TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ደረሰኝ

🔴 " ከዛ ቤት የሚወጣ እቃ ደረሰኝ አያውቅም ይሄንን ሳታውቁ ቀርታችሁ አይደለም። ቻይኖቹን ፈርታችሁ ይሁን ምን ይሁን እኛ አይገባንም " - የውይይት ተሳታፊ

🟠 " የ1 ሚሊዮን ብር እቃ ገዝታችሁ የ300 ሺህ ብር ደረሰኝ ነው የሚፅፉት (ይህ ምሳሌ ነው) " - የውይይት ተሳታፊ

🔵 " ከቻይኖች (ከፋብሪካዎች) ጋር የተነሳው ጉዳይ ከፌዴራልም ጋር በነበረን መድረክ ተነስቷልግብረኃይልም ተቋቁሞ ወደ ስራ ገብቷል " - የአ/አ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ

👉 " ያለ ደረሰኝ ግብይት ፈጽማችሁ የምትገኙ ከሆነ በ100 ሺህ ብር ቅጣት ብቻ አናልፍም ! "

ከሰሞኑን በአዲስ አበባ ከደረሰኝ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑ ይታወቃል።

በዚህም የተነሳ ከአሰራር ጋር ተያይዞ ከነጋዴዎች በኩል አንዳንድ ቅሬታዎች መደመጣቸው አይዘነጋም።

በተለይ ታች ያለው ነጋዴ " ጉዳዩ ስር የሰደደ ነው ከላይ ጀምሮ መጥራት አለበት። መቼ ፋብሪካዎች፣ አስመጪዎች ፣ አምራቾች አከፋፋዮች ደረሰኝ ይሰጡናል ፤ ዝም ብለው አይደል የሚያወጡት መጀመሪያ እነሱን መቆጣጠር አለባችሁ " የሚሉ አስተያየቶችን ሲሰጡ ነበር።

ከቀናት በፊት የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ ቢንያም ምክሩን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ከአስመጪዎች እና አከፋፋዮች ጋር ውይይት ተካሂዶ ነበር።

አንድ የውይይቱ ተሳታፊ " እኛ ፎሬይን ዳይሬክት ኢንቨስትመንት አይተግበር እያልን አይደለም ነገር ግን ዱከም ኢንዱስትሪ ዞንን ዞር ብላችሁ ያያችሁትም አይመስለኝም ፤ እኔ አሁን አሁንማ የሌላ ሀገር እየመሰለኝ መጥቷል። እሱ ቦታ ከዛ ቤት የሚወጣ እቃ ደረሰኝ አያውቅም ይሄንን ሳታውቁ ቀርታችሁ አይደለም። ቻይኖቹን ፈርታችሁ ይሁን ምን ይሁን እኛ አይገባንም " ብለዋል።

" ግራ እየገባን ነው እኛ ሀገራችን ነው ብንሰርቅም እዚሁ ነው የምንጥለው የሆነ ሰዓት መገኘታችን አይቀርም እነሱ ግን ሀገራቸው አይደለም ሰርቀው ይዘውት ነው የሚሄዱት " ሲሉ ተናግረዋል።

ሌላ ተሳታፊው " በኢስት ኢንዱስትሪ ዞን ያለው ነገር ግልጽ ነው ይሄ ለናተ ተደግሞ መነሳትም ያለበት ነገር አይደለም ፤ የ1 ሚሊዮን ብር እቃ ገዝታችሁ የ300 ሺህ ብር ደረሰኝ ነው የሚፅፉት (ይህ ምሳሌ ነው)" ብለዋል።

" በአንድ ደረሰኝ ከ20 እና 30 በላይ መኪና ይመላለሳል " ሲሉ ገልጸዋል።

" ኢንቨስትመንቱ ሁሉም ነገር እንዳለ ሆኖ ግን ሀገራችን ላይ እናተ በአቅማችሁ ደረጃ ማኔጅ ማድረግ የማትችሉትን ነገር ነው መሰለኝ እየፈቀዳችሁ ያላችሁት ለፎሬይን ኢንቨስትመንት ምክንያቱም ከውጭ ፌሬይን ኢንቨስትመንት ይግባ ሲባል ያንን ማኔጅ ማድረግ እንችላለን ወይ ? የሚለው ጥያቄ አብሮ መመለስ አለበት ካልሆነ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል እንደ ሀገር ። እዛ ላይ የሚመለከተው አካል ይስራበት " ሲሉ አክለዋል።

በዚሁ ጉዳይ ላይ የከተማው ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ቢንያም ምክሩ ሃሳባቸውን ሰጥተው ነበር።

" የተነሳው ትክክል ነው እኛም እናውቀዋለን " ብለዋል።

" ከቻይኖች ጋር የተነሳው ጉዳይ ከፌዴራልም ጋር በነበረን መድረክ ተነስቷል። ከዚህ ጋር የተያያዙ ችግሮችን የሚፈታ በክብርት ሚኒስትሯ የሚመራ የፌዴራል ገቢዎች ፣ ጉምሩክ ኮሚሽን፣ ኦሮሚያ ክልል መንግሥትን ያቀፈ አንድ የጋራ ቅንጅት የሚመራበት ማንዋል ፀድቆ ወደ ስራ ተገብቷል " ሲሉ ተናግረዋል።

" ይህ የኢስት ኢንዲስትሪ ዞንና ሌሎች ጋር የተገናኙ ወደ ከተማው የሚገባ ምርት በሸገር ከተማ ዙሪያ የሚመረቱ ነገር ግን ያለደረሰኝ ከፋብሪካ የሚወጡትን እዛ ያለው አዲስ የተቋቋመው ግብረኃይል ይከታተለዋል " ብለዋል።

በሌላ በኩል ፤ የገቢዎች ቢሮ ኃላፊው በመርካቶም ሆነ በሌላ የከተማው አካባቢ የሚካሄደው የደረሰኝ ቁጥጥሩ ወቅታዊ ሳይሆን በዘላቂነት የሚሰራበት ነው ብለዋል።

ከአሰራር ጋር በተያያዘ ያሉት ችግሮች እንደሚፈቱ ቃል ገብተው ለአስመጪና አስከፋፋዮች ጠንካራ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል።

ኃላፊው ፤ " ከዚህ በኃላ በግልጽ ልንነግራችሁ የምንፈልገው አስመጪ እና አከፋፋይ የሆናችሁ ያለ ደረሰኝ ግብይት ፈጽማችሁ የምትገኙ ከሆነ በ100 ሺህ ብር ቅጣት ብቻ አይደለም የምናልፈው " ብለዋል

" በቀጥታ የኦዲት ምርመራ (Investigation Audit) ውስጥ ነው የምንገባው ይህ ደግሞ በጣን ክፉኛ ይጎዳችኋል " ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

" መርካቶ ውስጥ ያለ ድረሰኝ ግብይት ሙሉ ለሙሉ መቆም አለበት " ያሉም ሲሆን ከጊዜ ጋር በተያያዘ ለሚነሳው ጥያቄ " ለዝግጅት የሚሰጥ ጊዜ የለም ቁጥጥራችን ይጠናከራል "  ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
609😡298😢62🙏62😭44👏37🕊28🤔25😱22🥰19