TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.2K photos
1.62K videos
218 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#አፋር #ቤንዚን

“አንድ ሊትር ቤንዚን በብላክ ማርኬት ከ250 ብር በላይ ገዝተን ሰርትን መተዳደር በጣም ከብዶናል” - የሰመራ ከተማ አሽከርካሪዎች

“ባለፉት ስድስትና ሰባት ቀናት ውስጥ በጣም ከፍተኛ የነዳጅ እጥረት አለ” - የአፋር ክልል ንግድ ቢሮ

በአፋር ክልል በተለይም ሰመራ ከተማ ያሉ ባለሦስት እግር ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች ቤንዚን ከማደያ እንዳይቀዱ በመከልከላቸው አንድ ሊትር ቤንዚን በችርቻሮ ከ250 ብር ገዝተው ሰርተው የኑሮ ውድነቱን መቋቋም ባለመቻላቸው ተማረሩ።

የከተማዋ አሽከርካሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ?

“እዚህ ከተማ እየተደረገ ያለው፥ የነዳጅ ቦቴዎች አልፎ አልፎ ይመጣሉ፡፡ ያም ማደያ ጉድጓድ ውስጥ ይገለበጥና እንደገና ወደ ጀሪካን እየቀዱ በማደያ ቤቱ አጠገብ ባሉ የችርቻሮ ኮንቴነሮች ይሸጣል።

እዛ ላይ በ200 ብር ነው አንድ ሊትር
ቤንዚን የምንቀዳው፡፡ ወደ ደረቅ ወደብ ማደያዎች ያሉም እንደዚሁ በብላክ ማርኬት ነው የሚገዙት፡ 

በችርቻሮ የሚሸጡልን ከማደያው በገሃድ በጀሪካን ቀድተው ነው የሚረከቡት፡፡ የሚቸረችሩት አንድ ሊትር
ቤንዚን ከ260 ብር በላይ ነው የሚሸጡት።

ከማደያ ላይ መቅዳት አይታሰብም፤ አንድም ቀን ቀድተን አናውቅም፡፡ 

መፍትሄ ተሰጥቶት የምንሰራበት ሁኔታ ይመቻችልን፡፡ በዚህ ኑሮ ውድነት
ቤንዚን በብላክ ማርኬት ከ250 ብር በላይ ገዝተን ሰርትን ገቢ ማግኘትና መተዳደር በጣም ከብዶናል፡፡ ከምንለው በላይ ነው ሁሉም የተቸገረው” ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ የባለሦስት እግር ሹፌሮች፣ “ ቤንዚን ማደያ እንዳንቀዳ ተከልክለናል ፤ በችርቻሮና ኮንትሮባንድ ዋጋ ነው የምንቀዳው ” ብለዋል፤ ጉዳዩን ተመልክታችሁት ነበር? ሲል የአፋር ክልል ንግድ ቢሮን ምላሽ ጠይቋል።

የክልሉ የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አሕመድ አብዱልቃድር ምን መለሱ ?

“ ማደያ ላይ ቤንዚን ድሮም አይቀዳም፡፡ ምክንያቱም በጣም ኃይለኛ ሙቀት ስላለ ጉድጓድ ላይ ቤንዚን ከተቀዳ አደጋ ያደሰርሳል።

ነገር ግን ማደያዎች አውርደው እዛው አካባቢ ነው ሹሬሮች የሚቀዱት፡፡ በጣም ኃይለኛ ሙቀት ስላለ ከዚያ አንጻር የሚቀዳው እንደዛ ነው፡፡ አዋሽ ግን በማደያ ነው የሚቀዳው ቀዝቀዝ ስለሚል፡፡

ሰመራ ከተማ ኮንትባንድ የለም፡፡ ግን የነዳጅ እጥረት አለ በኃይለኛ፡፡ በተለይ ሰማራ የክልሉ ዋና ከተማ ብቻ ሳይሆን የውጭ ንግድ የሚያልፈበት ከተማ እንደመሆኑ መጠን ባለፉት ስድስትና ሰባት ቀናት ውስጥ በጣም ከፍተኛ የነዳጅ እጥረት አለ።

ትልልቅ ካምፓኒዎች ጋር ለማዳረስ ጥረት እየተደረገ ነው ያለው፤ ኖክና ኦይልቪያ፡፡ ግን ሁሉም ማደያዎች ካላመጡ ወዲያው ነው የሚያልቀው፡፡ አብዛኛዎቹ መኪኖች ከአዋሽ እዚህ ለመቅዳት ነው የሚመጡት፡፡

ለመቅዳት ሲመጡም አንድ መኪና በቀን ማግኘት ያለባቸው ሰዎች የሚያገኙት በ2 ቀናት፣ በ3 ቀናት አንድ መኪና ከሆነ ሎዱ ይበዛል። እጥረቱን ከነዳጅና ኢነርጅ ባለስልጣን ጋር ሆነን ለመፍታት ጥረት እያደረግን ነው ”
ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
😭491172😁84🙏41😱39😢26🤔20👏19🕊19😡12🥰6