TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.2K photos
1.62K videos
218 files
4.4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" የሰላም ችግር ከሁሉም በፊት ቀድሞ መፍትሔ ማግኘት አለበት " - ፕ/ር መረራ ጉዲና

ባለፈው ሳምንት የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ ፓርቲ (ኦፌኮ) አዲሱን ዋና ፅ/ቤቱን በአዲስ አበባ አስመርቋል።

የቀድሞ ሜክሲኮ የሚገኘው ዋና ፅ/ቤቱ በኮሪደር ልማት ምክንያት በመፍረሱ አዲሱን ቢሮ ቀበና አደባባይ አከባቢ ከፍቶ ስራ አስጀምሯል።

በዚህ ወቅት የኦፌኮ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ንግግር ያደረጉ ሲሆን " አሁንም ሀገራችን ትልቅ ችግር ውስጥ ናት " ብለዋል።

የሰላም ችግር ከሁሉም በፊት ቀድሞ መፍትሔ ማግኘት እንዳለበትም ገልጸዋል። ለዚህ ደግሞ ወደጦርነት የሚመሩትን የፖለቲካ ችግሮች በውይይት መፍታት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።

" የኦሮሞ ህዝብ ፍላጎትም ሆነ የሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ፍላጎት ዘላቂ ሰላም ፣ ጠንካራ የዲሞክራሲ ስርዓት እና በኢኮኖሚ የበለፀገች ኢትዮጵያን ማየት ነው " ያሉ ሲሆን፤ " ይሄን ከግብ ለማድረስ ኦፌኮ'ን ጨምሮ ሌሎች የተቃዋሚ ፖርቲ ህብረቶች ትግላቸውን ማጠናከር አለባቸው " ሲሉ ተናግረዋል።

በወቅቱ ተገኝተው የነበሩ የተለያዩ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች " ህዝቡ ላይ እየደረሰ ያላውን ችግር ለመፍታት ህብረታችንን በደንብ በማጠናከር እና ህዝቡን ከጎን በማሰለፍ አንድላይ መቀጠል ይኖርብናል " ብለዋል።

ኦፌኮ አዲሱን ዋና ፅ/ቤቱን ስራ ባስጀመረበት ወቅት " በአገሪቱ ውስጥ ባለው ወቅታዊ ሁኔታ እና በቀጣዩ ትግል አቅጣጫ ላይ ዝርዝር ውይይት ተደርጓል " ያለ ሲሆን " በዚህ መሠረት በጦርነቱ ጉዳት፣ በኢኮኖሚ ውድቀት ምክንያት የማህበራዊ መቃወስና ወደ መፍረስ እየተኬደ ካለው መንገድ ኢትዮጵያን ለመታደግ ትኩረት ይሰጣል " ብሏል።

#OFC #AddisAbaba

@tikvahethiopia
337😡86🕊40🙏31😭15🤔11😱8😢7🥰5
#OFC  #OLF

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ለአራት ቀናት በአዲስ አበባ ከተደረገ ምክክር በኋላ በኦሮሚያ እየተከሰቱ ያሉ የፖለቲካ፣ የጸጥታ እና የሰብአዊ ቀውሶችን ለመፍታት አብሮ ለመስራት  መስማማታቸውን ኦፌኮ ባወጣው መግለጫ ገልጿል።

ኦፌኮ በመግለጫው መፍትሔና እንደ አቋም የተወሰዱ ዋና ዋና ኃሳቦችን አጋርቷል።

በዚህም፦

- በክልሉ የሚስተዋሉ ግጭቶችን ለመፍታት እና ሰላም ለማስፈን ሁለቱ አካላት ማንኛውንም መንገድ በመጠቀም ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ቃል ገብተዋል።

- ኦፌኮ እና ኦነግ ሌሎች ዋና ዋና ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ሁሉን አቀፍ "የኦሮሚያ ብሔራዊ የሽግግር አንድነት መንግስት/ Transitional National Unity Government of Oromia" ለመመስረት አብረው ለመስራት ተስማምተዋል።

° የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (OLA) የኦሮሞ ነጻነት ተዋጊዎች እንደሆኑና የሽግግር መንግሥት ውስጥ  ሰላምና ደህንነት የኦሮሚያን ወሰን የማስከበር ኃላፊነት እንዲወጣ እንደሚደረግ አመላክቷል።

