TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Earthquake ትላንት ለሊት 9:52 ላይ በርካቶችን ከተኙበት የቀሰቀሰው በሬክተር ስኬል 5.8 ከተለካው የመሬት መንቀጥቀጥ በኃላ በሬክተር ስኬል 4.4 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ እንደነበር መረጃ መለዋወጣችን ይታወሳል። ዛሬ ደግሞ በሬክተር ስኬል ፦ ➡️ 4.7 ➡️ 4.6 ➡️ በድጋሚ 4.7 ➡️ በድጋሚ 4.6 ➡️ 4.9 የተለኩ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶች ተመዝግበዋል። ሁሉም…
🔈 #የሰራተኞችድምጽ #ከሰም

" ሰራተኞቹ ከስራ የተሰናበቱበት መንገድ ከህግ ውጭ በመሆኑ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ለመውሰድ እንቅስቃሴ ተጀምሯል " - የሰራተኞች ማህበር ሊቀ መንበር

በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት ጉዳት የደረሰበት የከሰም ስኳር ፋብሪካ ከ1 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰራተኞቹን የ2 ወር ማስጠንቀቂያ በመስጠት የሥራ ውላቸው እንዲቋረጥ ማድረጉ ቅሬታ አስነስቷል።

ስሜ እንዳይጠቀስ ያሉን አንድ ሰራተኛ በአሁኑ ሰዓት ሰራተኞቹ በመጠለያ ጣቢያና ከዘመድ ጋር ተጠግተው እንደሚገኙ ገልጸው ለሁለት ወራት ያህል ደመወዝ ባለመከፈሉ በከፋ ችግር ውስጥ መውደቃቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል።

የከሰም ስኳር ፈብሪካ የሰራተኞች ማኅበር ሊቀ መንበር አቶ ጌታሁን አርፊጮ በበኩላቸው ፈብሪካው ሰራተኞችን ከስራ ያሰናበተበት መንገድ ከህግ አግባብ ውጭ በመሆኑ ጉዳዩን ወደ ፍ/ቤት ለመውሰድ እንቅስቃሴ መጀመሩን ገልጸዋል።

የከሰም ስኳር ፈብሪካ የሰራተኞች ማኅበር ሊቀ መንበር አቶ ጌታሁን በዝርዝር ምን አሉ ?

" ፋብሪካው ሰራተኞችን ሲያሰናብት የሁለት ወር ማስጠንቀቂያ ማለትም ሚያዚያ 10/2017 ዓ.ም የሚያበቃ ውል በመስጠት ነው።

ይህ ደግሞ ትክክል አይደለም በመጀመሪያ ሰራተኞችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ከመበተን አማራጮችን መመልከት ነበረበት።

በአማራጭነትም ወደ ሌሎች መስሪያ ቤቶች አዘዋውሮ ማሰራት ወይም እዛው ግቢ ውስጥ ምርት ሊሰጡ የሚችሉ ሰብሎችን እያመረቱ  እንዲቆዩ ማድረግ ይችል ነበር።

ፋብሪካው ለወጭ ቅነሳ ሲል የሰራተኞችን ጥቅም አሳጥቷል መብትም ጥሷል። ሰራተኞቹ በሁለት ወር የማስጠንቀቂያ ጊዜ ከሰጠ በኃላ 1 ወር ከ14 ቀን ወደ ኃላ ተመልሰው የዓመት እረፍት እንዲሞሉ አስገድዷቸዋል።

ይህም ትልቅ የመብት ጥሰት ነው። በዚህ ወቅት ስራ ላይ ነበሩ ደሞዝም በልተውበታል  ይህንን አናደርግም ያሉ ሰራተኞች በቅርብ አለቆቻቸው በግዳጅ የአመት እረፍት እንዲሞሉ ተደርገዋል።

ይህ የሆነበት ምክንያትም ሰራተኛው የዓመት እረፍቱን በገንዘብ እንዳይጠይቅ ለማድረግ ታስቦ ነው።

ሴት ሰራተኞችን በተመለከተ በአሰሪ ሰራተኛ አዋጅና በህብረት ስምምነቱ መሰረት ነፍሰጡር በሆኑበት ሰዓትና ወልደው አራት ወር እስኪሞላቸው ድረስ ከስራ አይቀነሱም ይላል ይህ ህግ ግን ተጥሷል።

ማስጠንቀቂያ አሰጣጡም ህግን የተከተለ አይደለም። በአሰሪና ሰራተኛ አዋጁ መሰረት አንድ ዓመት ያገለገለ የ 1 ወር ማስጠንቀቂያ ይኖረዋል።

እስከ 9 አመት ላገለገለ 2 ወር  ከ9 አመት በላይ ላገለገል 3 ወር የማስጠንቀቂያ  ይሰጠው ነበር ፋብሪካው ግን ይህንን አላደረገም።

ፋብሪካው የሰራተኞችን ቅነሳ ሲሰራ ከሰራተኛ ማኅበሩ ጋር መነጋገር ሲገባው ብቻውን ወስኖ ሰራተኞቹን አሰናብቷል፤ ይህንን የመብት ጥሰት በመያዝ ወደ ህግ ለመሄድ እንቅስቃሴ ተጀምሯል "
ብለዋል።

ሊቀመንበሩ እነዚህንና ሌሎች ጥያቄዎችን በመያዝ ለአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር ቢሮ ፤ ለኢትዮጵያ ኢንቭስትመንት ሆልዲንግ፤ ለከሰም ስኳር ፈብሪካ አመራር ቦርድ ጥያቄ አቅርበው እንደነበር ነገር ግን ምላሽ የሚሰጣቸው አካል አንዳላገኙ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም የከሰም ስኳር ፋብሪካ ስራ አስኪያጅን አቶ አሊ ሁሴን ለማግኘት ያደረገው ጥረት ስልኩ ባለማንሳታቸው አስተያየታቸውን ማካተት ለጊዜው አልቻለም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በተቋሙ በኩል ምላሽ የሚሰጥ ከሆነ ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኑን ይገልጻል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
177💔45😢19🕊19😡19😭15🤔7🥰5