TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63K photos
1.61K videos
216 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኮሬ

🚨" ማንም ከህግ በላይ መሆን አይችልም ህገ መንግስት ይከበር "- የታጣቂዎች ግድያ ከዘጠኝ አመታት በላይ ያማረራቸው ዞን ነዋሪዎች

➡️ " መንግስት ይህን ሕዝብ ስለማወቁ እጠራጠራለሁ " - የኮሬ ዞን የቀድሞ አመራር

ሰሞኑን የንጹሐን ሕይወት በታጠቁ አካላት ጥቃት ማለፉን የኮሬ ዞን ጎርካ ወረዳ የጀሎ ቀበሌ ነዋሪዎች እንደተረዳ የኮሬ ዞን ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስታውቋል።

ዞኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መልዕክት ምን አለ ?

" በአርሶ አደር ሹኩር ዩሱፍና በወጣት ቡጥሳ ጉይባ ላይ በደረሰው አሳዛኝ የሞት አደጋ የአካባቢ ማህበረሰብ ጥልቅ ሀዘኑን ገልጿል። 

አርሶ አደሩ የጀሎ ቀበሌ ነዋሪ ሲሆኑ፣ ቅዳሜ የካቲት 29 ቀን 2017 ዓ/ም ከብቶቹን ውሃ በማጠጣት ላይ ሳሉ በምዕራብ ጉጂ ዞን ጋላና ወረዳ የሚንቀሳቀሱ የጋላና ፎሌዎች (ታጣቂዎች) ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣
ኮሬ ዞን ጎርካ ወረዳ ጄሎ ቀበሌ ዘልቀው በመግባት ጥቃት ፈጽመዋል። 

ከጀሎ ቀበሌ ከማሳቸው ተፈናቅለው ወደ ኬሌ ቀበሌ አስተዳደር ተጠግቶ የሚኖሩ ነገር ግን ቀን በቀን ወደ ቀበሌያቸው ከብቶቻቸውን ውሃ ለማጠጣት ሲሄዱ ከነበሩ ሰዎች መካከል አቶ ሽኩር ላይ ጥቃቱ ደርሷል። 

አቶ ሹኩር የኬሌ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ደርሰው በጥቃቱ የደረሰባቸው ጉዳት ከባድ በመሆኑ ለአርባ ምንጭ ሆስፒታል ሪፈር ተደርገው፣ መንገድ ላይ ሕይወታቸው ማለፉን ከቤተሰቦቻቸው ለማረጋገጥ ተችሏል። 

'ከአርሶ አደሩ ግድያ በኋላ 10 ሰዓት ገደማ ቡጥሳ ጉይባ የተባለ ወጣት ለጊዜው ማንነቱ ባልተረጋገጠና የታጠቀ አካል ከባድ የጥይት ምት ደርሶበት ወደ ኬሌ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ተወስዶ ወደ አርባምንጭ ሪፈራል ሆስፒታል ቢባልም መንገድ ላይ ህይወቱ ማለፉን ተከትሎ 'ወጀ' ተመልሷል' የሚል ከቤተሰብ የደረሰልን መረጃ ያመለክታል። 

የአካባቢው ነዋሪዎችም፣ ‘ጥቃት የፈጸመው አካል ማንነት ተረጋገጦ ለህዝብ ይፋ አንዲደረግና በህግ ቁጥጥር ሥር እንዲውል’ ሲሉ ጠይቀዋል። 

‘ማንም ከህግ በላይ መሆን አይችልም፣ ህገ መንግስት ይከበር’ ብለዋል።

ከምዕራብ ጉጂ በሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች በሚፈጸም ወረራ  ከመኖሪያቸውና ከማሳቸው የተፈናቀሉ የጀሎና የዶርባዴ ቀበሌ ነዋሪዎች በአጎራባች ቀበሌዎች ውስጥ ባሉ የላስቲክ ቤቶችና ዛፎች ሥር እየኖሩ ችግሩ ሲያስገድዳቸው ቀን በቀን ወደ ማሳዎቻቸው ሄደው እንጨት እየለቀሙ መንገድ ላይ አውጥተው ይሸጣሉ። 

ከቋሚ ተክሎች ሊበላ የሚችል አንዳች ነገር የለም፤ በጉጂ ታጣቂዎች ሀብቶች ተጨፍጭፈዋል፤ በእሳት ተቃጥሎ ወድሟል። 

ከሐምሌ 16 ቀን 2009 ዓ/ም ጀምሮ የኮሬ ዞን ዋናው የንግድና የሕዝብ ትራንስፖርት መስመር የሆነው የኬሌ ቶሬ ጨለለቅቱ ዲላ መንገድ ተዘግቶ፣ የማህበራዊ፣ ከኢኮኖሚያዊና ፖሊቲካዊ እንቅስቃሴዎች ተቋርጠዋል። 

‘የጄሎና የዶርባዴ ቀበሌ ነዋሪዎች ጨምሮ ከ13 በላይ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው መች ተመለሱ? የምዕራብ ጉጂ አዋሳኝ ቀበሌዎች ለተደጋጋሚ ጥቃት ሰለባ እየሆኑ መች የፌዴራል መንግስት ጠየቀን?’ ሲሉ የኮሬ ዞን ማህበረሰብ ቅሬታ እያሰሙ ይገኛሉ " ብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸው የቀድሞ የኮሬ ዞን አመራር በበኩላቸው፣ " መንግስት በኮሚዩኒኬሽን ሚንስትሩ በኩል፣ 'ኢትዮጵያ ከመቸውም ጊዜ በላይ ሰላሟ የተረጋገጠ ነው' በሚል መግለጫ በሰጡበት ዕለት የኮሬ አርሶ አደሮች መከራ መቀጠሉ ያሳዝነኛል " ብለዋል።

" መንግስት ይህን ሕዝብ ስለማወቁ እጠራጠራለሁ " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ : https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-03-11-2

@tikvahethiopia
😭25463🕊13😁12🙏11😢8🥰5👏5😱3