TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#DireDawa

" በወንጀል ተግባሩ ላይ የተሳተፉ የፖሊስ አመራር እና አባላት በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራው ወደ መጠናቀቁ ነው " - ድሬ ፖሊስ

ከሰሞኑን በድሬዳዋ ከተማ አንድ ወጣት በአሰቃቂ ሁኔታ በፖሊስ አባላት ድብደባ መገደሉ በርካቶችን አስቆጥቷል ፤ አሳዝኗል።

በተለይ ገንደቦዬ ዛሬም ድረስ ሀዘን ላይ ናት።

የ1 ልጅ አባት የሆነው ወጣት ሙራድ መሀመድ (አሳዶ) ከሰሞኑን በፖሊስ ድብደባ ለሞት መዳረጉ ተነግሯል።

የቅርብ ወዳጆቹ ፥ " ሙራዴ ከሰው ጋር ተግባቢ ፤ በሚኖርበት አካባቢ ገንደቦዬ ላይም የሚታወቅ ፤ የሚወደድ ወንድማችን የሰፈራችን ድምቀት ነበር። ህግ አለባት በምንልበት ከተማችን ያውም ደግሞ ህግ አስከባሪ ተብሎ ዩኒፎርም በለበሱ ፖሊስ አባላት በአሰቃቂ ሁኔታ ተደብድቦ ተገደለ መባሉ እጅግ በጣም አስደንግጦናል፣ አሳዝኖናል ፣ አስቆጥቶናል " ብለዋል።

" የተፈጸመው አሰቃቂ ወንጀል ሰዎች በፖሊስ እና የህግ የበላይነት ላይ ጥያቄ እንዲያነሱ የሚያደርግ ነው። ሙራድ ሰላማዊ ህይወቱን እየመራ ባለበት ነው ይህ ግፍ የተፈጸመው " ሲሉ አክለዋል።

" ፍትህ ሊሰጥ ፤ እውነት ሊወጣ ፣ ወንድማችንን ለሞት የዳረጉት የሚገባቸውን ቅጣት ሊያገኙ ይገባል " ሲሉ አክለዋል።

የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ፥ " ወጣት ሙራድ መሀመድን በግል ቂም በቀል ተነሳስተው ኢሰብዓዊ በሆነ መልኩ በመደብደብ ፣ ለሞት በመዳረግ አስነዋሪ ተግባር የፈጸሙ አባላቶችን በቁጥጥር ስር አውለን ምርመራ በማጣራት ላይ ነን " ሲል መግለጫ አውጥቷል።

ድርጊቱ " ጥቂት " ሲል በጠራቸው የፖሊስ አባላት መፈጸሙን አመልክቷል።

ወጣት ሙራድ በፖሊስ አባላት ተደብድቦ ለሞት በመዳረጉ እጅግ ማዘኑን ገልጾ " ጠቅላይ መምሪያውን በፍጹም የማይወክል ነው " ብሏል። " አስነዋሪ " ሲል የጠራውን የወንጀል ተግባርም አውግዟል።

አሁን ላይ በወንጀል ተግባሩ ላይ የተሳተፉ የፖሊስ አመራር እና አባላት በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራው ወደ መጠናቀቁ እንደሆነ ገልጿል።

ወጣቱ ተደብድቦ ለሞት ከተዳረገ በኃላ ስርዓተ ቀብሩ በተፈጸመበት ወቅት የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ ከድር ጁሀር ፤ " ግለሰባዊ የቂም በቀል ጥላቻ ነው የመንግሥትን ልብስ ሽፋን አድርጎ የተፈጸመው " ያሉ ሲሆን ድብደባውን ፈጽመው ሙራድን ለሞት የዳረጉት 3 የፖሊስ አባላት እንደሆኑ ገልጸዋል።

" ጣቢያ አላመጡትም ፤ ከዚራ አላመጡትም እኛም ምንም መረጃ አልነበረንም ፤ ወስደው በድብደባ ነው የሞተው። ማታ ጤና ጣቢያ መልካ ላይ ነው የተወሰደው ከዛ በኃላ ነው መረጃው የደረሰን " ብለዋል።

በሙራድ መሀመድ ህልፈት ሀዘናቸውን ገልጸው " ልጅ አለው፣ ሚስት አለው እናትም አለው ቤተሰቦቹን የማገዝ እና መርዳት ኃላፊነት አለብን " ሲሉ ተናግረዋል።

