TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ የዘንድሮው በጀት ዓመት የፌዴራል መንግስት የአጠቃላይ በጀት 1.5 ትሪሊየን ብር ሆኗል። ዛሬ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት 582 ቢሊየን ብር ተጨማሪ የፌደራል መንግስት በጀት አፅድቋል። ለ2017 በጀት ዓመት ተጨማሪ ሆኖ የፀደቀው በጀት ፦ - ለውጭ እና ለሀገር ውስጥ ዕዳ ክፍያ፣ - ለማህበራዊ በጀት ድጎማ (ለነዳጅ፣ ለማዳበሪያ፣ ለመድሐኒት፣ ለምግብ ዘይትና ሌሎች)፣ - ለካፒታል ፕሮጀክቶች…
#ኢትዮጵያ

" ... የውጭ ምንዛሬ ለውጡ in in terms of Dollar ያመጣውን ለውጥ ሊያካክስ የሚችል የደመወዝ ጭማሪ መጨመር ነበረበት " - ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር)

🔴 " አንድ ደመወዝተኛ በውጭ ምንዛሬ ስናሰላው ያገኝ የነበረው ገቢ በዶላር ከ50% በላይ እንዲቀነስ ተደርጓል !! "


የህ/ተ/ም/ቤት አባሉና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ተወካዩ ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) በተጨማሪ በጀቱ ዙሪያ ስጋቶች እንዳላቸው ገልጸዋል።

የማክሮ ኢኮኖሚ እና ፊስካል ማዕቀፍ ማሻሻያው ሀገራዊ ውጥቅጥ ውስጥ እንዳስገባን በግልጽ እንደሚታይ ተናግረው ይሄ በጀት እሱን ምን ያህል አ
ተደራሽ ያደርጋል ? ሲሉ ጠይቀዋል።

ከዚህ ባለፈም ደሳለኝ (ዶ/ር) ፤ ስለ ኑሮ ውድነት ፣ ስለሰራተኞች የደመወዝ ጭማሪ ፣ በጀቱን ለመሸፈን ስለሚጣል ግብር አንስተው ጠይቀዋል ፤ ሃሳባቸውን አካፍለዋል።

ምን አሉ ?

" በኑሮ ውድነት ላይ / ቋሚ ደመወዝተኛ በሆነው አካል ላይ የውጭ ምንዛሬው (Foreign exchange) ለውጡ የፈጠረው ጫና አለ።

አንድ ደመወዝተኛ በውጭ ምንዛሬ ስናሰላው ያገኝ የነበረው ገቢ በዶላር ከ50% በላይ እንዲቀነስ ተደርጓል ፤ በውጭ ምንዛሬው ለውጥ ምክንያት።

መንግሥት የደመወዝ ማሻሻያ በተለይ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ተቀጣሪዎችን
ደመወዝ ማሻሻያ አድርጊያለሁ ቢልም አብዛኛው ደመወዝተኛ ከ1 ሺህ ብር እና ከ2 ሺህ ብር በላይ ጭማሪ አልተደረገለትም። ስለዚህ እነዚህ የማህበረሰብ ክፍሎች ኑሯቸውን እንዴት እንዲመሩ ታስቦ ነው ?

በእኔ በኩል ቢያንስ መንግሥት ሌሎች የmarket variables ትቶ የውጭ ምንዛሬ ለውጡ in in terms of Dollar ያመጣውን ለውጥ ሊያካክስ የሚችል ጭማሪ መጨመር ነበረበት።

አንድ የ12 ሺህ ብር ደመወዝተኛ ከምንዛሬ ለውጡ በፊት ወደ 300 እስከ 350 ዶላር አካባቢ ያገኝ ነበር አሁን መንግሥት ጨመርኩ ያለው 1 ሺህ ብር ነው ወደ ዶላር ሲቀየር ደመወዙ የሚወድቀው ወደ 150 ዶላር አካባቢ ነው።

