TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.2K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
🔈 #የነዋሪዎችድምጽ

⚫️ " ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ነው ያለብን መኖር አልቻልንም በሳምንት ሶስት እና አራት ቀን መብራት የለንም " - ቅሬታ አቅራቢ

🔴 " ከክረምት በፊት ችግሩ ይቀረፋል ታገሱ " - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት


በአዲስ አበባ ከተማ ሰሚት ፍርድ ቤት፣ ሰሚት ሳፋሪ፣ ሰሚት ፔፕሲ ፋብሪካ ፣ ፍየል ቤት ፣ ወጂ ሰፈር፣ ሰንራይዝ ሪል ስቴት፣ ፊሊንት ስቶን ሆምስ እና ጎሮ ሚካኤል አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች በአካባቢው በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለው የሃይል መቆራረጥ ከፍተኛ የሆነ ምሬት ውስጥ እንደከተታቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

በአካባቢው የሚገኙ በተለይም የፍሊንት ስቶን ትዊን የጋራ መኖሪያ መንደር ነዋሪዎች " ከህዳር 02/03/17 ዓ/ም ጀምሮ የመብራት አገልግሎት ቀንም ለሊትም ሳናገኝ በችግር ላይ እንገኛለን " ሲሉ ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ምስራቅ አዲስ አበባ ሪጅን በደብዳቤ ጭምር ቢያሳውቁም " መፍትሄ የሚሰጠን አጥተናል " ብለዋል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በበኩሉ በአካባቢው ለሃይል መቆራረጥ መንስኤ የሆነው በመሬት ውስጥ በሚቀበሩ የሃይል መስመሮች ላይ የሚያጋጥም የመሰረት ልማት ጉዳት እና ስርቆት ምክንያት መሆኑን በመግለጽ ደንበኞቹ የሃይል አቅርቦቱ እስኪመለስ በትዕግስት እንዲጠብቁ የሚጠይቅ ጽሁፍ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ላይ አስፍሯል።

ነዋሪዎች በዝርዝር ምን አሉ ?

" ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ነው ያለብን መኖር አልቻልንም በሳምንት ሶስት እና አራት ቀን መብራት የለንም መብራት አይመጣም ከመጣም ለሊት ነው ከዛ ተመልሶ ይጠፋል መኖር ከብዶናል።

ህመምተኞች አሉ ፤ ፍሪጅ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች አሉ ከዚህም በላይ በዚህ ኑሮ ውድነት ምግብ ለመድፋት ተገደናል።

ከህዳር 18 እስከ ታህሳስ 9 ባለው ጊዜ አምስት ጊዜ በተደጋጋሚ በመንገድ ስራ ምክንያት በመሬት ውስጥ ያለ መስመር በኤክስካቫተር እየተመታ ሃይል ተቋርጧል።

መፈጠር አልነበረበትም ቅድመ መከላከል ስራዎች ሊሰሩ ይገባ ነበር ከሆነ በኋላ ግን በተደጋጋሚ መፈጠር አልነበረበትም ተጠያቂነትም ሊኖር ይገባ ነበር።

ከታህሳስ 10 በኋላ ግን አንድ ጊዜ ሲመታ ከ18 ሰዓት እስከ 3 ቀን መብራት ይጠፋ ጀምሯል ከዛ በኋላ መቆራረጡ በከፍተኛ ሁኔታ ባሰ በ24 ሰዓት ጊዜ ውስጥ ለ25 ደቂቃ ብቻ ሃይል የምናገኝበት ጊዜ ሁሉ አለ።

ትልቁ ቆየ ከተባለ 4 ሰዓት ነው ይህም ከእኩለ ለሊት እስከ ንጋት ባለው ጊዜ ውስጥ ነው ሰው ከተኛ በኋላ ለምንም አገልግሎት መዋል በማይችልበት ሰዓት ነው ከሚመጣው።

የመልሶ ግንባታ ስራ ለማከናወን በሚል በወጣው ዝርዝር ውስጥ አካባቢያችን የሃይል አቅርቦት እንደሚቋረጥ የሚገልጸው ከ 3 ሰዓት እስከ 10 ሰዓት ቢሆንም እኛ ከንጋት ጀምሮ እስከ እኩለ ለሊት መብራት አናገኝም።

ችግሩን ማስቆም ሲችሉ ማህበረሰቡ በመሃል እየተቀጣ ነው ልጆች ከትምህርት ቤት መጥተው ማጥናት አልቻሉም ፣በተደጋጋሚ በመጥፋቱም ምክንያት ነዋሪው ለከፍተኛ የኢኮኖሚ ጫና እየተዳረገ ነው " ብለዋል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢ/ር ሺፈራው ተሊላ ምን ምላሽ ሰጡ ?