- አዲስ አበባ የኦሮሚያ ዋና ከተማ መሆኗን በግልጽ እንዲቀመጥና ኦሮሚያ ከተማዋን በቀጥታ የማስተዳደር መብት እንዲኖረው እንዲሁም ከኦሮሚያ ተወስደዋል የተባሉ አከባቢዎችን በዲፕሎማሲያዊ እና ሕጋዊ መንገድ ለማስመለስ ተስማምተዋል።

- የገዳ/ ሲንቄ ሥርዓቶችን ለማጠንከርና በኦሮሞ ባህል ላይ የተመሰረተ የአስተዳደር መዋቅር ለመዘርጋት ተስማምተዋል።

- በገዳ ሥርዓት አስተምህሮ መሰረት በኦሮሚያ ውስጥ ያሉ ሁሉም ብሄረሰቦች ያለምንም ፍርሃትና አድልዎ እንዲኖሩ ለማስቻል እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

- ኦሮሚያ በሁሉም የፌደራሉ መንግስት መዋቅር ማለትም በፍትሕ ተቋማት፤ በመከላከያ ሰራዊት፤ በፌደራል ፖሊስ እንዲሁም የበጀት (የሀብት) ምደባ ላይ ተገቢው ድርሻ እንዲኖረው እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

ኦፌኮ በመግለጫው ከፌዴራል መንግሥት ጋር ለመነጋገር ክፍት መሆኑን የጠቆመ ሲሆን ለሚመጡ ማስፈራሪያዎች፣ ማታለያዎች ወይም ለማይፈጸሙ ተስፋዎች ጥንቃቄ አደርጋለሁ ብሏል።

አክሎም ከመንግስት ጋር የሚደረግ ማንኛውም ስምምነት ተጨባጭ በሆነ ነገር እንዲሁም በጊዜ ገደብ መመዘን አለበት ያለ ሲሆን " ተራ ተስፋዎች አሁን ተቀባይነት የላቸውም " ሲል ገልጿል።

በሰሞነኛው የኦፌኮና ኦነግ መድረክ አባገዳዎች፣ ሃደሲንቄዎች፣ የወጣቶች ተወካዮች፣ የፓርቲ መሪዎች ፣ ታዋቂ ሰዎች ተገኝተው ነበር።

ከዚህ ባለፈ ለረጅም ጊዜ ከእይታ ርቀው የነበሩት የኦነግ መሪ አቶ ዳውድ ኢብሳ ታይተዋል።

🔗 ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😡885301🕊98🤔62🙏39👏25😭17🥰6😢4😁3
#OFC

" በ2018 ምርጫ ለመሳተፍ የምንወስነው እነዚህ መሠረታዊ ጥያቄዎች ምላሽ በማግኘታቸው ላይ የተመሰረተ ነው " - ኦፌኮ


የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የውጭ መረጃ አሰባሳቢ ልዑክ ጋር በዋና ፅ/ቤቱ መወያየቱን ገለጸ።

ፓርቲው ውይይቱ የነበረው በ2018 ዓ/ም የሚካሄደው 7ኛው አጠቃላይ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምርጫ ላይ እንደሆነ አመልክቷል።

" ምርጫው ቁልፍ እና ወሳኝ የተባሉ ጥያቄዎችን አቅርቢያለሁ " ብሏል።

ኦፌኮ " ነጻ፣ ፍትሃዊ እና ተአማኒነት ያለው የምርጫ ሂደት እንዲረጋገጥ መንግስት ሊያሟላቸው የሚገባቸውን መሰረታዊ ጥያቄዎችን እንዲሁም የሀገሪቱን የፖለቲካ ቀውስ አስመልክቶ ዝርዝር እና የማያዳግም ግምገማ አቅርበናል " ብሏል።

በውይይቱ ላይ እነማን ተገኙ ?

ኦፌኮን በመወከል ፦
- የፓርቲው ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና
- የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሱልጣን ቃሲም ተገኝተዋል።

የተባበሩት መንግስታት ልዑካን ቡድን አራት አባላት የያዘ ሲሆን ፦
- በተመድ የአፍሪካ ህብረት ቢሮ (UNOAU) የምርጫ ድጋፍ ክፍል ዋና ኦፊሰር አኪንየሚ ኦ. አዴግባላን
- በኢትዮጵያ የተመድ የነዋሪ አስተባባሪ ጽ/ቤት የሰላምና ልማት አማካሪ ዶ/ር ዘቡሎን ሱይፎን ታክዋን እንዲሁም ሌሎች ሁለት ቁልቅ የተመድ ልዑካን አካትቷል።

ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ምን አሉ ?