ይህ ከፍተኛ ጫና፣ የመንግሥት ሰራተኛውን ወደ ልመና፣ ወደ ጎዳና እያስወጣው እንደሆነ  መሸፈን በማንችልበት ሁኔታ ዘገባዎች እየወጡ ነው።

ስለዚህ ይህን በስነስርዓት address በሚያደርግ መንገድ የደመወዝ ማስተካከያው መስተካከል ነበረበት። ጭማሪውም ለዛ ትኩረት መስጠት ነበረበት።

ሌላው የ281.5 ቢሊዮን ተጨማሪ ታክስ raise በማድረግ ይሄን 532 ቢሊዮን ተጨማሪ በጀት ለመሸፈን ከሚደረገው ውስጥ አንደኛው ታክሱ ነው።

ይህ ከፍተኛ የታክስ ጫና (burden) ነጋዴው ላይ የሚጭን ነው። ነጋዴው ላይ ከፍተኛ የታክስ ጫና እየፈጠረ ነው። የንግዱ ማህበረሰብን ከፍተኛ confusion (መደናገር) ውስጥ እየተከተተው ነው።

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ጋር ተያይዞ ቀድሞውኑ shock ውስጥ ነው ቢዝነሱ ፤ ብዙ ነጋዴዎች confusion ውስጥ እንደገቡ ይናገራሉ ከዛ ላይ ተጨማሪ confusion እና ተጨማሪ መደናገጥ እንዲሁም shock የሚፈጥር ነው ይሄ እንዴት ታስቦ ነው ?

መንግሥት fair በሆነ መንገድ ከከፍተኛ ታክስ ከፋዩ ላይ ከሚደበቁትን፣ የታክስ ሆሎችን ተጠቅመው የሚሰወሩትን እሱን መሰብሰብ አለበት በእርግጠኝነት ፤ ግን ደግሞ ከአቅም በላይ የሆነውን የመንግሥት spending compensate ለማድረግ ሲባል የታክስ ጫናውን ከአቅም በላይ መለጠጥ በንግድ እንቅስቃሴው ላይ በተለይ በሀገር ውስጥ የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ያለው ችግር በደንብ ተገምግሟል ? የሚኒስትሮች ም/ቤት ይሄን እንዴት አይቶት ነው ?

ሌው ጭማሪው 532 ቢሊዮኑ በዋነኝነት ለዕዳ ክፍያ፣ ለማህበራዊ ድጎማ ፣ ለደመወዝ ጭማሪ እንደሚውል ነው የተገለጸው።

ባለፈው 971 ቢሊዮኑ በጀቱ ሲፀድቅ አሁንም የካፒታል ፕሮጀክቶችን ጉዳይ አንስቼ ነበር። መንግሥት literally ትቶታል።
- አዲስ መንገድ
- አዲስ ግድብ
- አዲስ ዩኒቨርሲቲ
- አዲስ ሆስፒታል ... አዳዲስ መሰረተ ልማቶችን መተው የሚታየው አሁን በተጨመረው 582 ቢሊዮን ውስጥ 90 ቢሊዮን ብቻ የካፒታል ፕሮጀክት ማሻሻያ ብቻ ነው የተካተተው።

ሌላው ነገር የለም። already እያልን ያለነው ኮሪደር ልማት ብቻ እንስራ ነው። እንደዚህ ሆኖ ሀገር እንዴት ሊለማ ይችላል ? መሰረታዊ የሚባሉ የ irrigation development ፣ ግድቦች ላይ ፣ አገር አቋራጭ መንገዶች ላይ፣ ፈጣን መንገዶች ላይ ፣ የኃይል ተቋማት ላይ፣ ሆስፒታሎች ፣ ዩኒቨርሲቲዎች ላይ እንዲህ አይነት critical የሆኑ የህዝብ መሰረተ ልማቶች ላይ በጀታችንን ካላዋልነው አሁንም ዞሮ ዞሮ የማብለጭለጭ አይነት ልማት structurally ምንም ለውጥ የማያመጣ ልማት ላይ ነው እንዳለ ገንዘባችንን ፈሰስ እያደረግን ያለነው። እዚህ ላይ ስጋት አለኝ።