" ቀን ቀን የፕሮጀክት ስራ አለ በስራው ምክንያት ይቋረጣል ማታ ማታ ይለቁላቸዋል ሙሉ ቀን የማይበራላቸው ብልሽት ሲኖር ነው እንደዛ የሚሆነው ሁሌ አይደለም።

ከሰሚት ጀምሮ እስከ ወረገኑ ድረስ እዛ መስመር ላይ መሰረተ ልማት ስራ እየተሰራ ነው ስራዎች በቅንጅት ነው የሚሰሩት አንዳንዴ ብዙ ስራ ስለሆነ እየተሰራ ያለው ከአቅም በላይ በሆኑ ምክንያቶች ችግሮች ይከሰታሉ።

ለዘለቄታው ለመገልገያ (Utility) የሚሆን ኮሪደር አብሮ እየተሰራ ነው ለተወሰነ ጊዜ ነው የተጠቀሰው አይነት ችግር የሚኖረው በቀጣይ በጣም አስተማማኝ የሆነ መሰረተ ልማት እየተሰራ ነው።

መንገድ በሚሰራበት ጊዜ ከእግረኛና ከአስፋልት መንገድ ጎን የውሃ ፣ የቴሌኮም እና የኤሌክትሪክ መስመር (Utility Corridor) አብሮ እየተገነባ ነው።

ቀደም ሲል የነበረው አካሄድ ብልሽት በሚኖርበት ጊዜ አስባልት ተቆፍሮ ነበር የሚሰራው በአሁኑ አሰራር ደረጃውን በጠበቀ መንገድ ብልሽት ሲኖር መቆፈር እና ማፍረስ ሳያስፈልግ ገብቶ ለመስራት ያስችላል ፣ የመቀየር እና የማሻሻል ስራ ሲያስፈልግ ማሟላት የሚችል የአቅም ማሳደግ ስራ እየተሰራ ነው።

ይህ አይነት ቅንጅት ባለመኖሩ ብዙ ችግሮች ሲከሰቱ ነበር አሁንም የምናየው ችግር የተከሰተው ቀደም ሲል ይህ አይነት ቅንጅት እና የUtility corridor ባለመኖሩ ምክንያት የተከሰተ ነው ።

ይሄንን ችግር ለአንዴ እና ለመጨረሻ ችግሩን ለመፍታት እና ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት እየሰራን ነው።

የተወሰነ ጊዜ መታገስ ነው ለዘመናት የሚያገለግል ስራ ነው የሚሰራው ስራው እስከ 6 ወር ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቅ ነው ከክረምቱ በፊት ያልቃል" ብለዋል።

እስከዛ አሁን ባሉበት አይነት የመብራት ችግር ውስጥ ይቆያሉ ወይ ? ስንል ለዋና ስራ አስፈጻሚው ጥያቄ አንስተናል።

ኢ/ር ሺፈራው ተሊላ

" ሲሪየስ በሆነ ነገር ውስጥ ላይቆዩ ይችላሉ ብዙ ነገር እየተሻሻለ ነው የሚሄደው ብዙ ቁፋሮ አለ ቁፋሮ ካለቀም በኋላ መሰረተ ልማቱ ቦታውን ይይዛል ለስራ ሲባል ሃይል መቆራረጥ ይኖራል ነገር ግን እየተሻሻለ ይሄዳል።

ከመገናኛ ሰሚትም ሲሰራ እንደዚህ አይነት ችግሮች ነበሩ አሁን CMC አካባቢ እንደዚህ አይነት ችግር የለም ከዚህ በኋላ እንደዚህ አይነት ችግሮች አይኖሩም የሁሉም ስራ ያልቃል ከክረምት በፊት ችግሩ ይቀረፋል ታገሱ " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ችግሩን በማቃለል እስከዛ በተሻለ መንገድ ሃይል የሚያገኙበት እድል ይኖራል ወይ ? የሚል ጥያቄም ያነሳንላቸው ሲሆን በምላሻቸውም " እንደዛ እናደርጋለን ከባድ ችግር ስለነበር አንድ ጊዜ ነው እስካሁን ለቀናት በሚባል ደረጃ የተቋረጠው ከዚህ በኋላ እንደዚህ አይነት ነገር እንዳይኖር ጥረት እናደርጋለን " ሲሉ መልሰዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😭339163😡96🕊40🙏22🤔12👏11😱9😢7🥰3
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
🔈 #የነዋሪዎችድምጽ

