" ወረዳው ከነእቃዬ ሜዳ ላይ ጥሎኝ የኔን ጉዳይ ይዞ የነበረውን ዳኛ ከቤቴ አስገባው " - እንባ የሚተናነቃት ወጣት
በአዲስ አበባ አስተዳደር የካ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ቀበሌ 9/10 የምትገኝ ወጣት ከአሳዳጊ አክስቷ ጋር ትኖርበት ከነበረው የቀበሌ ቤት አሳዳጊዋ ስትሞት ከቤቱ እንድትወጣ ተደርጋ ጎዳና እንደወጣች በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል እሮሮ አሰምታለች።
" ወረዳው ከነእቃዬን ሜዳ ጥሎ የኔን ጉዳይ ይዞ የነበረውን ዳኛ ከቤቴ አስገባው " ብላለች።
ወርቅነሽ አለሙ የምትባለው ይህች ወጣት የአባቷ ታላቅ እህት ከ3 ዓመቷ ጀምሮ ከባህር ዳር ወደ አ/አ አምጥታት ነው ያሳደገቻት።
እዚሁ ቤት እስከ 2016 ዓ/ም ማለቂያ ድረስ ነበሩ።
በ2016 ዓ/ም አሳዳጊ አክስቷ ከሞትች ከ40 ቀናት በኃላ ወረዳው " ወራሽ ልጅ ስላልሆሽ ልቀቂ " ይላታል።
ጉዳዩን ይዛ ፍርድ ቤት ሄደች። ፍርድ ቤትም ሄዳ መፍትሄ አልተሰጣትም።
" ወረዳ እኔን ጠዋት በግብረ ኃይል ከነእቃዬ አውጥቶ ጥሎኝ ከሰዓት በኋላ ራሱ የኔን ጉዳይ ይዞ የነበረውን ዳኛ ቤቴ ውስጥ አስገባው " ስትል ቅሬታ አሰምታለች።
ከዚህ አለፍ ሲል ቤቱ ሁለት ክፍል ሆኖ ሳለ ወደ አራት ክፍል አስፋፍቶ ሰርቶት ዞር ብሎ የጠየቀው አካል የለም ብላለች።
ወረዳው ምን ምላሽ ሰጠ ?
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታውን ይዞ የወረዳ 6 ጽ/ቤት አስተዳደር ኃላፊ አቶ ምስጋናው ሂጂቱን አነጋግሯል።
ቅሬታዋ አቅራቢዋ ልጅ ከሆነች የመውረስ መብት እንዳላት አምነውበታል።
ኃላፊው ፤ " ባለመብት ናት የቀበሌ ቤት መውረስ የሚችለው ልጅ ነውና ልጅ ከሆነች መውረስ መብቷ ነው " ብለዋል።
" በሕጉ መሠረት የቀበሌ ቤት ፣ ልጅ ከሆነች የመውረስ መብቷ የተጠበቀ ነው ፤ በዚያ ደረጃ ሆኖ ከነበረ እኔ ጋ ይምጡ እናስተካክላለን ይሄ የተነሳው ጉዳይ ትክክል ከሆነ " ሲሉ ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ ጉዳይ ተጨማሪ ማብራሪያ እና ግልጽነት ስለሚፈልግ የሕግ ባለሙያ አነጋግሯል።
የሕግ ባለሙያ የሆኑት አቶ ጥጋቡ ደሳለኝ ምን አሉ ?
