TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ቅድሚያ የምንሰጠው ለአሜሪካ ነው። እሱ ደግሞ ነገ ይጀምራል " - ትራምፕ

ትራምፕ በመጀመሪያ የሥልጣን ቀናቸው በርካታ ትዕዛዞችን ለማስተላለፍ ቃል ገቡ።

የዶናልድ ትራምፕ በዓለ ሲመት ዛሬ የሚከናወን ሲሆን ቃለ መሐላ በፈፀሙ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ " በታሪካዊ ፍጥነት እና ጥንካሬ " እንደሚንቀሳቀሱ ተናግረዋል።

ይህ የተናገሩት በዋሺንግተን ዲሲ በሺዎች ለሚቆጠሩ ደጋፊዎች ንግግር ባደረጉበት ወቅት ነው።

ትራምፕ ያላቸውን ፕሬዝደንታዊ ኃይል ሁሉ ተጠቅመው ስደተኞችን በገፍ ለማባረር፣ የተፈጥሮ ጥበቃ ላይ የሚያተኩሩ መመሪያዎችን ለመቀነስ እና የስብጥር (ዳይቨርሲቲ) ፕሮግራሞችን ለማስቆም ቃል ገብተዋል።

" ቅድሚያ የምንሰጠው ለአሜሪካ ነው። እሱ ደግሞ ነገ ይጀምራል " ሲሉ ተናግረዋል።

አክለው " ነገ ቴሌቪዥን ስትመለከቱ እንደምትዝናኑ እርግጠኛ ነኝ " ብለዋል።

ትራምፕ ከበዓለ ሲመታቸው በኋላ 200 ገደማ ትዕዛዞች ላይ ፊርማቸውን እንደሚያሰፍሩ ይጠበቃል።

አንዳንዶቹ ትዕዛዞች እንደ ሕግ የሚቆጠሩ ሲሆን ሌሎች ደግሞ ፕሬዝደንታዊ መመሪያዎች ናቸው።

ትራምፕ " እኔ ሥልጣን በያዝኩ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ የባይደን አስተዳደር ያስተላለፋቸው ትዕዛዞች ይሰረዛሉ " ብለዋል።

የሰው ሰራሽ ክህሎትን (AI) ዕድገት የሚያፋጥን እንዲሁም ኢላን መስክ የሚመራው ዶጅ የተባለ መሥሪያ ቤት እንዲቋቋም የሚወጣ ትዕዛዝ እንደሚፈርሙ አሳውቀዋል።

በተጨማሪ፦

➡️ እኤአ በ1963 ስለተገደሉት ጆን ኤፍ ኬኔዲ መረጃዎችን እንደሚለቁ፤

➡️ ወታደራዊ ኃይሉን 'አይረን ዶም' እንዲሠራ እንደሚያዙ፤

➡️ ብዝሀነት፣ እኩልነት እና አካታችነት የሚባሉ ፖሊሲዎችን ከጦር ሠራዊቱ እንደሚያስወግዱ፤

➡️ ፆታ የቀየሩ (ትራንስጀንደር) ሰዎች በሴቶች ስፖርት እንዳይሳተፉ እንደሚያደርጉ፤

➡️ የትምህርትን ሥልጣን ለአሜሪካ ግዛቶች አሳልፈው እንደሚሰጡ ቃል ገብተዋል።

ትራምፕ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሕጋዊ ወረቀት የሌላቸውን ስደተኞች ከአሜሪካ እንደሚያባርሩ ገልጸዋል።

" እናንተን በጣም ደስተኛ የሚያደርጉ ብዙ ትዕዛዞች ማየታችሁ አይቀርም " ሲሉ ለደጋፊዎቻቸው ተናግረዋል።

#BBC

@tikvahethiopia
👏559171😡60🤔39🕊27🙏23😭21😢15😱10🥰5
TIKVAH-ETHIOPIA
" ዜለንስኪ ጥሩ የነበረበት ብቸኛው ነገር ባይደንን ማታለል ብቻ ነበር " - ፕሬዜዳንት ትራምፕ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሊድሚር ዘለንስኪን " ትሁትና ውጤታማ ኮሜዲያን ነው " ሲሉ ወረፏቸው። ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትሩዝ በተባለው የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው የዩክሬኑን ፕሬዝዳንት ቮሊድሚር ዘለንስኪን " ያለ ምርጫ የተቀመጠ አምባገነን ነው " ብለዋል። ትራምፕ…
" ይህን ተናግሬያለሁ ብዬ ማመን ይከብደኛል፤ ዘሌንስኪን በጣም ደፋር መሪ ነው " - ዶናልድ ትራምፕ

አወዛጋቢው የአሜሪካው ፕሬዝዳነት ዶናልድ ትራምፕ ከዚህ ቀደም " አምባገነን " ሲሉ የጠሯቸውን የዩክሬኑን ፕሬዜዳንት ቮሊድሚር ዘለንስኪን " ጀግና መሪ ነው " ሲሉ አሞካሿቸው።

ፕሬዝዳት ትራምፕ በዛሬው ዕለት ከዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው።

ትራምፕ አስቀድመው በዋይት ኃውስ በሰጡት አስተያየት፤ " ለቮሊድሚር ዘለንስኪ ትልቅ ክብር አለኝ " ብለዋል።

በቅርቡ ዘለንስኪን " አምባገነን " ብለው በመጥራታቸው ይቅርታ እንደሚጠይቁ ከቢቢሲ ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ ትራምፕ " ይህን ተናግሬያለሁ ብዬ ማመን ይከብደኛል፤ ዘሌንስኪን በጣም ደፋር መሪ " ነው ሲሉ አሞካሽተዋል።

በዛሬው እለት ከዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሊድሚር ዘሌንስኪ ጥሩ ውይይት እንደሚኖራቸው የገመቱት ትራምፕ፤ በዩክሬን ሰላም ለማምጣት የሚደረገው ጥረት በጥሩ ሁኔታ እና በፍጥነት እየሄደ መሆኑን አስታውቀዋል።

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዶሚር ዘለንስኪ ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር ለመነጋገር እና በዩክሬን ውድ ማዕድናት ዙሪያ ስምምነት ለመፈራረም ትናንት ምሽት ወደ አሜሪካ አቅንተዋል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባሳለፍነው ሳምንት የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሊድሚር ዘለንስኪን " ትሁትና ውጤታማ ኮሜዲያን እንዲሁም ያለ ምርጫ የተቀመጠ አምባገነን ነው " ማለታቸው ይታወሳል።

" ዘለንስኪ አሜሪካን 350 ቢሊየን ዶላር በማስውጣት መጀመር ያልነበረባቸው እና የማያሸንፉት ጦርነት ውስጥ ገብተዋል " ብለዋቸው ነበር።

" ዜለንስኪ ጥሩ የነበረበት ብቸኛው ነገር ባይደንን ማታለል ብቻ ነበር " ሲሉም ነበር የገለጹት።

ትራምፕ " ያለ ምርጫ የተቀመጠ አምባገነን ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ በፍጥነት መንቀሳቀስ ይኖርበታል፤ ካልሆነ ግን የሚያተርፈው ሀገር አይኖርም " ብለውም ነበር።
#AlAin #BBC

@tikvahethiopia
😁1.19K123🤔33😱19🥰17😡16🙏13🕊11😭11😢7👏5