TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ፓስፖርት : ፖስፖርት ለማውጣት ፋይዳ መታወቂያ መያዝ የግዴታ እንደሚያስፈልግ ተገልጿል። ከሰኔ 1/2017 ጀምሮ የፋይዳ መታወቂያ ለፓስፖርት አገልግሎት ከሚስፈልጉ ዋና ሰነዶች ውስጥ አንዱ ይሆናል። ከሰኔ 1 በኃላ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የፓስፖርት አገልግሎት ጥያቄ አቅርበው በመጠባበቅ ላይ ያሉ ግለሰቦች ፓስፖርት ለመውሰድ ሲመጡ የፋይዳ መታወቂያ ፦ - ልዩ ቁጥር መያዝ፣ - QR ኮዱን በወረቀት…
#ፋይዳ #NationalID

ከትላንት በስቲያ ሰኞ ጀምሮ ፋይዳ መታወቂያ ለፓስፖርት አገልግሎት አስፈላጊ ከሆኑ ሰነዶች መካከል አንዱ ሆኗል።

ፓስፖርት ለማውጣት ፋይዳ መያዝ የግድ ያስፈልጋል።

ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ለመመዝገብ በአቅራቢያ በሚገኝ የምዝገባ ጣቢያ
id.gov.et/locations በመሄድና በመመዝገብ የታተመ QR ኮድ ወይም በስልክ ዲጂታል ኮፒ በመያዝ አገልግሎት ማግኘት ይቻላል።

የብሔራዊ መታወቂያ አገልግሎት ፅ/ቤት  " ወደ ኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ፅ/ቤት ከመሄዳችሁ በፊት በአቅራቢያችሁ ባሉ ማዕከላት ተመዝግባችሁ ኮዱን ማሳተም እና መያዝ ይኖርባችሗል " ብሏል።

" QR ኮድን ከ " Fayda ID " ሞባይል መተግበሪያ ፣ ከቴሌብር ሱፐር አፕ፣ እንዲሁም ሲቢኢ ብር ሞባይል መተግበሪያ ላይ በማውረድ እና በወረቀት በማሳተም መያዝ ይቻላል " ሲል ገልጿል።

የፋይዳ ቁጥር ያልደረሰው ወይም ከጠፋበት በተመዘገበበት ስልክ *9779# በመደወል ወይም የፋይዳ መተግበሪያ " Fayda ID " በመጠቀም በድጋሚ ማስላክ እንደሚችል ተመላክቷል።

በምዝገባ ወቅት የመረጃ ስህተት ካጋጠመም
id.gov.et/update ወይም በ "Fayda ID" ፋይዳ ሞባይል መተግበሪያ በቀላሉ ማስተካከል ይቻላል።

#ፋይዳለኢትዮጵያ

@tikvahethiopia
744😡162🥰22😭21🙏19🕊13👏5🤔4😱3😢2