TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.2K photos
1.62K videos
218 files
4.4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" የግብፅ እና ኢትዮጵያ ጨዋታ የኪሳራ ጨዋታዎች ናቸው። ... ለመሸነፍ ለመሸነፍ ብዙ ወጣት ተጫዋቾች አሉን " - መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ

የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አክስዮን ማህበር በፋይናንስ አሰራር ተቆጣጣሪ ኮሚቴ በተላለፉ ወሳኔዎች ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ በትላንትናው ዕለት ሰጥቶ ነበር።

የሊጉ አክስዮን ማህበር የፋይናንስ አጣሪ ተቆጣጣሪ ኮሚቴ የፋይናንስ ደንቡን በጣሱ ክለቦች እና ተጨዋቾች ላይ የቅጣት ውሳኔ ከቀናት በፊት አስተላልፎ የነበረ ሲሆን በተላለፈው ቅጣትም 4 ክለቦች እና 15 ተጫዋቾች ላይ ባደረገው ምርመራ ክለቦቹ የቅድመ ክፍያ(በሶስተኛ ወገን) ከፍለዋል በማለት 45 ሚልዮን ብር ቀጥቷል።

የአክስዮን ማህበሩ የቦርድ ሰብሳቢ መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ በሰሞነኛ የክለቦች የዝውውር ክፍያ ስርዓት ላይ በተሰጠ መግለጫ የብሔራዊ ቡድኑ ተጫዋቾች እንደሚቀጡ አስረግጠው ተናግረዋል።

ከጋዜጠኞች ይቀጣሉ ወይ ? ተብሎ ለተነሳላቸው ጥያቄ " አዎ ይቀጣሉ " ሲሉ መልሰዋል።

በቀጣይ ከግብፅ ጋር ስለሚደረግ ጨዋታ ሲጠየቁም " እሱን ግጥሚያ ብለህ ትጠራለህ ? ማሟያ ነው " ብለዋል።

መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ አያይዘውም " ካፍ ስላስገደደን ነው የምንሄደው የኪሰራ ጨዋታዎች ናቸው ፣ ለመሸነፍ ለመሸነፍ ብዙ ወጣት ተጫዋቾች አሉን " የሚል ምላሽን ለጋዜጠኞች ሰጥተዋል።

ዋልያዎቹ ከሶስት ሳምንት በኃላ በዓለም ዋንጫ ማጣርያ መርሐ ግብር በሞሮኮ ካሳብላንካ ዛውል አል አረቢ ስታዲየም የግብፅ አቻውን ይገጥማል።

ዋልያዎቹ ለመጨረሻ ጊዜ ከሁለት ዓመት በፊት በሜዳቸው ማድረግ የነበረባቸውን መርሐ ግብር በማላዊ ባደረጉበት ወቅት በሽመልስ በቀለ እና ዳዋ ሆቴሳ ጎሎች 2ለ0 ማሸነፋቸው የሚታወስ ነው።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
😁479108👏49😭27😡25😢8🕊8😱7🥰3
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ትግራይ ሌላ ዙር ጦርነት ታስተናግድ ይሁን ?

አቶ ጌታቸው ረዳ ፦

" ትግራይ በፍጹም ጦርነት ማስተናገድ አትችልም።

አንድም የትግራይ ወጣት ለእንደዚህ አይነት ርካሽ ተግባር መስዋዕት ለመሆን ዝግጁ አይደለም።

በእርግጠኝነት መናገር የምችለው ትግራይ ላይ ጦርነት በሌላ አካል ከታወጀ ብቻ ነው የትግራይ ወጣት ሊዋጋ የሚችለው ከዚህ ውጭ የእገሌን ወንበር ለማዳን ብሎ መስዋዕት የሚሆን ወጣት የለም። በምንም መልኩ !!