“ የእሳትና ድንገተኛ አደጋ መጥተው ከድልድዩ ቆመው አይተው ሄዱ ተመልሰው ” - የቦታው ነዋሪ

“ ምናልባት በኛ የማይሰራ ከሆነ ብዬ እንደዛም ገምቼ ነው፡፡ ይነግሩኝ ነበር ከሄዱ አሳውቃለሁ ” - ኮሚሽኑ 

አዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11፣ ቀጠና 2፣ “ወይናምባ ማርያም” የተሰኘ አካባቢ ነዋሪዎች፣ የአካባቢው ወንዝ በአፈር በመዘጋቱ ትላንት የጣለው ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ ንብረታቸው እንደተወሰደና ውጪ እንዳደሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸው ነበር።

በዚህም ነዋሪዎቹ ወንዙ እንዲከፈትላቸው ተማጽነው የነበረ ሲሆን፣ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጉዳዩን ለእሳትና አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን በሰዓቱ አሳውቆ ነበር።

የነዋሪዎቹ ቅሬታ መፍትሄ ተሰጠው ?

የእሳትና አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች መጥተው ነበር ? ስንል የጠየቅናቸው ከነዋሪዎቹ አንዱ፣“ የእሳትና ድንገተኛ አደጋ መጥተው ከድልድዩ ቆመው አይተው ሄዱ ተመልሰው ” ብለዋል። 

“ ‘ሌላ ቀን እንመጣለን ይሄ በኛ መኪና የሚቻል አይደለም’ አሉ። ሌሎች ከእሳትና አደጋ ‘መጥተናል’ ብለው ደግሞ ሰውን መዝግቡ ብለው፤ ግማሹን ራሳቸው መዝግበው፣ ግማሹን 'መዝግባችሁ ወረቀቱን አምጡ’ ብለው ሄዱ” ሲሉም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

“‘ወደ ወንዙ በመኪና ለመግባት በጣም ከባድ ነው፣ ይሄን መጀመሪያ ለምን ወረዳው፤ ቀበሌው አልተከታተሉም?’ አሉ” ብለው፣ የተዘጋው ወንዝ ገና አልተከፈተም ብለዋል።

ሌሎቹ ቅሬታ አቅራቢዎችም፣ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞቹ ደርሰው እንደተመለሱ፣ ነገር ግን ጉዳዩ  መፍትሄ እንዳላገኘ፣ ንብረታቸውን ከወንዙ እየለቀሙ እንደዋሉ ገልጸዋል።

ትላንት በጣለው ዝናብ ከደረሰባቸው የንብረት ውድመት ሳያገግሙ በድጋሚ ዝናብ ከጣለ ሌላ የከፋ አደጋ እንዳይደርስ የሚል ስጋት እንደገባቸው አስረድተዋል።

ኮሚሽኑ ምን አለ ?

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ መጀመሪያ ጉዳዩን ካሳወቀበት ቆይታ በኋላም የነዋሪዎቹ ቅሬታ ከምን ደረሰ? በቦታው ሄዳችሁ? ሲል የኮሚሽኑን የሕዝብ ግንኑነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞን ምላሽ ጠይቋል፡፡

እሳቸውም በምላሻቸው፣ “ለዲስፓይ ሴንተር ስልካቸውን ሰጥቻለሁ፤ ቼክ አድርጉና ደውሉላቸው ብያለሁ፡፡ ምላሹን አልጠየኳቸውም” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

አክለው ፤ “ከተሰማሩ፤ ከሄዱ ችግር የለም፡፡ ምናልባት በኛ የማይሰራ ከሆነ ብዬ እንደዛም ገምቼ ነው፡፡ ይነግሩኝ ነበረ ከሄዱ አሳውቅሃለሁ” ብለው ነበር፡፡

