይነት የተጀመረውን ሰላም እንዲያፀኑና ከዳር እንዲያደርሱ ተማፅኖ ቀረበ።

ተማፅኖ ያቀረቡት ከ12 ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ የሃይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች ናቸው።

ቁጥራቸው 50 የሆኑት መላ የኢትዮጵያ ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች የወከሉ የሰላም ልኡካን ዛሬ ሀምሌ 21/2017 ዓ.ም ጠዋት መቐለ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፍያ ሲደርሱ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ፣ የሃይማኖት አባቶች ፣ የአገር ሽማግሌዎች ፣ ባለሃብቶችና ታዋቂ ሰዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ከአውሮፕላን ማረፍያ ውይይቱ ወደ ሚካሄድበት ቦታ ያቀኑት የሰላም ልኡካኑ ፕሬዜዳንት ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደና እና ካቢኔያቸው በተገኙበት በየእምነታቸው ፀሎት አድርሰዋል።

የክልሉ አመራሮችና ፓለቲከኞችም ለተሻለ ሰላምና አገራዊ መረጋጋት አሁንም በፍፁም ትዕግስትና ቻይነት ተጨማሪ ግጭት እንዲያስቀሩ አባታዊና ሃይማኖታዊ ምክርና ተማፅኖ ቀርበውላቸዋል።

የሰላም ልኡካኑ ከጦርነቱ በፊት ወደ ትግራይ ተመላልሰው ያደረጉት ጥረት ግጭቱ ማስቀረት ባለመቻሉ በቁጭት አስታውሰው  ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በኃላ ለሦሥተኛ ጊዜ መምጣታቸውና የሰላም ጥረታቸው ሳይታክቱ እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።

" የጀመረው ሰላም እንዲፀና ፤ ዳግም ጦርነት እንዳይቀሰቀስ ከመስራትና ከመጣር የበለጠ ሃይማኖታዊና አባታዊ ተልእኮ የለንም ለዚህም የሚከፈለውን ሁሉም ዓይነት መስዋእትነት እንከፍላለን " ብለዋል።

የሰላም ልኡካኑ ከትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደርና ካቢኔያቸው ፣ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ አባላት፣  የተፎካካሪ የፓለቲካ ፓርቲ አመራሮችና ስቪክ ማህበራት እንደሚወያዩ ከወጣው መርሀ ግብር ሐመረዳት ተችሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamliyMekelle

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
625🕊155😡30🤔26🙏24👏7😭4🥰3😱3💔2
#Tigray 🇪🇹 #EthiopianNationalDialogue

መተማመን እንዲጎለብትና ዘርፈ ብዙ ችግሮች በሰላማዊ መንገድ መፍታት እንዲቻል የፖለቲካ ውይይት ማካሄድ ወሳኝና አስፈላጊ እንደሆነ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን አሳወቀ።

የትግራይ ጊዝያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀኔራል ) በበኩላቸው የምክክር ኮሚሽኑ ዓላማና ጥረት ለዘላቂ ሰላም ያለውን አወንታዊ አስተዋፅኦ እንደሚገነዘቡ አረጋግጠዋል።

ዛሬ በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የፕሬዜዳንት ፅህፈት ለመጀመሪያ ጊዜ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ አመራሮች ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች ጋር የፊት ለፊት ግንኙነት አደርገዋል።

የምክክር ኮሚሽኑ ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ፣ " አገራዊ ችግሮችና ቁርሾዎቻችን ከንግግርና ውይይት ውጪ ሌላ ፍቱን መድሀኒት የላቸውም " ብለዋል።

" አገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ህዝብን የሚያቃቃሩ ትርክቶች ነቅሶ በንግግርና ውይይት በመፍታታ ህዝባዊና አገራዊ መግባባትና መተማመን ፅኑ መሰረት እንዲይዝ አልሞ እየሰራ ነው " ብለዋል።

የአገራዊ የምክክር ኮሚሽኑን ዓላማው አስፈላጊነት በማመን የተናገሩት ፕሬዚዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጄነራል) " ከምክክሩ በፊት በፌደራል መንግስትና በትግራይ ክልል መካከል የሚካሄድ የፖለቲካ ውይይት መቅደም አለበት " ብለዋል።

" የትግራይ ህዝብና መንግስት መልሶ ወደ ግጭትና ጦርነት አዙሪት የመግባት ፍላጎት ፈፅሞ የለውም " ያሉት ፕሬዜዳንቱ ፤ የምክክር ኮሚሽኑ በክልሉ ለሚሰራቸው ስራዎች ራሳቸውንና ካቢኔያቸው ተባባሪ ለመሆን ያላቸው ቁርጠኝነት ማረጋገጣቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከፕሬዘዳንት ፅህፈት ቤት ያገኘው መረጃ ያሳያል።

#Peace #Ethiopia

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
908🕊159😡49🙏44😭44🤔15😢13🥰9😱1
#Peace🕊

" 35 አመት ተዋግተዋል፣ አሁን ግን ወዳጆች ሆነዋል " - አሜሪካ

ከ1980ዎቹ አንስቶ ጦርነት ውስጥ የነበሩት አርሜኒያና አዘርባጃን በአሜሪካ አማካኝነት የሰላም ስምምነት ፈጽመዋል።

የአዘርባጃን ፕሬዚዳንት ኢልሃም አሌቭ እና የአርሜኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ኒኮል ፓሽኒያን የፈረሙት ስምምነት ለአስርት አመታት የዘለቀውን ግጭት ያስቆማል ተብሏል።

የሰላም ስምምነቱን የአሜሪካው ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሸማግለዋል።

ፕሬዚዳንት ትራምፕ የሰላም ስምምነቱን " ረጅም ጊዜ የወሰደ ታሪካዊ ስምምነት ነው " ብለውታል።

ሁለቱ ሀገራት በአወዛጋቢው የናጎርኖ ካራባህ ግዛት ጦርነት ውስጥ እንደነበሩ ያስታወሱት ትራምፕ ግጭቱን " እስከወዲያኛው ይወገዳል " በማለት ተናግረዋል።

ትራምፕ፣ " 35 አመት ተዋግተዋል፣ አሁን ግን ወዳጆች ሆነዋል " ብለዋል።

በስምምነቱ መሰረት ሁለቱ ሀገራት የትራንስፖርት አገልግሎት፣ የንግድ ግንኙነትና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች እንዲጀመሩ እና ለተፈፃሚነቱ አሜሪካ ጣልቃ እንድትገባ ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

Via @ThiqahEth
575🕊114👏62🤔26😡9🥰7😱6😢5💔4🙏3