TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ድሬዳዋ

" አንድም ጫኝ እና አውራጅ የሚባል ነገር እንዳይኖር። ነግሬያችኃለሁ
!! " - ኮሚሽነር ዓለሙ

የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ዓለሙ መግራ ድሬ ውስጥ ሰዎች ቤት ሲቀይሩ " ጫኝ አውራጅ ነን እያሉ የሚከተሉ ጎረምሶች እንዳይኖሩ " ሲሉ ትዕዛዝ አስተላለፉ።

ይህን እጅግ ጠንካራ ትዕዛዝ የሰጡት ከከተማውን የፀጥታ አመራሮች ጋር በመከሩበት ወቅት ነው።

በህዝብ ላይ እንግልትና ዘረፋ በሚፈፅሙ ጫኝና አውራጆች ላይ የተጠናከረ እርምጃ ይወሰዳል ተብሏል።

ኮሚሽነር ምን አሉ ?

" ሰፈር ላይ ቁጭ ብሎ ሰው ቤት ሲቀይር ጫኝ አውራጅ ብሎ የሚከተል ጎረምሳ እንዳይኖር።

በየቀጠናችን ያለው የጫኝ አውራጅ ስቃይ ህዝቡን ብታዩ አንድም ጫኝ እና አውራጅ የሚባል አደረጃጀት የለም።

ይሄን ያደራጀ ሰው ካለ ኃላፊነቱን አናውቀውም።

አንድም ጫኝ እና አውራጅ በየትኛውም ቀጠና የውሃ ፋብሪካ ምናም ካልሆነ በስተቀር ሰፈር ላይ ቁጭ ብሎ ሰው ቤት ሲቀይር ጫኝ አውራጅ ብሎ የሚከተል ጎረምሳ እንዳይኖር።

ይሄ ከተገኘ እወቁ ! አንድም ቦታ ሰውዬው ሲፈልግ ተሸክሞ ያውርድ ሲፈልግ ይስበረው።

በቀደም አንዱ መጥቶ ነገረኝ ትንሽ እቃ ነው በዳማስ ሄዶ ቀስ ቀስ እያለ አወረደ ... ከዛ ሮጠው መጡና አንኳኩ ' ክፈቱ ' አሉ ግር ብለው ገቡ ፤ እቃው ወርዷል ከዛ ' ስጡን (ብር) ' አሉ ለምን ? ' የደንቡን ' የምን ደንብ ? እኛ አውርደናል እቃችንን አላቸው ' ሊሰጠን ይገባል አታውቅም እንዴ ይሄ የሰፈሩ ደንብ ነው ' አሉ።  ሰውዬው ወደ ፖሊስ ሲደውል ከግቢ ወጥተው በር ላይ ቁጭ አሉ። ትንሽ ሲቆይ አንድም ሁለትም እየሆኑ ሄዱ።

እኚህ ወጣቶች ሌላ ቀን ወንጀል ከመስራት ወደኃላ አይሉም። ለዚህ ነው ሰግቶ የነገረኝ።

ሰው በፍርሃት ነው ያለው።

አይቻልም አንድም ጫኝ እና አውራጅ የሚባል !! ነግሬያችኃለሁ።

ቤት ሲቀየር ገና ሰው እዛ ጋር መጥቶ የሚያወርደውን ነገር ታሳቢ ተደርጎ ነው ሰው የሚደራጀው ስራ ?

አይቻልም !

ብሎኬት ማውረድ ከፈለገ ሰውየው ቤት ሲሰራ እዛው ጋር የሚሰሩትን ሰዎች ማስወረድ ይችላል ፤ ሌላ ሰው ጠርቶ ዋጋ ተደራድሮ እሱ ባለው ዋጋ ማስወረድ ይችላል አለቀ።

' እኔ ማህበር ነኝ ፤ እኔ እንደዚህ ነኝ ' ማን እንዳደራጃቸው የማይታወቁ።

አንድም እንዳይኖር ይሄን ሰፈራችሁ ላይ አወያዩ ፤ ማህበረሰቡ ይሄን ይወቅ ለናተ መረጃ ይስጣችሁ። ሰፈር መድረስ ማለት ይሄ ነው።

ጫኝ እና አውራጅ ጣጣው በጣም ብዙ ነው " ብለዋል።

ይሄ የጫኝ እና አውራጅ ስቃይ የድሬዳዋ ብቻ አይደለም። በአዲስ አበባ በየሰፈሩና በክልል ከተሞች ተመሳሳይ ነው።

ገና ሰው እቃ ይዞ ሲመጣ " እኛ ካላወረድን ማንም ማውረድ አይችልም " በሚል አምባጓሮ የሚፈጡ አሉ።

አውርዱ ሲባሉ ደረታቸውን ነፍተው የሚጠሩት ብር ደግሞ አስደንጋጭ ነው።  ሰው በስንት ድካም ገንዘቡን እንደሚያገኝም አይረዱም።

ሰው ከፍራቻ የተነሳ በስንት መከራና ጭቅጭቅ ከፍተኛ ዋጋ ከፍሎ እቃውን ያስወርዳል። " ነገ የት እኖራለሁ " ብሎ በመፍራት።

እራሱና ቤተሰቦቹ፣ ጓደኞቹ በጋራ የገዛ እቃቸውን እንዳያወርዱ ዛቻ ሁሉ ሊፈጸምባቸው ይችላል።

ይህንን ስርዓት አልበኝነትና ድንፋታ እንዲያስቆሙ የሚጠሩ አንዳንድ የፀጥታ አባላት ነገሩን ለማስተካከል እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ የሚሉት ' ከነሱ ጋር ተስማሙ ' ነው።

ሰው ከፍራቻ የተነሳ ለሊት እቃውን ይዞ ይገባል። በገዛ ሀገሩ በገዛ ከተማው በገዛ እቃው ተሳቆ ነው የሚኖረው። ስቃዩ ብዙ ነው !

#TikvahEthiopiaFamily

#DirePolice #ድሬ

@tikvahethiopia
👏7.87K980🙏513🕊119🥰101😱36😢34🤔28😡22😭16