በድጋሚ ከቆይታ በኋላ ስንሞክር ምላሽ አላገኘንም።

አቶ ንጋቱ በከተማዋ ሰምኑን የተከሰተውን የጎርፍ አደጋ በተመለከተ ዛሬ ጠዋት በሰጡን ገለጻ፣ "ኮሚሽን መስሪያ ቤታችን ስሙ እሳት ብሎ ስለሚጀምር እዛ ላይ ብቻ አገልግሎት እንደምንሰጥ መረዳት አለ። ግን ማናቸውም አደጋ ይመለከተናል” ሲሉ አደጋ ሲያጋጥም ህዝቡ ወደ ኮሚሽኑ እንዲደውል አሳስበው ነበር።

(ጉዳዩ የሚመለከታቸውን የከተማውን አካላት ሁሉ የምንጠይቅ ይሆናል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😢26499🙏26🕊19😡17💔8😭8👏5😱2🥰1
🔈#የነዋሪዎችድምጽ

" አምና ቁምሳጥኑን ፣ ቲቪውን ሽጦ እስከ 11 ሺሕ ብር የከፈለ አለ፡፡ ዘንድሮ ተሻሽሎ ወደ 20 ሺሕ ብር መሆኑ ደግሞ ከህዝቡ አቅም በላይ ነው " - ነዋሪዎች

➡️ " ያለደረሰኝ የሚሰበሰብ ገንዘብ የለንም፡፡ ልማት ሲባል መቼም መንግስት ከቅጠል ላይ ዘርፎ የሚሰበስበው ብር የለም " - የሸገር ከተማ ከንቲባ

በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማና ዙሪያው ነዋሪዎች ከሚጠየቁት ከፍተኛ ግብር በተጨማሪ የቡሳ ጎኖፋን ጨምሮ ሌሎች ደረሰኝ እንኳ የማይቆረጥባቸው ክፍያዎች ከኑሮ ውድነቱ ጋር እንዳማሯቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ።

" የግብር ክፍያውን በግለሰብ ወደ 20 ሺሕ ብር አደረሱት፡፡ በየዓመቱ ከ100 ፐርሰንት በላይ እየጨመሩ ህብረተሰቡ በጣም ሰቀቀን ላይ ነው " ሲሉ አማረዋል።

- ለማዘጋጃ ቤት14 ሺሕ 200 ብር፣
- ለቀይ መስቀል 500 ብር፣
- ለቡሳ ጎኖፋ ማኀበር 100 ብር፣
- ለኦሮሚያ ልማት ማኀበር 500 ብር
- ለስፖርት አካውንት 500 ብር፣
- ለጤና መድህን 1310 ብር ክፍያ እየተጠየቁ መሆኑን አመልክተዋል።

" የአፈር ግብር በምን ስሌት ተሰልቶ ነው 14 ሺሕ 200 ብር የሚሆነው? አምና ቁምሳጥኑን፣ ቲቪውን ሽጦ እስከ 11 ሺሕ ብር የከፈለ አለ፡፡ ዘንድሮ ደግሞ ተሻሽሎ 20 ሺሕ ብር በመሆኑ ከህዝቡ አቅም በላይ ነው " ሲሉ መፍትሄ ጠይቀዋል፡፡

" መዋጮው ከህብረተሰቡ አቅም በላይ ነው፡፡ ደረሰኝ የሚሰጠው ለቀይ መስቀል ለማዘጋጃ ቤት ክፍያው ነው፤ ለሌላው ደረሰኝ እንኳ የለውም " ብለው፣ " አምና ለማዘጋጃ ቤት 6 ሺሕ ብር፣ በ2015 ዓ/ም 2400፣ 2500 ብር ነበር የከፈልነው፡፡ 2016 ዓ/ም 6700 ብር ገባ፡፡ ዘንድሮ ወደ 14 ሺሕ 200 ብር ከፍ አለ " ነው ያሉት፡፡

ቅሬታውን ይዘን የሸገር ከተማ ከንቲባ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር) ምላሽ ጠይቀናቸዋል።

" ያለደረሰኝ የሚሰበሰብ ገንዘብ የለንም፡፡ ልማት ሲባል መቼም መንግስት ከቅጠል ላይ ዘርፎ የሚሰበስበው ብር የለም፡፡ ማህበረሰቡ በተለያየ የሚሰሩትን በአንድ ቦታ ለመሰብስብ ካልሆነ በስተቀር የበዛ ክፍያም የለም " ሲሉ መልሰዋል።

