#ችሎት
⚫️ “ እኔን አጅባችሁ ውሰዱኝና ቤቱን ላሳያችሁ ” - አቶ ክርስቲያን ታደለ
🔴 “ ከአሁን ቀደምም በስም ማጥፋት ወንጀል ፍርድ ቤት ከስሸው ተቀቷል። ፖሊስ ቋሚ አድራሻ ቢኖረውም በተደጋጋሚ ሄዶ እያየ ሰላምታ እየሰጠው ነው የሚመለሰው ” - አቶ ዮሐንስ ቧያለው
የእነ አቶ ክርስቲያን ታደለ እና አቶ ዮሐንስ ቧያሌውን ጉዳይ የሚከታተሉ የቅርብ ሰዎች፣ “የመንግስት አክቲቪስት” ሲሉ የጠሯቸውና “እነ ክርስቲያን ወንጀለኛ ናቸው” ያሉትን ግለሰብ ፌደራል ፓሊስ ማግኘት እንዳልቻለ ለፍርድ ቤት መግለጹን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ።
በዚህም፣ አቶ ስዩም ተሾመ የተባሉት ግለሰብ በቻናላቸው እነ አቶ ዮሐንስን ወንጀለኞች እንደሆኑ በመናገራቸው፣ እነ አቶ ዮሐንስም ክሰዋቸው ስለነበር ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ታዞ የነበረ ቢሆንም፣ ፌደራል ፓሊስ አቶ ስዩም ተሾመን ማግኘት አለመቻሉን ለፍርድ ቤት መግለጹን ነው ያስረዱት።
የእነ አቶ ዮሐንስ እና አቶ ክርስቲያን የቅርብ ሰዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ?
“ አቶ ዮሃንስ ቧያሌው እና ክርስቲያን ታደለ በከፍተኛው ፍርድ ቤት ተከሰው ጉዳያቸው በመታዬት እያለ አቶ ስዩም ተሾመ መጋቢት 11/2017 ዓ/ም ባስተላለፉት ፕሮግራም ከተከሰሱበት ጉዳይ ጋር በተያያዘ ‘የአማራን ወጣት አስፈጅተዋል፣ ድሽቃ መሣሪያ መግዣ ጠይቀዋል’ ብለው እንደነበር አስታውሰዋል።
በዚህም፣ “በፍትህ ሂደቱ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ የሚያሳድር፣ ሕግን የተላለፈ ፕሮግራም ስላቀረቡ፣ የፌደራል ፖሊስ ለዛሬ መጥሪያ አድርሶት ችሎት እንዲያቀርበው ቢታዘዝም፣ ‘የስዩም ተሾመ አድራሻው ስላልተገለጸልኝ ላቀርበው አልቻልኩም’ ብሎ ምላሽ ሰጥቷል ” ብለዋል።
አቶ ዮሐንስ ቧያሌው በዚሁ ጉዳይ ዛሬ ምን አሉ ?
“ ከአሁን ቀደምም በስም ማጥፋት ወንጀል ፍርድ ቤት ከስሸው ተቀቷል። ፖሊስ ቋሚ አድራሻ ቢኖረውም በተደጋጋሚ ሄዶ እያየ ሰላምታ እየሰጠው ነው የሚመለሰው። ትምህርት ሳያገኝ በመቅረቱ ነው አሁንም ተመሳሳይ ድርጊት የፈጸመው።
መንግስት ቤት የሰጣቸው፣ ደሞዝ የሚከፍላቸው እና መኪና የተሰጣቸው የመንግስት አክቲቪስት ናቸው። አማራ ሲሆን የትም ይገኛል። ደብል ስታንዳርድ ነው። የፌደራል ፖሊስ የሰጠው መልስ ለእኛ አሳማኝ አይደለም ” ብለዋል።
አቶ ክርስቲያን ታደለ በዚሁ ጉዳይ ምን አሉ ?
“ ይሄ ‘ወስፌ ሲለግም ቂቤ አይወጋም’ የሚለው አባባል እውነት መሆኑን ያሳየ ነው። አቶ ስዩም ማለት የኢትዮጵያ መንግስት ጠባቂ ፖሊስ የመደበለት የመንግስት ተከፋይ ሃሜተኛ ነው።
እኔን አጅባችሁ ውሰዱኝና ቤቱን ላሳያችሁ። የመንግስት ሹመኛን የሚጠብቀው የፌደራል ፖሊስ አካል ነው።
እኛን የህዝብ እንደራሴዎችን ከቤተሰባችን ፊት ደብድቦና አዋርዶ ለማምጣት ያልተቸገረው ፌዴራል ፖሊስ፣ ላገኛቸው አልቻልኩም ማለቱ ስላቅ ነው። እውነቱን ንገረኝ ካላችሁኝ አቶ ስዩም ያልታሰረው አማራ ነኝ ስላላለ ነው ” ሲሉ ለፍርድ ቤቱ ገልጸዋል ተብሏል።
በመጨረሻም፣ “ የተከሳሾች ጠበቆች በደንበኞቻቸው ላይ የተላለፈው ፕሮግራም ሕግን የተላለፈ በመሆኑ ፖሊስ ያለምንም ምክንያት አቶ ስዩምን እንዲያቀርብ ይደረግልን ” ማለታቸውን የቅርብ ሰዎቻቸው ተናግረዋል።
“ ፍርድ ቤቱም በድጋሚ የፌደራል ፖሊስ ስዩም ተሾመን እንዲያቀርባቸው ለሚያዝያ 7 ቀን 2017 ዓ/ም ቀጠሮ ሰጥቷል ” ብለዋል።
N.B፦ ፌደራል ፓሊስ ፍርድ ቤት እንዲያቀርባቸው ተብለው ነበር የተባሉት አቶ ስዩም ተሾመ፣ ከሳምንት በፊት ባሳራጩት ዩቱዩብ ቻነል ስለነ አቶ ዮሐንስ ቧያሌው ሲናገሩ፣ “ቧያሌው ተንኮለኛ ነው። ከኔ በላይ ማን ምስክር አለ ያረገውን፤ እሰይ ቧያሌው ታሰረ ብዬ ስላልፎከርኩ ነው? መከራዬን አይደል ያበላኝ እሱ ምን ብዬ ስላልኩት ፋኖ ትጥቅ ይፍታ ' አይፈታም' ሲል የአማራን ህዝብ ታስበላላችሁ ሆን ብላችሁ ይሄ ሴራ ነው ስላልኳቸው ነው ይሄ ችግር የተፈጠረው ፤ የተለየ ወንጀል ሰርቼ አይደለም ፤ ገዱም እሱም ጠምደው መከራዬን ሲያበሉኝ የነበረው ፋኖ ትጥቅ አይፈታም ሲሉ ይሄ የድንቁርና ሃሳብ የአማራን ህዝብ ከፌዴራል መንግሥት ጋር ያጋጫል ፣ የማይሆን ቅርቃር ውስጥ ያስገባዋል፣ የአማራን ህዝብ ታስበላላችሁ፣ ወጣቱን ታስፈጃላችሁ እንዳልኩ ወጣት አስፈጅተዋል። እነዚህ ሰዎች ከዛ አልፈው ታጥቀው ' መንግሥት እንግለብጣልን ' ሲሉ መንግሥት ገልብጦ እስር ቤት ከቷቸዋል ስራቸው ያውጣቸው ” ሲሉ ተደምጠዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia

❤419😡136😭76🙏43🕊33😢32👏22🤔19😱8🥰4