መሰረታዊ የሚባሉ investment ላይ መንግሥት ውጪውን ቅድሚያ መስጠት አለበት። "

#TikvahEthiopia #ደመወዝ #ዶክተርደሳለኝጫኔ

@tikvahethiopia
👏3.29K407🙏126🥰61🕊32😭31🤔23😢20😱19😡18
#ደመወዝ

🚨 " የሚከፈለው ክፍያና እንከፍላለን ብለው የሚያሳውቁት በጣም የሚያስቅ ልዩነት ያለው ነው " - ገቢዎች ቢሮ

🔴 " ቢሮው የፈጸመው ህገወጥ ድርጊት ነው " - የህግ ምሁር


የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ሆቴሎች እና መጠጥ ቤቶችን ጨምሮ በተመረጡ የንግድ መስኮች የሚሰሩ ሰራተኞችን ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እና የሰራተኞቻቸውን ብዛት የሚተምን ተመን አውጥቶ ስራ ላይ አውሏል።

ሆቴሎች፣ ስጋ ቤቶች፣ መጠጥ ቤቶች ፣ ምግብ ቤቶች፣ ካፍቴሪያዎችን ጨምሮ ሌሎች የንግድ ዘርፎች ላይ የሰራተኞች ደመወዝን በተመለከተ አሰሪዎች ትክክለኛ መረጃ ስለማይሰጡ ግብር እያጭበረበሩ ነው ብሏል።

ይህንን ተከትሎም ነው ይህን አሰራር መዘርጋቱን ገልጻል።

ስራ ላይ በዋለው ተመን መሰረት ፦
👉 የሆቴሎች ከ32 እስከ 50 ሰራተኞች
👉 ባርና ሬስቶራን ከ20 እስከ 24 ሰራተኞች
👉 ካፍቴሪካ ከ17 እስከ 25 ሰራተኞች
👉 ምግብ ቤት ከ17 እስከ 22 ሰራተኞች
👉 ምግብ፣ መጠጥ እና ስጋ ቤት ከ28 እስከ 48
👉 ስጋ ቤት እና መጠጥ ንግድ ከ20 እስከ 28 ሰራተኞች ይኖራቸዋል ተብሎ ተተምኗል።

በዚህ መሰረት የደመወዝ ግብር በተጠቀሰው የሰራተኛ ቁጥር ልክ ይጠየቃሉ።

ከአስተናጋጅ፣ ጥበቃና የፅዳት ሙያ ውጭ ላሉ ሰራተኞች ትንሹ የሚከፍሉት ደመወዝ 5,000 ብር ሆኖ ተተምኗል።

የወር ደመወዝ ተመኑ ምን ይመስላል ?

ስጋ ቤት እና መጠጥ ንግድ
° የስራ አስኪያጅ /ተቆጣጣሪ/ ከ5,000 እስከ 9,500
° ካሸር 5,000 እስከ 6,000
° ዋናው ሼፍ ከ5,000 እስከ 18,000
° አስተናጋጅ ከ3,000 እስከ 3,500
° ፅዳት ከ2,500 እስከ 3,000
° ጥበቃ ከ2,500 እስከ 3,000
° ዋና ስጋ ቆራጭ ከ5,000 እስከ 7,000
° ረዳት ስጋ ቆራጭ ከ5,000 እስከ 5,500
° ስጋ ጠባሽ ከ6,000 እስከ 9,000

ምግብ፣ መጠጥ እና ስጋ ቤት
° የስራ አስኪያጅ /ተቆጣጣሪ/ ከ8,000 እስከ 13,500
° ካሸር 5,000 እስከ 7,000
° ዋናው ሼፍ ከ6,000 እስከ 18,000
° አስተናጋጅ ከ2,500 እስከ 4,000
° ፅዳት ከ3,000 እስከ 3,500
° ጥበቃ ከ3,500 እስከ 4,000
° ዋና ስጋ ቆራጭ ከ5,000 እስከ 6,000
° ረዳት ስጋ ቆራጭ ከ5,000 እስከ 5,500
° ስጋ ጠባሽ ከ6,000 እስከ 9,000

