TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
🔈#የዜጎችድምጽ

" በተደጋጋሚ ቀጠሮዎች ለአላስፈላጊ ወጪና ለጤና ችግሮች እየተዳረግን ነዉ " - ቅሬታ አቅራቢዎች

➡️ " ሴቶችን ጨምሮ ከሌሎች አከባቢዎች የሚመጡ ተገልጋዮች መንገድ ላይ የሚያድሩበት አጋጣሚ ብዙ ነዉ ! "


በኢትዮጵያ ኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ሀዋሳ ቅርንጫፍ ፓስፖርት ለመዉሰድ ፣ አሻራ ለመስጠትና ሌሎችም ከፓስፖርት ጋር ለተያያዙ አገልግሎቶች በተሰጣቸዉ ቀጠሮ መሰረት ወደ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቱ መጥተዉ በተቋሙ በሚስተዋሉ ፍትሐዊ ባልሆኑ አሰራሮች ለአላስፈላጊ ወጪ፣ ለእንግልት እና የጤና ችግሮች እየተዳረጉ መሆኑን ዜጎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

" አሻራ ለመስጠት ሚያዚያ 5/2017 ዓ/ም በተሰጠን ቀጠሮ መሰረት መጥተን ለሁለት ቀናት ከተጉላላን በኋላ ሰኔ 4/2017 ዓ/ም ተመለሱ ተብለን ከግቢዉ እንድንወጣ ተደርገናል " የሚሉት ቅሬታ አቅራቢዎች " በተቋሙ አቅራቢያ እንኳን እንዳንሆን ' ከፌዴራል ለጉብኝት እንግዶች ስለሚመጡ ' በሚል ከመንገድ ላይም በፖሊስ እንድንባረር ተደርገናል" ብለዋል።

በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ቅሬታቸው ያሰሙ አንድ አባት እንደገለፁት " ከጥበቃ አንስቶ ተቋሙ ዉስጥ ያሉ ሰራተኞች ያልተገባ ስነምግባር የሚታይባቸዉና እጅ መንሻ ገንዘብ የማይሰጥና አገልግሎቱን በህጋዊ መንገድ ለማግኘት የሚሞክሩ ተገልጋዮችን እስከ መምታት የሚደርስ እርምጃ እንደሚወስዱ " መመልከታቸዉን አስረድተዋል።

ከግቢ ዉጪ ሆነዉ አዳዲስ የሚመጡ ተገልጋዮችን የገንዘብ አቅም በማጥናት " እኔ ላስጨርስልህ " በሚል ያልተገባ ገንዘብ እየተቀበሉ ዉስጥ ካሉ ሸሪኮቻቸዉ ጋር በመሆን ያለወረፋ የሚያስተናግዱ ደላሎችም ስለመኖራቸዉ ቅሬታ አቅራቢዎቹ ተናግረዋል።

" በዚህ ምክንያት በህጋዊ መንገድ አገልግሎት ማግኘት የሚገባቸዉ ሰዎች ለተደጋጋሚ ቀጠሮዎች ስለሚዳረጉ ለአላስፈላጊ ወጪና እንግልት እንዲሁም በተቋሙ ዉስጥ ባለዉ የሰዉ ብዛት በሚኖረዉ መተፋፈግና መነካካት ለጤና ችግሮች እየተጋለጡ ነው " ሲሉ አብራርተዋል።

አልፎ አልፎ የገንዘብ አቅም ችግር ያላቸዉ ተገልጋዮች እና ወረፋ ለመያዝ የሚፈልጉ ተገልጋዮች ሴቶችን ጨምሮ በተቋሙ በር ላይ የማደር ሁኔታዎች እንደሚስተዋሉም ቅሬታ አቅራቢዎቹ ገልጸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘትና ማጣሪያዎችን ለማድረግ ባደረገዉ ጥረት ምሽት 3 ሰዓት ገደማ በር ላይ ለማደር የተሰበሰቡ ሰዎችን ፓትሮል ፖሊስ ለመበተን ሲሞክር ተመልክቷል።

በተገልጋዮቹ ቅሬታ ዙሪያ ከቅርንጫፍ መስሪያ ቤቱ ምላሽና ማብራሪያ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ " ከዋናዉ መስሪያ ቤት አዎንታ ሲያገኙ ብቻ ለሚዲያ ምላሽ እንደሚሰጡ " በመግለፃቸዉ ሳይሳካ ቀርቷል።

ምላሽና ማብራሪያ እንዳገኘን የምናካትት ይሆናል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
575😭148🙏24😡16😢14😱7🕊7