TIKVAH-ETHIOPIA
#ፋይዳ #NationalID " ከፍርድ ቤት እና ከብሔራዊ ደኅንነት ጥያቄው ከዛ እስካልመጣ [የግል መረጃ] ለመንግስት የሥራ አስፈጻሚ አይሰጥም " - አቶ ዮዳሄ አርአያሥላሴ ኢትዮጵያ የዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራምን በይፋ ካስተዋወቀችበት ጀምሮ እስከ አሁን 12 ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎች ተመዝግበዋል፤ እስካሁንም ይህንን አገልግሎት ከ50 በላይ ከሆኑ አገልግሎቶች ጋር የማስተሳሰር ሥራም ተሰርቷል። ይህ ፕሮጀክት…
#ፋይዳ #NationalID
" የትምህርት እና የጤና መረጃን በፋይዳ ለማረጋገጥ የሚያስችል የዋሌት ሥርዓት እየሰራን ነው " - ራሄል አብርሃም የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ምክትል አስተባባሪ
° " በምዝገባ ሥርዓቱ ውስጥ የግል ተቋማት በቅርቡ ይቀላቀላሉ ! "
ስለ ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች በተሰበሰቡ ጥያቄዎች ላይ የተቋሙ ምክትል አስተባባሪ ራሄል ምላሽ ሰጥተዋል። በዋናነትም ከትግበራና አፈጻጸም ላይ ተያይዞ ያሉ ጥያቄዎች ቀርበዋል።
ምክትል አስተባባሪዋ፥ በዚህ ወቅት ለቀረቡት ጥያቄዎች ምላሽ በሰጡበት ወቅት እንደገለጹት በቀጣዮቹ አምስት ወራት ወደ 30 ሚሊዮን ዜጎችን ለመመዝገብ መታቀዱን ጠቁመዋል።
ለዚህም አሁን ላይ በአጋርነት ከሚሰሩት ኢትዮ ፖስት እና ኢትዮ ቴሌኮም በተጨማሪ፥ የግል ተቋማትን ወደ ምዝገባ ሥርዓቱ ለማስገባት ጨረታ መውጣቱን ገልጸው፤ ለዚሁ የሚያስፈልጉ የቁሳቁሶች ግዢም በሂደት ላይ መሆኑን ተናግረዋል።
የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ በቅርቡ ዜጎች የተለያዩ አገልግሎት የሚያገኙበትን የራሱን የሞባይል መተግበሪያ በ Android እንዲሁም IOS አስተዋውቋል። እንደ ም/አስተባባሪዋ ከሆነ በቅርቡ የዋሌት ሥርዓትም እንደሚዘረጋ ጠቁመዋል።
የአዲሱ የፋይዳ የዋሌት ሥርዓት ምንድን ነው ?
አዲሱ የዋሌት ሥርዓት "የትምህርት እና የጤና መረጃህን ከፋይዳ ጋር በማገናኘትና በማረጋገጥ በስልክህ ይዘህ እንድትንቀሳቀስ ያስችልኃል" ሲሉ ገልጸዋል።
"ስኮላርሺፕ የሚጠቀሙ ተማሪዎች አንድን የትምህርት ዶክመንት ለማረጋገጥ በተማሩበት ትምህርት ቤት ተገኝተው በመኃተም ወይም ትምህርት ቤታቸው ለሚያመለክቱበት ት/ቤት ማስላክ ነበር። ይህንን አላስፈላጊ መጉላላት የሚያስቀር ዋሌት እየሰራን ነው።" ራሄል አብርሃም
የዋሌት ሥርዓቱ አላስፈላጊ መረጃ እንዳይሰጥ ጭምር ያግዛል ያሉት ምክትል አስተባባሪዋ "አላስፈላጊ መረጃም እንዳይሰጥ ይጠቅማል፤ እድሜህን ብቻ የሚፈልግ ተቋም እድሜህን ብቻ በፋይዳ በኩል Verifiable Credentials (VCs) በመፍጠር ለዛ ተቋም መላክ ትችላለህ፥ ያም ተቋም ያንን አይቶ አገልግሎት የሚሰጥበትን እየሰራን ነው" ሲሉ ገልጸዋል።
"ፋይዳ ላይ ያለው ፎቶዬ ተበላሽቷል እንዴት መቀየር እችላለሁ?"