" የቡሳ ጎኖፋ ጉዳይ ዓለም የሚሰራው ነው፡፡ በኛ አገር በተለይ በኦሮሚያ ክልል ይሄው ጉዳይ ውጤታማ ሆኖ የተፈጥሮና ተፈጥሯዊ ያልሆኑ ችግሮች በሚከሰቱበት ጊዜ ቡሳ ጎኖፋ የምንለው ሥርዓት ነው ላለፉት ሁለት ሦስት ዓመታት ብዙ ችግር የፈታልን፡፡ ስለዚህ ፈቃደኛ የሆነ ሰው ይህንን ይከፍላል " ነው ያሉት።

ነዋሪዎች በግዴታ ተጠየቅን የሚሉትን የቡሳ ጎኖፋ ክፍያ እርስዎ አስገዳጅነት የለውም ነው የሚሉት ? ስንል የጠየቅናቸው ከንቲባው፣ " ሜምበርሽፕ ነው፡፡ ሰውን መርዳት ምን ችግር አለው ? የተወሰነ ገንዘብ ከገቢህ ሼር ማድረግ የሰውነት ግዴታ ነው " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ከንቲባ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር) አክለው ምን አሉ ?

" ይቺን መክፈል ይህን ያክል ከባድ አይደለም። ባደጉት ሀገራት ሰው 60 በመቶ እየከፈለ ነው ጠንካራ መንግስት ያቋቋመው፤ ከየትም መጥቶ አይደለም እነ አውሮፓ እነ አሜሪካ የተገነቡት፡፡ ስለዚህ እያንዳንዱ ማውጣት ያለበትን ማውጣት አለበት።

ከእያዳንዱ ሰው የሚዋጣው ትንሽ ብር ነው ይሄን ያህል ብዙ አይደለም። ሁሉም ነገር ሥርዓት ያለው ነው፤ ክፍተቶች ካሉ ደግሞ እናያለን።

የኦሮሚያና ልማት ማህበር ክፍያን በተመለከተ የኦሮሚያ ልማት የራሱ ሜምበር አለው፤ የራሱ ሜምበር ይከፍላል፤ አልከፍልም ካለም መብቱ ነው። የማዘጋጃ ቤት ክፍያ ይጨምራል፤ አገልግሎት ላይ ዋጋ ይጨመር ስንል ሰው ለምን ይገረማል ? ድንችና ሽንኩርት ሲጨምር ሰው ዝም ብሎ የለ እንዴ።

መጨመር አለበት ብለን ሪቫይዝ አድርገናል። መንግስት አንድን ከተማ ጠንካራ የሚያደርገው ገቢ ሰብስቦ መስራት ከቻለ ነው። 3 ሚሊዮን ህዝብ ነው ያለኝ፤ ከ3 ሚሊዮን ህዝብ ባለፈው 24 ቢሊዮን ነው የሰበሰብኩት ይሄን 24 ቢሊዮን ምንድን ነው የማደርግበት ?

በዚህ በኩል ሳትከፍል በዚህ በኩል ውሃ፣ መንገድ የለም ማለት እኛ ጋ ስለተለመደ ነው፡፡ እኛም እንደ መንግስት ገቢ ሳናሰባስብ የምንሰራቸው ሥራዎች የሉም።

ስለዚህ ከፍሎ ከምን ዋለ ? ብሎ ነው ዘመናዊ ማህበረሰብ የሚጠይቀው። መንገድ አልተሰራልኝም ፣ ትምህርት ቤት አልተሰራልኝም ብሎ ከፍሎ ይጠይቅ። ኢትዮጵያ ውስጥ ግብር የሚሰበሰበው የጂዲፒው 6% ነው
" ሲሉ ተናግረዋል።

የነዋሪዎቹ ቅሬታ ግብር መክፈልን መቃረን ሳይሆን የሚጠየቁት የክፍያ አይነቶች መብዛትና መደራረብ ነው ከኑሮ ውድነቱ ጋር ሁነቱን ከባድ ያደረገው የሚል ሀሳብ ስናነሳላቸውም፣ " ማህበረሰቡ ይክፈል፤ የገባበትን ኦዲት እናድርግ። ዘላለም ' ለምን ከፈልኩ ' ማለት ግን ተቀባይነች የለውም " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😭1.44K1.11K😡579🤔43😱33😢21🙏20🕊17👏13🥰11💔3