የሰረቀውን ገንዘብ ለማቆየት ብሎ ወዲያ ወዲህ የሚንከላወስ የሆነ ሰው አይጠፋም ግን እሱ ብቻውን ነው። አላፊ አግዳሚውም በክርኑም በምኑም ያስቆማዋል።

ግን የህዝብ ትርምስ ለማስመሰል የግል አጀንዳቸውን የህዝብ አጀንዳ ለማስመሰል የሚያደርጉት ጥረት ምን ያስመስለዋል ትግራይ ሌላ ዙር ጦርነት የናፈቀው ነው የሚያስመስለው ሆታው።

የትግራይ ህዝብ በፍጹም ሌላ ጦርነት ማስተናገድ አይችልም። በቂ ሞተናል፣ በቂ ረግፈናል፣ በቂ መሰረተ ልማት ወድሟል።

ሁሌ እናገራለሁ መፎከር በኔ ነው የሚያምረው በቂ ብለናል ያኔ የምንለውን ብለናል አሁን ግን ሌላ የሰላም ምዕራፍ ሲፈጠር ሁሉንም አጋጣሚ ተጠቅመህ የትግራይ ህዝብ እንደገና እንዳይንበረከክ እኔ ልንበርከክ ነው ማለት ያለብህ። "

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
765🕊168😁121🙏53😡27😭20👏17🤔8😱7🥰3😢2
🔈#የጤናባለሙያዎችድምጽ

" አስተዳደራዊ በደል በድሬዳዋ ጤና ቢሮ ተፈፅሞብኛል " - የሳቢያን ሆስፒታል ሀኪም ዶክተር ሀብታሙ አለሙ

➡️ " በሆስፒታሉ ከተቀጠረ ጀምሮ እስካሁን ድረስ የቀረበበት የዲስፕሊን ጉድለት የለም " - የሳቢያን ሆስፒታል የዲሲፕሊን ኮሚቴ


በድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ሳቢያን ሆስፒታል የጠቅላላ ህክምና ሃኪም የሆኑት ዶክተር ሀብታሙ አለሙ በሀገር አቀፍ ደረጃ የህክምና ባለሙያዎች ያቀረቡትን ቅሬታ በመደገፋቸው በቢሮው አስተዳደራዊ በደል ተፈፅሞብኛል በማለት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተውና ለባለሞያው የተጻፈው ደብዳቤ " ለስራ በተመደበበት ክፍል የሙያ ስነምግባርን በተፃረረ መልኩ በእናቶች እና በህፃናት ክፍል ወላድ እናቶችን በተደጋጋሚ ማመናጨቅ፣ መሳደብ እና ያለአግባብ ማመላለስ እና ማስጠንቀቂያ ቢሰጥም ባለመታረሙ ወደ ገኦዳ ጉዱንፈታ ጤና ጣቢያ አዘዋውረናል " የሚል ነው።

የጤና ባለሙያው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ?

" በሀገር አቀፍ ደረጃ የህክምና ባለሙያዎች የደመወዝ ጭማሪ ይደረግልን ተብሎ ቅሬታ ሲያቀርቡ ለምን ሃሳቡን ደገፍክ ብለው የድሬዳዋ ከተማ ጤና ቢሮ ሃላፊ እና ምክትል ደውለው ለምን ይሄን አደረክ አሉኝ፣ እኔም ጥያቄው እንደሀገር ነው የቀረበው፣ እንደ ድሬዳዋ አይደለም፣ ይሄ ደግሞ የመብት ጥያቄ ነው ብየ መለስኩኝ ።

የሃላፋዎች ምላሽም በድሬዳዋ ከተማ አንደዚህ መንቀሳቀስ አትችሉም፣ የከተማችንን ስም ያቆሽሽብናል፣ ስለዚህ የህክምና ባለሙያው ዝም ነው ማለት ያለበት አሉኝ።

በነጋታው ከሰዓት የዝውውር ደብዳቤ እና የዲስፕሊን ጉድለት አለብህ ብለው ከሃላፊዎች ሲሰጠኝ የጤና ቢሮ ሃላፊዋን ዶክተር ፅጌሬዳን ለማናገር ቢሮ ስሄድ ባለማግኜቴ ስልክ በመደወል ሳናግሯቸው ቅድሚያ ስሜን አጥፍተሀል እና ፌስቡክ ላይ ይቅርታ ብለህ ፃፍ ከዚያ ውጭ አላናግርህም አሉኝ " ሲሉ አስረድተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በዚህ ላይ ስማቸው የተጠቀሰው የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ጽጌረዳ ክፍሌ እንዲሁም ምክትል ኃላፊ አቶ ዩሱፍ ሰይድ ለማነጋገር በተደጋጋሚ ስልካቸው ላይ ቢደውልም ምላሽ ማግኘት አልቻልም።

በጉዳዩ ላይ የሳቢያን ሆስፒታል የዲሲፕሊን ኮሚቴ ምን አለ ?

