TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63K photos
1.61K videos
216 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#USA ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቀዳሚ ስራቸው ዶክመንት የሌላቸውን / ሰነድ አልባ ስደተኞችን በብዛት ከሀገር ማስወጣት ነው ተብሏል። የትራምፕ ዘመቻ ቃል አቀባይ ካሮሊን ሌቪት እንደገለፁት ትራምፕ በፕሬዚዳንትነት ስልጣናቸው ከሚወስዷቸው የመጀመሪያ እርምጃዎች መካከል አንዱ ዶክመንት የሌላቸው / ሰነድ አልባ ስደተኞችን በብዛት ለማስወጣት የገቡትን ቃል መፈጸም ነው። ሌቪት ፥ ትራምፕ…
#ዴሞክራሲ #አሜሪካ

" ሕዝቡ የሚመርጠውን እንቀበላለን " - ተሰናባቹ ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን

ተሰናባቹ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን የ2024 የአሜሪካ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫን ዶናልድ ትራምፕ ካሸነፉ በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ንግግር አድርገዋል።

በዚህም ፥ ለተተኪያቸው ዶናልድ ትራምፕ ስልክ ደውለው " የእንኳ ደስ ያለዎት !" መልዕክት ማስተላለፋቸውን ተናግረዋል።

ባይደን ከዲሞክራቷ ዕጩ ካማላ ሀሪስ ጋር እንደተናጋገሩ አስታውቀው " መልካም አጋር እና የሕዝብ አገልጋይ ናት " ብለዋል።

የካማላ የምርጫ ዘመቻን " አነቃቂ " ሲሉ ያሞገሱት ባይደን ምክትል ፕሬዝደንቷ በሥራቸው እንዲኮሩ መክረዋል።

" አንዲት ሀገር ምርጫዋ አንድ ነው። ሕዝቡ የሚመርጠውን እንቀበላለን " ሲሉም ተናግረዋል።

ባይደን " ስናሸንፍ ብቻ አይደለም ሀገራችንን የምንወደው፤ ስንስማማ ብቻ አይደለም ጎረቤታችንን የምንወደው " የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።

ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር እንደሚኖርም አስታውቀዋል።

የምርጫ አስተባባሪዎችም " ምስጋና ይገባቸዋል " ብለዋል።

ተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ጥር 12/2017 በኦፊሴላዊ መንገድ መንበረ-ሥልጣኑን ይረከባሉ።

የ2024 ፕሬዝደንታዊ ምርጫ " ታሪካዊ ነው " ያሉት ባይደን በሚቀጥሉት 74 ቀናት ያልተቋጩ ሥራዎችን ጨርሰው ሥልጣናቸውን እንደሚያስረክቡ አሳውቀዋል።

" መሸነፍ ያለ ነው። ነገር ግን ተስፋ መቁረጥ ይቅር የማንለው ነው " ብለዋል።

በሌላ በኩል ፥ የዲሞክራቲክ ፓርቲ ዕጩ የሆነው ለፕሬዝዳንትነት ከዶናልድ ትራምፕ ጋር የተፎካከሩት ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስ ሽንፈታቸውን ተቀብለው ለተመራጩ ፕሬዝዳንት መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

ሃሪስ፥ ለትራምፕ ስልክ ደውለው " እንኳን ደስ አለዎ " ማለታቸው ተዘግቧል።

ሃሪስ ለትራምፕ ስልክ ደውለው የ2024 ፕሬዝዳንታዊ ምርጫን በማሸነፋቸው ውጤቱን መቀበላቸውን የሚያመለክት መልካም ምኞታቸውን ገልጸውላቸዋል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia
773👏202🕊47🙏39😡38😢17😭14🤔12😱11🥰2
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ዴሞክራሲ 👏 #ሶማሌላንድ

" የምርጫ ውጤቱን እንቀበላለን " - ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ

ባለፈው ሳምንት በራስ ገዟ ሶማሌላንድ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ መደረጉ ይታወሳል።

በከፍተኛ ብልጫም የተቃዋሚው ዋደኒ ፓርቲ መሪ አብዲራህማን ሞሐመድ አብዱላሂ " ኢሮ " ምርጫውን አሸንፈዋል።

በምርጫው የተሸነፉት ተሰናባቹ ፕሬዜዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ " የምርጫውን ውጤት እንቀበላለን " ብለዋል።

ተመራጩ ፕሬዜዳንትንም " እንኳን ደስ አልዎት ! " ብለዋቸዋል።

" ባስመዘገቡት ድል እንኳን ደስ አልዎት " ያሉት ፕሬዜዳንት ቢሂ " ሰላማዊና የተረጋጋ የስልጣን ሽግግር እንዲደረግ ለማድረግ የተሟላ ድጋፌን አደጋለሁ  " ሲሉ ቃል ገብተዋል።

" የአገልግሎት ዘመንዎ ሰላምን ፣ እድገትን እና ዘላቂ ስኬትን ለሀገራችን እንዲያመጣ እመኛለሁ " ብለዋል።

ተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ቢሂ ለህዝቡ ባስተላለፉት መልዕክት " ፕሬዝዳንታችሁ ሆኜ እንዳገለግላችሁ ዕድሉን ስለሰጣችሁኝ አመሰግናለሁ " ሲሉ ገልጸዋል።

" የስልጣን ዘመኔ ማብቂያ ላይ ሆኜ የምለው ነገር ለሀገራችን እድገት ያለኝ ቁርጠኝነት ጸኑ መሆኑን ነው " ሲሉ አክለዋል።

" በአንድነት እና በጋራ ተነስተን ለሶማሌላንድ ብልፅግና እንስራ " ብለዋል።

6ኛው የሶማሌላንድ ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡት አብዲራህማን ኢሮ " ማንም ተሸናፊ ማንም አሸናፊ የለም ያሸነፈው የሶማሌላንድ ህዝብ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

ሶማሌላንድ እራሷን እንደ ሉዓላዊ ሀገር ምትቆጥር ናት። ከሶማሊያ መንግሥት ጋርም ግንኙነት የላትም። ላለፉት በርካታ ዓመታት ራሷን በራሷ እያስተዳደረች ነው።

እጅግ ሰለማዊ ፣ የተረጋጋ ፣ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ በማድረግ እና ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር በማድረግ ትወደሳለች።

#TikvahEthiopia #ቲክቫህኢትዮጵያ
#Somaliland

@tikvahethiopia
👏2.06K210🙏60🕊52🥰20🤔17😱12😭9😡9😢5