- ኑዛዜውን ማጽደቅ ትችላለች። ግን የቀበሌ ቤት ላይ ተወላጆች ካልሆኑ በስተቀር ከሕግ አንጻር በባዮሎጂካል ተወላጅ ያልሆነ ልጅ የጉጂፈቻ ማስረጃ ቀደም ሲል ሊኖር ይገባል።
- ለቀበሌ ቤት የጉዲፈቻ ማስረጃ ስሌላት ውርስ ተቀባዩዋን ከሞራልና ከአስተዳደራዊ አንጻር ካልሆነ በስተቀር ከሕግ አንጻር የወረዳው አስተደዳደር ሊያስተናግዳት አይችልም።
- ከሞራል አንጻር አሳዳጊዋ ስላረፉ፣ ልጅቷ ደግሞ ተተኪ ልጅ ናት፤ በሥነ ልቦና እናትና ልጅ ሆነው አብረው ኖረዋል። የቀበሌ ቤት የሚባለው ደግሞ አነስተኛ ገቢ ያላቸው ሰዎች የሚኖበት ነው። ስለዚህ ከሕግ አንጻር የኑዛዜ ተቀባይ መሆን ባትችልም አንዱ ወጥቶ ሌላው የሚገባበት፣ ለዜጎች የተሰራ ቤት በመሆኑ ልትኖርበት ይገባ ነበር ከሞራል አንጻር።
- ከሕግ አንጻር በቀበሌ ቤት ላይ ኑዛዜ ማድረግ አይቻልም።
- ለምሳሌ የፌደራል ኪራይ ቤቶችን አንድ ሰው ተከራይቶ ቢኖር ሲሞት ሊናዘዝበት አይችልም። ምክንያቱም የንብረቱ ባለቤት መንግስት ነው። በመሳሳይ ሁኔታ የቀበሌ ቤቶች ውስጥ የሚኖር ሰው ሲሞት ኑዛዜ ሊያደርግ አይችልም። ኑዛዜ ማድረጉ በሕግ ውጤት አያመጣም።
- በዜጎች ንብረትና ሕይወት ላይ ውሳኔ የሚሰጡ ሰዎች (ዳኞች) ከወረዳ ጋር በመመሳጠር ክርክር በተነሳበት የመንግስት ቤት ውስጥ መግባት የሕግ ጥሰት ነው። ሕግን ያልተከተለ አካሄድ ነው። በተወሰነ ደረጃ ሙስና ተብሎ ጉዳዩን ወደ ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ብታመለክትበት ዳኛው ከኃላፊነቱ የሚነሳበት ቀጥተኛ ማስረጃ ነው የሚሆነው።
- ክርክር በተነሳበት ጉዳይ ላይ የጥቅም ግንኙነት በመፍጠር እንዲህ ማድረግ ትልቅ የዲሲፒሊን ጥፋት ነው።
- ልጅቷ ቅጹ ላይ አለች፣ ደባል ናት፣ የቤተሰብ አባል ናት ቀጥተኛ ልጅ ባትሆንም፣ የቀበሌ ቤቶች ደግሞ አነስተኛ ገቢ ላላቸው ሰዎቸ ነው የተዘጋጁት፣ ሜዳ ላይ መጣል የለባትም ብሎ የወረዳው አስተዳደር ወስኖ ወይ በዚያው ቤት ሊያስቀጥላት ይገባል የቀበሌ ቤቱ የሚፈርስ ከሆነም ምትክ የመንግስት ቤት እንድታገኝ ሁኔታዎችን ማመቻቸት አለበት።
- በህሊና ፍርድ ወይ አስተዳደራዊ በሆነ መንገድ የወረዳው አስተዳደር መፍትሄ ሊሰጣት ይገባል።
ያንብቡ ፦ https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-12-08
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
5😢569❤166😭80😡80🙏38👏26🕊10🥰8😱3
" በተደጋጋሚ ቀጠሮዎች ለአላስፈላጊ ወጪና ለጤና ችግሮች እየተዳረግን ነዉ " - ቅሬታ አቅራቢዎች
➡️ " ሴቶችን ጨምሮ ከሌሎች አከባቢዎች የሚመጡ ተገልጋዮች መንገድ ላይ የሚያድሩበት አጋጣሚ ብዙ ነዉ ! "