" ኦፌኮ በ2018 ምርጫ ላይ መሳተፉ ሙሉ በሙሉ በመሠረታዊ እና በተጨባጭ ለውጦች ላይ የተመሰረተ ነው።

ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ድምፅ የመስጠት ቴክኒካዊ ሂደት ብቻ አይደለም፤ የዲሞክራሲያዊ ሂደት ውጤት ነው። ይህ ሂደት ዛሬ በኢትዮጵያ የለም። በጦርነት እና በፖለቲካ ስደት ውስጥ ተአማኒነት ያለው ምርጫ ማካሄድ አይቻልም። " ብለዋል።

ኦፌኮ፣ ተመድ ዲፕሎማሲያዊ ተጽዕኖውን ተጠቅሞ እንዲያስፈጽም በማሳሰብ ለመንግስት የሚቀርቡ ዝርዝር ጥያቄዎችን አቅርቧል።

በኦፌኮ የቀረቡ ዋና ዋና ጥያቄዎች ምንድናቸው ?

➡️ በኦሮሚያና በመላ ኢትዮጲያ ሰላም ፣ በክልሉ ያለውን አውዳሚ ግጭት ለማስቆም በመንግስት ኃይሎች እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (ኦነሰ) መካከል በአለም አቀፍ ታዛቢዎች የሚረጋገጥ አፋጣኝ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ።

➡️ ሁሉንም የፖለቲካ እስረኞች መፍታት፣ የኦፌኮ አባላትን፣ አመራሮችንና ደጋፊዎችን ጨምሮ በመላ አገሪቱ የታሰሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ሌሎች የፖለቲካ እስረኞች፣ ጋዜጠኞችና አክቲቪስቶች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ።

➡️ በነጻነት የመንቀሳቀስ ዋስትና፣ በተቃዋሚዎች ላይ የሚደርሰው ማስፈራራት፣ ወከባና እስራት እንዲቆም። ኦፌኮ የፓርቲ ጽ/ቤቶችን በነጻነት የመክፈትና የማንቀሳቀስ እንዲሁም ከሃገር ውስጥ አስተዳዳሪዎችና ከጸጥታ ኃይሎች ምንም አይነት ጣልቃ ገብነት ሳይኖር ህዝባዊ ስብሰባዎችን የማድረግ መብት እንዲከበርለት ጠይቋል።

በተጨማሪ፦

➡️ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ የፌደራል ፖሊስ እና የክልል የጸጥታ ኃይሎች አመራሮች በፖለቲካው ሂደት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ገለልተኛ ለመሆናቸው በይፋ ቃል የሚገቡበት እና ጥሰቶችን የሚመረምር ገለልተኛ አካል የሚቋቋምበት ስምምነት እንዲፈረም።

➡️ ከምርጫ በፊት የሁሉም ፓርቲዎች ውይይት፣ በገዥው ፓርቲ እና በሁሉም ዋና ዋና ተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል ግልጽ የሆነ የምርጫ ፍኖተ ካርታ ላይ ለመስማማት የሚያስችል ይፋዊ ውይይት እንዲካሄድ።

➡️ የምርጫ ቦርድን እንደገና ማቋቋም፣ ገለልተኝነቱን ለማረጋገጥ ሁሉም ዋና ዋና የፖለቲካ ፓርቲዎች በሚሳተፉበት ግልጽና አካታችነት ላይ በተመሰረተ ሂደት ኮሚሽነሮችን በመሾም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ (NEBE) እንደገና እንዲዋቀር።

➡️ አሁን በስራ ላይ ያለውንና አሸናፊ ሁሉን የሚወስድበትን የአብላጫ ድምፅ የምርጫ ሥርዓት መሠረታዊ በሆነ መልኩ መከለስ። ሁሉም ማህበረሰቦችና የፖለቲካ ቡድኖች በፓርላማ ውስጥ ፍትሃዊ ውክልና እንዲኖራቸው ለማድረግ ወደ ተመጣጣኝ ውክልና (MMP) የምርጫ ሥርዓት እንዲሸጋገር።

