TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የትግራይ ማእከላይ ዞን ፍርድ ቤት የአክሱም ከተማ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ከነሂጃባቸው እንዲማሩ ወሰነ። የወረዳ ፍርድ ቤት በትግራይ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ላይ ያስቀመጠው የገንዘብ መቀጮም እንዲቀር ወስኗል። የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት መጋቢት 30/2017 ዓ.ም በይፋዊ የማህበራዊ የትስስር ገፁ እንዳሰፈረው ፤ ከአሁን በፊት በአክሱም ከተማ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች…
#Axum
" የአክሱም ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ሂጃብ በመልበሳቸው ምክንያት የ12ኛ ክፍል ፈተናን እንዳይወስዱ ተደርገዋል " - የሙስሊም ሴት ተማሪዎችን ጉዳይ የሚከታተሉ አካላት
➡️ " ፈተና ማእከል ደርሳ ሂጃብ በመልበስዋ ምክንያት የተባረረች እንዲት ሙስሊም ተማሪ የለችም ፤ የፈጠራ ወሬና ጥላሸት መቀባት ይቁም " - የትምህርት ቢሮ ሃላፊ
የአክሱም ከተማ ሴት ተማሪዎች የሂጃብ መልበስ ክልከላ ጋር ተያይዞ የተነሳው ውዝግብ ወራትን አስቆጥሯል።
ዛሬ በአገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረው የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተና ሲጀመር የአክሱም ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ጉዳይ ተነስቷል።
የሙስሊም ሴት ተማሪዎችን ጉዳይ የሚከታተሉ አካላት ፥ " የአክሱም ከተማ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች በሂጃብ ክልከላ ምክንያት የ12ኛ ክፍል ፈተናን እንዳይወስዱ ተደርገዋል " በማለት አስተያየታቸውን በማህበራዊ የትስስር ገፆች አሰራጭተዋል።
" ሂጃብ ከመልበስ ጋር ተያይዞ እንዲት ሙስሊም ተማሪ ከፈተና ማእከል የተባረረች የለችም " በማለት ለተሰራጩት ፅሁፎችና አስተያየቶች ምላሽ የሰጡት የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ኪሮስ ጉዕሽ (ዶ/ር) " ፈተና ለመውሰድ የተመዘገቡት 24 ሴት ተማሪዎች በራሳቸው ፍላጎት ሳይመጡ ቀርተዋል " ብለዋል።
" ሴት ሙስሊም ተማሪዎቹ የመፈተን ፍላጎት ካላቸው ሀሙስ ሰኔ 26/2017 ዓ.ም በሚጀመረው ሁለተኛ ዙር ፈተና መፈተን ይችላሉ ፤ ከዚህ ውጪ ተማሪዎቹ እንዳይፈተኑ በመከልከል ሆን ተብሎ የሚፈጠረው የማጠልሽት ተግባርና ውሸት ለህዝብና አገር አይጠቅምም " በማለት አክለዋል።
ዛሬ በተጀመረው የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና 36 ሺህ ተማሪዎች ፈተናውን መውሰድ ጀምረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia

4❤1.66K😡668💔205😭141👏105🕊60🤔55🙏30🥰28😢25😱24
#Axum
የአክሱም ከተማ ፖሊስ በከተማው ክንደያ በተባለ ቀበሌ ሁለት ተጠርጣሪዎች አደገኛ ኬሚካል በመጠቀም የወርቅ ማጣራት ተግባር ሲያከናውኑ በቁጥጥር ስር እንዳዋላቸው አሳውቋል።
ፖሊስ ከህብረተሰብ በደረሰው ጥቆማ የፍ/ቤት የፍተሻ ትእዛዝ በመያዝ የተለያዩ የፍትህ አካላት ፣ የአገር ሽማግሌዎችና የጤና ባለሙያዎች በማሳተፍ ነው ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ያዋላቸው፡፡
የከተማዋ አቃቤ ህግ የህበረተሰብ የጤና ጠንቅ የሆነውን አደገኛ ኬሚካል በመጠቀም ህገወጥ ተግባር ሲፈፅሙ የተገኙት ተጠርጣሪዎቹ በአጭር ጊዜ አስተማሪ ቅጣት እንዲያገኙ ከባለ ድርሻ አካላት በመሆን ይሰራል ብሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
Photo credit - Tigrai Television

❤400👏47🤔18🙏12😡12🕊6😭6😱1