TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ኦሮሚያ
“ በMpox በአጠቃላይ ኦሮሚያ ክልል ዘጠኝ ኬዞች ደርሰዋል። ሁለት ኬዞች በነቀምት ተገኝተዋል ” - የክልሉ ጤና ቢሮ
በዝንጀሮ ፈንጣጣ /Mpox በሽታ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ዘጠኝ መድረሱን፣ በነቀምት ከተማ ሁለት ኬዞች መገኘታቸውን የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።
የቢሮው ምክትል ኃላፊ ተስፋዬ ክበበው (ዶ/ር) በሰጡን ቃል፣ “ በክልሉ Mpox ከግንቦት 17/2017 ዓ/ም ጀምሮ እየሰራንበት ያለው ኬዝ ነው። በአጠቃላይ በኦሮሚያ ዘጠኝ ኬዞች ደርሰዋል ” ብለዋል።
ከዘጠኙ ኬዞች፣ አምስቱ ሞያሌ፣ ሁለቱ ጅማ፣ ቀሪ ሁለቱ በነቀምት ከተማ የተገኙ መሆናቸውን፣ ከተያዙት ሰዎች መካከል አገግመው የተመለሱ ፤ በክትትል ላይ ያሉ እንዳሉም ተናግረዋል።
“ ክትትል ላይ ያሉት ታመውም ሳይሆን ቆዳ ላይ የሚታይ ምልክቶች አላቸው። ግን ከዛ በዘለለ ሲስተም የሚያስቸግሩ ምልክቶች የሏቸውም ” ያሉት ዶ/ር ተስፋዬ ወደ ሌሎች እንዳያስተላለፉ ለብቻቸው ሆነው ህክምናና ትምህርት እየተሰጣቸው ስለመሆኑ አብራርተዋል።
በክልሉ ለምርመራ ከ100 በላይ ናሙናዎች ከጅማ፣ ከነቀምት፣ ከሸዋ፣ ከምዕራብ ሸዋ፣ ሀረርጌ እንደመጡ ገልጸው፣ “ ብዙዎቹ ተመርምረው ነጌቲቭ ናቸው። ከትላንት በስቲያ ብቻ ወደ 28 ምርመራ ከተደረገው ናሽናሊ ከአንድ ኬዝ ውጪ ኔጌቲቭ ናቸው ” ብለዋል።
ለበሽታው ህክምና ምን መደረግ እንዳለበት በብዛት ስለማይታወቅ በክልል ደረጃ የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጥቶ 300 የሚሆኑ ጤና ባለሙያዎች ወደ ዞን፣ ከተማ፣ ሆስፒታል መመለሳቸውን አስረድተዋል።
ጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው መሠረት በአጠቃላይ በMpox በሽታ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 19 ደርሷል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
ፎቶ፦ ፋይል
@tikvahethiopia

❤888😱193😭165😢42🙏37🕊35🤔17👏16😡14🥰5💔4