ምግብ ቤት
° የስራ አስኪያጅ /ተቆጣጣሪ / ከ6,000 እስከ 10,000
° ካሸር 5,000 እስከ 6,000
° ዋናው ሼፍ ከ5,000 እስከ 7,000
° አስተናጋጅ ከ2,000 እስከ 3,000
° ፅዳት ከ2,500 እስከ 3,000
° ጥበቃ ከ2,500 እስከ 3,000

ካፍቴሪያ
° የስራ አስኪያጅ /ተቆጣጣሪ/ ከ6,000 እስከ 7,000
° ካሸር 5,000 እስከ 7,000
° ዋናው ሼፍ ከ5,500 እስከ 7,000
° አስተናጋጅ ከ2,500 እስከ 3,000
° ፅዳት ከ2,500 እስከ 3,000
° ጥበቃ ከ2,500 እስከ 3,000
° ሻይ ቡና / ጁስ አስተናጋጅ ከ5,000 እስከ 8,000

ባርና ሬስቶራንት
° የስራ አስኪያጅ /ተቆጣጣሪ/ ከ7,000 እስከ 10,000
° ካሸር 5,000 እስከ 6,000
° ዋናው ሼፍ ከ5,000 እስከ 7,000
° አስተናጋጅ ከ2,000 እስከ 2,500
° ፅዳት ከ2,500 እስከ 3,000
° ጥበቃ ከ3,000 እስከ 3,500

ሆቴል
° የስራ አስኪያጅ /ተቆጣጣሪ/ ከ8,000 እስከ 13,500
° ካሸር 5,000 እስከ 7,000
° ዋናው ሼፍ ከ6,000 እስከ 18,000
° አስተናጋጅ ከ2,500 እስከ 4,000
° ፅዳት ከ3,000 እስከ 3,500
° ጥበቃ ከ3,500 እስከ 4,000
° ዋና ስጋ ቆራጭ ከ5,000 እስከ 6,000
° ረዳት ስጋ ቆራጭ ከ5,000 እስከ 5,500

ወርሃዊ
ደመወዝ ተተምኗል።

ይህ ለአንድ ሰራተኛ ይከፈላል ተብሎ የተተመነ ነው።

በዚህ ተመን ባለቤቶቹ የደመወዝ ግብር ሲከፍሉ ለተጠቀሱት የስራ መደቦች " ከዚህ ያነሰ ነው የምከፍለው " ማለት አይችሉም።

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ ምን አሉ ?

ቢሮው ተመን ማውጣቱን አረጋግጠዋል።

ዳይሬክተሩ " በጥናት ላይ ተመስርቶ ነው ውሳኔው የተቀመጠው።

ከደመወዝ ግብር ጋር በተያያዘ የሚከፈለው ክፍያና እንከፍላለን ብለው የሚያሳውቁት በጣም የሚያስቅ ልዩነት ያለው ነው። በጣም ትልቅ ክፍተት ነው ያለው እኛ በከተማችን ያሉ የስራ መደቦችን በዝርዝር ጥናት አድርገን አብዛኛው በትንሹ የሚከፈላቸው ከ5000 ብር በላይ መሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም።

ለፅዳት እና የቤት ሰራተኛ እንኳን ስንት እንደሚከፈል ይታወቃል።

እነሱ እንከፍላለን ብለው የሚያቀርቡት ዋጋ በጣም በጣም ዝቅተኛ ነው። ያንን ምንቀበልበት ሁኔታ የለም አሰራሩም አይፈቅድም። ጥናት ላይ ተመስርተን ዝቅተኛውን ተመን አስቀምጠናል " ብለዋል።