#Murad #DireDawa #Police

@tikvahethiopia
😢1.68K😭489214😡171🙏55🕊44👏22😱22🥰16🤔14
TIKVAH-ETHIOPIA
" ግለሰቡ ስነምግባር የጎደለው በአሽከርካሪው ላይም ሲያደርግ የነበረው አጸያፊ ተግባር ነው ፤ ተይዞ ምርመራ እየተጣራ ነው " - ፖሊስ የድሬዳዋ ፖሊስ በአንድ የከባድ ተሽከርካሪ ሹፌር ላይ " አጸያፊ " ሲል የጠራውን ተግባር የፈጸመ ግለሰብን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን አሳውቋል። ሰሞኑን በአንድ የከባድ መኪና አሽከርካሪ ተቀርጾ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተሰራጨ ቪድዮ አለ። ይኸው ቪድዮ…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#DireDawa

" የትኛውም አሽከርካሪ ላይ የሚደርስን የትኛውም አይነት ህገወጥ ተግባር አንታገስም ! " - ድሬዳዋ ፖሊስ

በድሬዳዋ " ፎርስ " እየተባለ የሚጠራው ተሽከርካሪ የሚያሽከረክር ሹፌር ላይ አፀያፊ ህገወጥ ተግባር የፈጸመ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የድሬዳዋ ፖሊስ አሳውቋል።

አሽከርካሪዎች ላይ የሚፈጸም ማንኛውም ህገወጥ ድርጊት አልታገስም ሲልም ገልጿል።

በድሬዳዋ ፖሊስ የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥር መምሪያ ኃላፊ ም/ኮማንደር ይሔነው ሽፈራው ፥ " አፀያፊ ድርጊቱ የተፈጸመው ህብረተሰቡን በሰላማዊ ሁኔታ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ የሚያጓጉዝ ፣ የሚያደርስ እና የሚመልስ የፎርስ አሽከርካሪ ላይ ነው " ብለዋል።

ድርጊቱ የተፈጸመው ' ሳቢያን አንበጣ ' አካባቢ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

" ግለሰቡ ከፎርስ አሽከርካሪው ጋር አለመግባባት ሲፈጠር የተሽከርካሪውን ቁልፍ ጭምር ነቅሎ ይዞ ሲሄድ የሚታይበት ምስል በቀጥታ ወደእኔ ነው የተላከልኝ ከዛ ወዲያ በአቅራቢያው ላለው ለጎሮ ፖሊስ ጣቢያ መረጃውን ሰጠናቸው እነሱም ወዲያው ድርጊቱን የፈፀመውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውለውታል " ብለዋል።

ህብረተሰቡ መሰል ህገወጥ ተግባራት ሲመለከት መረጃ እየሰጠ መሆኑ የሚበረታታ መሆኑን ገልጸዋል።

ም/ኮማንደር " የትኛውም አሽከርካሪ ላይ የሚፈጸምን የትኛውም አይነት ህገወጥ ተግባር አንታገስም፤ እንዲህ ያለው ድርጊት የሚፈጽሙትን በትዕግስት አናይም " ብለዋል።

" በከተማችን ያሉ ሁሉም አሽከርካሪዎች በእኩብ አይን ነው የምናያቸው ፤ ከተማ ውስጥ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አሽከርካሪዎች ምንም አይነት ጥቃት ሳይደርስባቸው አገልግሎት እንዲሰጡ እንፈልጋለን " ሲሉ አክለዋል።

የጎሮ ፖሊስ ጣቢያ አዛዥ ኢንስፔክተር አበበ ጥላሁን ፥ " መጋቢት 5 ከምሽቱ 11 ሰዓት ተኩል ገደማ ላይ ነው ' በቀጠናችሁ የተፈጸመ ወንጀል ነው ' በሚል በቪድዮ መረጃው የደረሰን " ብለዋል።

" የተላከውን ቪድዮው ስንመለከት MM ሆቴል አካባቢ በሚገኘው የታክሲ መሳፈሪያ ቦታ ላይ በታክሲ ተራ አስከበሪ አማካኝነት የተፈጸመ የወንጀል ተግባር ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

ድርጊት ፈጻሚው ተራ በአስከባሪነት እዛ ይሰራ የነበረ ኤርሚያስ ማሞ የተባለ ግለሰብ እንደሆነና ሚያዚያ 6 በስራ ቦታው ላይ እያለ ተይዞ ምርመራ እየተጣራ መሆኑን አመልክተዋል።

" ማንኛውም ግለሰብ ድሬዳዋ ላይ ወንጀል ፈጽሞ ማምለጥ አይችልም " ብለዋል።

የድሬዳዋ ፖሊስ በቅርቡ በአንድ የከባድ ተሽከርካሪ ሹፌር ላይ " አጸያፊ " ሲል የጠራውን ተግባር የፈጸመ ግለሰብን በቁጥጥር ስር ማዋሉ ይታወሳል።

#DirePolice

#TikvahEthiopiaFamilyDD

@tikvahethiopia
1.02K👏619😡37🙏27🥰24😱13🕊12😢11😭6🤔4