ዶ/ር ሀብታሙ " እንደ ሆስፒታል በዲስፕሊን ተፅፎብኝ የሚያውቅ ደብዳቤ የለም " ማለታቸውን ተከትሎ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሳቢያን ሆስፒታል የዲሲፕሊን ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑትን ዶክተር አባይነህን ጠይቋል።

በምላሻቸውም " በሆስፒታሉ ከተቀጠረ ጀምሮ እስካሁን ድረስ የቀረበበት የዲስፕሊን ጉድለት ክስ #የለም " ሲሉ ማረጋገጫ ሰጥተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህንን መረጃ እያዘጋጀ በነበረበት ወቅት የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ ሲስተር መስከረም አሰፋ በኃላፊነት ቦታቸው ላይ እንደሌሉ ሰምቷል።

ሲስተር መስከረም ይኽ መረጃ እስከተዘጋጀበት ጊዜ ከሥራ እረፍት እንዲያደርጉ እንጂ ዝውውርም ሆነ እድገት እንዳልተሰጣቸው ለማረጋገጥ ችለናል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከደመወዝ ጥያቄው ጋር በተገናኘ እንዲሁም በዚህ መረጃ ላይ ለቀረቡት ቅሬታዎች የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ሃላፊዎችን ለማናገር ያደረግው ጥረት ባለመሳካቱ ምላሻቸውን ማካተት ሳይቻል ቀርቷል።

በጉዳዩ ላይ ቢሮውም ሆነ ማንኛውም አካል ምላሽ እና ማብራሪያ ለመስጠት ፈቃደኛ ከሆነ ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኑን ይገልጻል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😭911😡166128💔33🤔23😢20🥰10🕊10👏8🙏8😱5
" ከ52 ሽህ በላይ ህዝብ ለውሃ ጥም ተጋልጧል፣ በዙሪያዋ የሚገኙ እንስሳቶች የሚጠጡት ውሃ አጥተዋል " - የፍላቂት ገረገራ ከተማ

በሰሜን ወሎ ዞን ፍላቂት ገረገራ ከተማ እና በዙሪያዋ የሚኖሩ ከ52 ሺህ በላይ ህዝቦች እና እንስሳቶች በውሃ ጥም ለከፋ ችግር መጋለጣቸውን የከተማዋ ከንቲባ ጽህፈት ቤት  ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የፍላቂት ገረገራ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አንደበት ተስፋዬ እመ ምዑዝ የውሃ ፕሮጀክት በብልሽት ምክንያት ከ5 ዓመት በላይ ሲሰጥ የነበረውን የንጹህ መጠጥ ውሃ አገልግሎት በመቋረጡ የከተማዋ ህዝብ በውሃ ችግር ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ከንቲባው በዝርዝር ምን አሉ ?

" ንጹህ መጠጥ ውሀ ለከተማዋ ከ9 ኪ.ሜ በላይ ተጉዞ ነው አገልግሎት ይሰጥ የነበረው፣ አሁን ግን ፕሮጀክቱ የፓምፕ እና የመሥመር ችግር ገጥሞት ከተቋረጠ 20 ቀን ሆኖታል።

ፕሮጀክቱን የገነባው አውስኮር ነው፣ ግንባታው ሳይጠናቀቅ የሰሜኑ ጦርነት ተካሄደ፣ ከዛም በኋላ ሙሉ ጥገና ሳይደረግለት በመቅረቱ ችግሮቹ ሲደራረቡበት ጉድጓዱ በርሃ ላይ ያለ በመሆኑ ፓምፑ ችግር ገጥሞታል።

የከተማው ህዝብ ርቀት ቦታ በመጓዝ የጉድጓድ ውሃ እንዲጠቀም ተገዷል፣ በከተማው ውስጥ በግል፣በመንግስትና በረጂ ድርጅቶች የሚገነቡ ፕሮጀክቶች ግንባታቸው ለጊዜው ተቋርጧል።

በንግድ ዘርፍ የተሰማሩ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ሆቴሎች፣ሬስቱራንትና ግሮሰሪ ቤቶች እና  ሻይ ቤቶች  የተሟላ አገልግሎት ለመስጠት ተቸግረዋል።