ይህ ጥያቄ ከበርካታ ቤተሰቦቻችን የተነሳ ጥያቄ ሆኖ አግኝተነዋል። ይህንንም አስመልክቶ የፋይዳ መታወቂያ ላይ ያሉ መረጃዎችን እንዴት መቀየር እንችላለን ብለን ለምክትል አስተባባሪዋ ጥያቄውን አቅርበንላቸዋል።
በምዝገባ ወቅት የሚፈጠሩ የቃላት ግድፈት፤ የዶክመንት አለመገናኘት እና መሰል ስህተቶች በፋይዳ ዌብሳይት ላይ በመግባት እና ማስተካከያ በመጠየቅ እንዲስተካከል የሚያስችል አሰራር አሁን ላይ መኖሩን ገልጸዋል።
ሆኖም የፎቶ እንዲሁም ማንነት ላይ ለውጥ የሚያመጡ የባዮሜትሪክ መረጃዎች ለውጥ በተመለከተ የህግ ማዕቀፎች መዘጋጀታቸውንና አሁን ላይ በምዝገባ ላይ ላሉ አጋር ተቋማት የሥልጠና ሥራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
የፎቶ ቅያሬን በተመለከተም በአጭር ጊዜ ውስጥ ዜጎች በምዝገባ ተቋማት በመሄድ ፎቶ መቀየር እንዲችሉ የሚያስችላቸውን ሥርዓት በመዘርጋት ላይ እንገኛለን ብለዋል።
- የፋይዳ ካርድ በድጋሜ ማሳተም ይቻላል?
- የጣትና የአይን አሻራ የሌላቸው ዜጎች መመዝገብ ይችላሉ ?
- የጥሪ ማዕከላችሁ ይሰራል ? እና መሰል ከቲክቫህ ቤተሰቦች የተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።
📱 የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ምክትል አስተባባሪ ራሄል አብርሃም ለቀረቡት ጥያቄዎች የተሰጡትን ምላሾች ይመልከቱ https://youtu.be/7cYEVy3sDd8
@tikvahethiopia

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😡283❤125👏115😭20🤔18🙏14🕊10😢9🥰8😱6
TIKVAH-ETHIOPIA
#ፓስፖርት : ፖስፖርት ለማውጣት ፋይዳ መታወቂያ መያዝ የግዴታ እንደሚያስፈልግ ተገልጿል። ከሰኔ 1/2017 ጀምሮ የፋይዳ መታወቂያ ለፓስፖርት አገልግሎት ከሚስፈልጉ ዋና ሰነዶች ውስጥ አንዱ ይሆናል። ከሰኔ 1 በኃላ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የፓስፖርት አገልግሎት ጥያቄ አቅርበው በመጠባበቅ ላይ ያሉ ግለሰቦች ፓስፖርት ለመውሰድ ሲመጡ የፋይዳ መታወቂያ ፦ - ልዩ ቁጥር መያዝ፣ - QR ኮዱን በወረቀት…
#ፋይዳ #NationalID
ከትላንት በስቲያ ሰኞ ጀምሮ ፋይዳ መታወቂያ ለፓስፖርት አገልግሎት አስፈላጊ ከሆኑ ሰነዶች መካከል አንዱ ሆኗል።
ፓስፖርት ለማውጣት ፋይዳ መያዝ የግድ ያስፈልጋል።
ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ለመመዝገብ በአቅራቢያ በሚገኝ የምዝገባ ጣቢያ id.gov.et/locations በመሄድና በመመዝገብ የታተመ QR ኮድ ወይም በስልክ ዲጂታል ኮፒ በመያዝ አገልግሎት ማግኘት ይቻላል።
የብሔራዊ መታወቂያ አገልግሎት ፅ/ቤት " ወደ ኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ፅ/ቤት ከመሄዳችሁ በፊት በአቅራቢያችሁ ባሉ ማዕከላት ተመዝግባችሁ ኮዱን ማሳተም እና መያዝ ይኖርባችሗል " ብሏል።
" QR ኮድን ከ " Fayda ID " ሞባይል መተግበሪያ ፣ ከቴሌብር ሱፐር አፕ፣ እንዲሁም ሲቢኢ ብር ሞባይል መተግበሪያ ላይ በማውረድ እና በወረቀት በማሳተም መያዝ ይቻላል " ሲል ገልጿል።
የፋይዳ ቁጥር ያልደረሰው ወይም ከጠፋበት በተመዘገበበት ስልክ *9779# በመደወል ወይም የፋይዳ መተግበሪያ " Fayda ID " በመጠቀም በድጋሚ ማስላክ እንደሚችል ተመላክቷል።
በምዝገባ ወቅት የመረጃ ስህተት ካጋጠመም id.gov.et/update ወይም በ "Fayda ID" ፋይዳ ሞባይል መተግበሪያ በቀላሉ ማስተካከል ይቻላል።
#ፋይዳለኢትዮጵያ

❤744😡162🥰22😭21🙏19🕊13👏5🤔4😱3😢2