➡️ ገዥው ፓርቲ በመገናኛ ብዙኃን ላይ ያለውን የበላይነት በማስቀረት ሁሉም የተመዘገቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች በመንግስት ሚዲያዎች (EBC, OBN የመሳሰሉት) ላይ ፍትሃዊ እና እኩል የአየር ሰዓት እንዲያገኙ የሚያስችል በገለልተኛ አካል የሚመራ ህጋዊ ማዕቀፍ እንዲዘረጋ።

➡️ በሂደት ላይ ያለው ብሔራዊ ምክክር ሁሉንም የፖለቲካና የትጥቅ ቡድኖችን ያካተተ እንዲሆንና እንደ ፌዴራሊዝምና የራስን ዕድል በራስ የመወሰን ባሉ መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ የሚያስተላልፋቸው ውሳኔዎች አስገዳጅ እንዲሆኑ ማድረግ።

የሚሉትን ጥያቄዎች በይፋ አቅርቧል።

የተመድ ልዑካን ቡድን የምርጫውን ቅድመ-ሁኔታዎች የመገምገም ኃላፊነት የተሰጠው መሆኑን ያመለከተው ኦፌኮ ቡድኑ የቀረበለትን ሃሳብ በትኩረት እንዳዳመጠው ገልጿል።

ኦፌኮ በ2018 ምርጫ ለመሳተፍ የሚያደርገው ውሳኔ እነዚህ " መሠረታዊ " ያላቸው ጥያቄዎች ምላሽ በማግኘታቸው ላይ የተመሰረተ እንደሆነ አሳውቋል።

መረጃውን የላከው የኦፌኮ የህዝብ ግንኙነት ፅ/ቤት ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
2.09K👏137😡113🤔54😭54🕊37🙏26💔23🥰20😱9😢8
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#OFC

የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን ማካሄድ መጀመሩን የህዝብ ግንኙነት ፅ/ቤቱ በላከልን መረጃ ገለጸ።

" በአገሪቱ ላይ የተደቀነውን የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የፀጥታ ቀውስ ለመገምገም እና የፓርቲውን የወደፊት አቅጣጫ ለመቀየስ የሚያስችለውን ወሳኝ ስብሰባ ነው " ብሏል።

ዛሬ ስብሰበው በፓርቲው የውስጥ አቅም ግንባታና ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ላይ ያተኮረ እንደነበር አመልክቷል።

የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት የፓርቲውን አመራርና ድርጅታዊ ብቃት ለማጠናከር ልዩ ሥልጠናዎችን እንደወሰዱና ሥልጠናው በፍጥነት በሚለዋወጥና ፈታኝ በሆነው የፖለቲካ ምህዳር ውስጥ የኦፌኮን የወደፊት አቅጣጫ ለመቅረፅ ያለመ እንደሆነ ገልጿል።

ነገ ደግሞ ውይይቱ ትኩረት " በኦሮሞ ሕዝብ፣ በኢትዮጵያና በሰፊው የአፍሪካ ቀንድ ክልል ላይ በተደቀኑት ከባድ ፈተናዎች ላይ ይሆናል " ብሏል።

" በአጀንዳው ውስጥ በዋናነት የተካተቱት ጉዳዮች በቀጠለው ጦርነትና ማኅበረሰቡን ባወደመው ከፍተኛ የፀጥታ እጦት፣ በመንግሥት የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም የተባባሰው ከባድ የኢኮኖሚ ችግር፣ የተንሰራፋው የወጣቶች ሥራ አጥነት እና ስር የሰደደው ሥርዓታዊ ሙስና ናቸው " ሲል ገልጿል።

በእነዚህ ውይይቶች ማዕከላዊው ጉዳይ ፓርቲው ለመጪው የ2018 አገራዊ ምርጫ ያለው ስትራቴጂ እንደሆነ አመልክቷል።

" ኦፌኮ ነፃ፣ ፍትሐዊ እና እምነት የሚጣልበት ምርጫ በማካሄድ እውነተኛ የዲሞክራሲ ሽግግርን ለማረጋገጥ መንግሥት እንደ ቅድመ ሁኔታ የፖለቲካ ምህዳሩን እንዲከፍት ተጨባጭና ሊረጋገጡ የሚችሉ እርምጃዎችን እንዲወስድ ጥያቄዎቹን በይፋ ያቀርባል " ብሏል።

ስብሰባው ከተጠናቀቀ በኃላ ፓርቲው ይፋዊ መግለጫ እንደሚያወጣ ጽ/ቤቱ በላከልን መረጃ አሳውቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamliyAA

@tikvahethiopia
558😡94🤔22🙏17👏13🕊12😱11😢3
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#OFC

" በሰላማዊ ትግል ለመቀጠል ቁርጠኛ ነኝ " - የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ)

🗳" በ2018 ሀገራዊ ምርጫ ለመሳተፍ ቁልፍ ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጠናል ! "

የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ማዕከላዊ ኮሚቴ ለሁለት ቀናት ያካሄደውን መደበኛ ጉባኤ ዛሬ እንዳጠናቀቀ ገለጸ።

ፓርቲው በጉባኤው ማጠናቀቂያ ላይ መግለጫ አውጥቷል።

" ሀገሪቱ የመንታ መንገድ ላይ ትገኛለች " ያለው ፓርቲው " ቀጣዩ ምርጫ 'በዲሞክራሲያዊ መታደስ ወይም በሀገር መፍረስ' መካከል የሚደረግ " ነው ብሏል።

" ያለፉት ሰባት ዓመታት 'የባከነ ተስፋ' የታየባቸው እንዲሁም የፖለቲካ፣ የጸጥታና የኢኮኖሚ ቀውሶች እርስ በርስ እየተመጋገቡ ወደ ከፋ ጥፋት ያመሩበት ጊዜ ነበር " ሲል ገልጿል።

" ለዚህ ሀገራዊ ውድቀት ዋነኛውን ምክንያት በሕብረ ብሄራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት ላይ የተፈጸመ ስልታዊ ጥቃትና ሰላማዊ የፖለቲካ አማራጮች በሙሉ መዘጋታቸው ነው " ሲል አመልክቷል።

ፓርቲ በመጪው የ2018 ሀገራዊ ምርጫ ላይ የሚሳተፈው በቅድመ ሁኔታ እንደሆነ ገልጿል።

ኦፌኮ " 'ለተሰባበረ የፖለቲካ ሂደት' ሕጋዊ ዕውቅና አልሰጥም " ያለ ሲሆን " በምርጫው ፍተሃዊነትና ታዓማኒነት የሚረጋገጠው መንግሥት መሰረታዊ የሆነ ዳግም ማስተካከያ ሲያደርግ ብቻ  ነው " ብሏል።

ፓርቲው " ቁልፍ " ያላቸውን ቅድመ ሁኔታዎች ይፋ አድርጓል።

" እነዚህም ፦

1. በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ያለው ጦርነት በአፋጣኝና በዓለም አቀፍ ታዛቢዎች በተረጋገጠ መልኩ እንዲቆም እና ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ውይይት እንዲጀመር።

2. ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ፤ ይህም ለሀገራዊ እርቅ መሰረት እንዲሆን። የፖለቲካ ነጻነቶች ሙሉ በሙሉ እንዲከበሩ፤ የታሸጉ የኦፌኮ ቢሮዎች እንዲከፈቱ እንዲሁም አፋኝ የሆኑ፣ የምርጫ ፣የሚዲያና የሲቪል ማህበረሰብ ሕጎች እንዲሻሩ።

3. የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የህዝብን አመኔታ መልሶ እንዲያገኝ በሁሉም ፓርቲዎች ሙሉ ስምምነት ላይ ተመስርቶ በአዲስ መልክ እንዲዋቀር። " የሚሉ ናቸው።

ኦፌኮ በማጠቃለያው " የኦሮሞ ህዝብ አንድነቱን እንዲያጠናክር " ሲል ጥሪ አቅርቦ " ከሌሎች የኦሮሞና የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ጋር ቃልኪዳን ለዲሞክራሲ ለመፍጠር የትብብር እጁን መዘርጋቱን " አመልክቷል።

"  ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም በመንግሥት ላይ ተጨባጭ ጫና ያሳድር " ሲል ገልጿል።

ኦፌኮ ፥ በሰላማዊ ትግል ለመቀጠል ቁርጠኛ መሆኑን አሳውቆ " ለዲሞክራሲ ምቹ ሁኔታን የመፍጠር ዋነኛው ኃላፊነት በገዥው ፓርቲ ላይ የሚወድቅ ነው " ሲል አቅጣጫ አስቀምጧል።

መረጃውን የላከው የፓርቲው ህዝብ ግንኙነት ፅ/ቤት ነው።

#TikvahEthiopiaFamliyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
665😡117🤔29🕊26👏12🙏5😭4😱2