የክልሉ ውሃ ቢሮ መጥቶ ችግሩን አይቶ ጥናት አካሂዶ ከሄደ በኋላ በጉድጓዱ አካባቢ ሌላ የውሃ ጉድጓድ ስላለ ከእሱ ጋር ማገናኘት እና አዲስ ፓምፕ መቀየር የሚያስችል ሁለት ጊዜያዊ መፍትሄዎችን በማስቀመጥ ችግሩን ለመቅረፍ እየተረባረብን ነው።

ከዚህ በፊት አገልግሎት የምንሰጥበት የእመምዑዝ ፕሮጀክት በየወሩ ከ300 ሺህ እስከ 400 ሺህ ብር ለኤሌክትሪክ አገልግሎት እንከፍላለን፣ ለዚህ ደግሞ ማህበረሰቡ የሚከፍለው ብር አይበቃም፣ ይህም ሌላ ችግር ነው። " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸው የፍላቂት ገረገራ ከተማ ነዋሪዎች የንፁህ መጠጥ ውሃ አገልግሎቱ ከተቋረጠ ከአንድ ወር በላይ እንደሆነው በከተማዋ ብቻ ሳይሆን በዙሪያዋ ባሉ የገጠር ቀበሌዎችም እንደተቋረጠ ገልጸዋል።

አሁን ላይ በአስከፊ ችግር ላይ እንደሚገኙ ተናግተዋል።

የከተማዋ ከንቲባ አቶ አንደበት ተስፋዬ ከተማዋ በርሃማ በመሆኗ የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር ከባድ ነው ያሉ ሲሆን ለችግሩ ዘላቂ የሆነ መፍትሄ ለማምጣት ከክልሉ ውሃ ቢሮ እና ድርጅቶች ጋር በመነጋገር እየተሰሩ መሆናቸውን አመላክተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
676😭341💔50😡31🙏28🕊26😢19👏5
" ህክምናውን ለማግኘት በተስፋ ሲጠባበቁ ለነበሩ 88 ህፃናት ህክምና መስጠት ተችሏል " - የኢትዮጲያ የልብ ሕሙማን ሕጻናት መርጃ

የኢትዮጲያ የልብ ሕሙማን ሕጻናት መርጃ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ በ6 ቀናት ለ88 የልብ ሕሙማን ሕፃናት የልብ ሕክምና መስጠቱን ገልጿል።

ከኪንግ ሰልማንሁማኒተሪያን ኤይድ ኤንድ ሪሊፍሴንተር ( KSrelief) በተሰጠው በዚህ የህክምና ተልዕኮ ከማዕከሉ የመጡ 30 የህክምና ባለሙያዎች ከማዕከሉ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

የህክምና ቡድኑ ከማዕከሉ ባለሞያዎቾ ጋር በመተባበር ፦

- ለ24 ህፃናት የልብ ቀዶ ህክምና፤

- ለ64 ህፃናት ደግሞ በደም ስር በኩል የሚሰጥ የልብ ህክምና ወይም (cathertarazation) ህክምና መስጠት ችሏል።

በዚህም፥ በአስቸጋሪ ሁኔታ ለነበሩ እና ህክምናውን ለማግኘት በተስፋ ሲጠባበቁ የነበሩ አጠቃላይ 88 ህፃናት ህክምና ማግኘት ችለዋል።

ሳልማን ሁማኒተሪያን ኤይድ ኤንድ ሪሊፍ ሴንተር የህክምና ቡድን የፈፀመው የህክምና አገልግሎት በብር ሲተመን ከ39 አስከ 51 ሚልየን የሚገመት እንደሆነ የኢትዮጲያ የልብ ሕሙማን ሕጻናት መርጃ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ ጠቅሷል።

ተቋሙ ከሳኡዲ አረቢያድረስ በመምጣት ላበረከተው ትልቅ ኣስተዋፅኦም ምስጋና ያቀረበ ሲሆን አጋርነታቸውን በማስቀጠል በልብ ሕመም ከሚሰቃዩ ሕፃናት ጎን እንዲቆሙ ጥሪ አቅርቧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
1.91K👏197🙏137😡28🥰18🕊11😱7😭7🤔4😢3💔3