ገቢዎች ቢሮ ከተማውን የምታመነጨውን ገቢ አሟጦ ለመሰብሰብ ኃላፊነት እንደተጣለበትና በዚህም ምክንያት ዝቅተኛ የደመወዝ ተመን ስራ ላይ እንዳዋለ አሳውቋል።

ጉዳዩ በሚመለከተው አካል ህግ ሆኖ ሳይወጣ ገቢዎች ቢሮ ዝቅተኛ የደመወዝ መጠን አስቀምጦ ግብር መሰብሰብ ይቻላል ወይ ? የሚለው የህግ ጥያቄ ተነስቶበታል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ንግድና የኢኮኖሚ ህጎች መምህር አቶ ጌዲዮን ወ/ዮሐንስ ምን ይላሉ ?

" ድርጊቱ ህገወጥ ነው።

እስካሁን ባለው ነባራዊ  ሁኔታ በገቢዎች በኩል አነስተኛ ደመወዝን መወሰን ያንን ተከትሎ ግብር መሰስበብ እስካሁን ባለው የህግ ማዕቀፍ ይህንን የሚፈቅድ ነገር ስለሌለ ህጋዊ አይደለም።

በተለይ ከግብር ጋር ተያይዞ ህገመንግስቱ ግብር የሚጣለው በህግ ነው ይላል። በአንድ አስፈጻሚ / በአንድ የስራ ክፍል ኃላፊ ወይም እንደ ገቢዎች ቢሮ አይነት ደብዳቤን መሰረት አድርጎ ደመወዝን መወሰን አይቻልም።

ደመወዝ ግብር የሚከፈልበት አንድ ገቢ ነው። ይሄም ታክስ ቤዝ / ግብር የሚጣልበት አንድ ገቢ እንለዋለን። እሱ በህግ ተወስኗል። ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ከዚህ እስከዚህ ሲሆን ይሄን ያህል ... ከዚህ እስከዚህ ይሄን ያህል ... ብር እየተባለ በግብር አዋጃችን ላይ ተቀምጧል።

በዚህ በገቢ ግብር አዋጅ ላይ በተለያዩ የስራ ክፍሎችና አይነቶች የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ዝቅተኛውን የደመወዝ መጠን ለመወሰን ስልጣን ተሰጥቶታል የሚል ህግ የለም ኢትዮጵያ ላይ።

በህግ ባልተከለከለበት / አይቻልም ባልተባለበት ሁኔታ አንድ ሰው 10,000 ብር ነው ዝቅተኛ መቅጠር የምትችለው ፣ በ8,000 ነው በ18,000 እያሉ ሰንጠረዥ ማውጣት የሰዎችን የመዋዋል ነጻነት ይጎዳል።

ድርጊቱ፦
- የመዋዋል ነጻነትን የሚገድብ
- ህገመንግስታዊ ድንጋጌን የሚጥስ ተግባር ነው።

ቢሮው ' ግብር እየተጭበረበርኩ ነው ' ብሎ ካሰበ የተለያዩ የምርመራ ስራዎችን በመስራት ፣ የስራ ውሉን ከአሰሪዎቹ በመቀበል ይሄም ደግሞ በህግ አነስተኛ ደወመዝን በማውጣትና በመደንገግ ነው። እንጂ የግብር ማጭበርበር ለመከላከል ተብሎ የገቢ ግብርን በዚህ መንገድ ለማስተዳደር መሞከር የታክስ ህግን፣ መርሆችን የሚጥስ ነው። "

NB. በኢትዮጵያ እስካሁን ድረስ መንግሥት ለግሉ ዘርፍ ለተቀጣሪዎች ዝቅተኛ ደመወዝ ወለል አላስቀመጠም። ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እንዲያስቀምጥ ጥረቶች እየተደረጉ እነደሆነ ይታወቃል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ነው። #ሸገርኤፍኤም

@tikvahethiopia
1.03K😡316🤔198👏93🙏70🕊61🥰54😢51😱48😭41💔1