በኢትዮጵያ ኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ሀዋሳ ቅርንጫፍ ፓስፖርት ለመዉሰድ ፣ አሻራ ለመስጠትና ሌሎችም ከፓስፖርት ጋር ለተያያዙ አገልግሎቶች በተሰጣቸዉ ቀጠሮ መሰረት ወደ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቱ መጥተዉ በተቋሙ በሚስተዋሉ ፍትሐዊ ባልሆኑ አሰራሮች ለአላስፈላጊ ወጪ፣ ለእንግልት እና የጤና ችግሮች እየተዳረጉ መሆኑን ዜጎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
" አሻራ ለመስጠት ሚያዚያ 5/2017 ዓ/ም በተሰጠን ቀጠሮ መሰረት መጥተን ለሁለት ቀናት ከተጉላላን በኋላ ሰኔ 4/2017 ዓ/ም ተመለሱ ተብለን ከግቢዉ እንድንወጣ ተደርገናል " የሚሉት ቅሬታ አቅራቢዎች " በተቋሙ አቅራቢያ እንኳን እንዳንሆን ' ከፌዴራል ለጉብኝት እንግዶች ስለሚመጡ ' በሚል ከመንገድ ላይም በፖሊስ እንድንባረር ተደርገናል" ብለዋል።
በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ቅሬታቸው ያሰሙ አንድ አባት እንደገለፁት " ከጥበቃ አንስቶ ተቋሙ ዉስጥ ያሉ ሰራተኞች ያልተገባ ስነምግባር የሚታይባቸዉና እጅ መንሻ ገንዘብ የማይሰጥና አገልግሎቱን በህጋዊ መንገድ ለማግኘት የሚሞክሩ ተገልጋዮችን እስከ መምታት የሚደርስ እርምጃ እንደሚወስዱ " መመልከታቸዉን አስረድተዋል።
ከግቢ ዉጪ ሆነዉ አዳዲስ የሚመጡ ተገልጋዮችን የገንዘብ አቅም በማጥናት " እኔ ላስጨርስልህ " በሚል ያልተገባ ገንዘብ እየተቀበሉ ዉስጥ ካሉ ሸሪኮቻቸዉ ጋር በመሆን ያለወረፋ የሚያስተናግዱ ደላሎችም ስለመኖራቸዉ ቅሬታ አቅራቢዎቹ ተናግረዋል።
" በዚህ ምክንያት በህጋዊ መንገድ አገልግሎት ማግኘት የሚገባቸዉ ሰዎች ለተደጋጋሚ ቀጠሮዎች ስለሚዳረጉ ለአላስፈላጊ ወጪና እንግልት እንዲሁም በተቋሙ ዉስጥ ባለዉ የሰዉ ብዛት በሚኖረዉ መተፋፈግና መነካካት ለጤና ችግሮች እየተጋለጡ ነው " ሲሉ አብራርተዋል።
አልፎ አልፎ የገንዘብ አቅም ችግር ያላቸዉ ተገልጋዮች እና ወረፋ ለመያዝ የሚፈልጉ ተገልጋዮች ሴቶችን ጨምሮ በተቋሙ በር ላይ የማደር ሁኔታዎች እንደሚስተዋሉም ቅሬታ አቅራቢዎቹ ገልጸዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያም በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘትና ማጣሪያዎችን ለማድረግ ባደረገዉ ጥረት ምሽት 3 ሰዓት ገደማ በር ላይ ለማደር የተሰበሰቡ ሰዎችን ፓትሮል ፖሊስ ለመበተን ሲሞክር ተመልክቷል።
በተገልጋዮቹ ቅሬታ ዙሪያ ከቅርንጫፍ መስሪያ ቤቱ ምላሽና ማብራሪያ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ " ከዋናዉ መስሪያ ቤት አዎንታ ሲያገኙ ብቻ ለሚዲያ ምላሽ እንደሚሰጡ " በመግለፃቸዉ ሳይሳካ ቀርቷል።
ምላሽና ማብራሪያ እንዳገኘን የምናካትት ይሆናል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤575😭148🙏24😡16😢14😱7🕊7