TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.9K photos
1.61K videos
216 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በአዲስ አበባ ከፍጥነት ወሰን በላይ በማሽከርከር ለሞት የሚዳርጉ 5 መንገዶች የትኞቹ ናቸው ?

በተደረገ የዳሰሳ ጥናት ከፍጥነት ወሰን በላይ በማሽከርከር ከፍተኛ የሞት አደጋ የሚያስከትሉ 5 መንገዶች ተለይተዋል።

ከፍተኛ የሞት አደጋ ያስከትላሉ ተብለው የተለዩት ፦
° መገናኛ፣
° ኃይሌ ጋርመንት፣
° ቦሌ ሚካኤል፣
° ጦር ኃይሎች
° ቻይና ካምፕ መንገዶች ናቸው። በአማካይ በዓመት ከ6 እስከ 13 ዜጎች በእነዚህ መንገዶች በሚደርሱ የተሽከርካሪ አደጋቸው ሕይወታቸውን ያጣሉ።

ከመንገዶቹ አንዳንዶቹ የእግረኛ መተላለፊያ የላቸውም ፤ አሽከርካሪዎች ይህን ግምት ውስጥ በማስገባት ከፍጥነት ወሰን በላይ እያሽከረክሩ አደጋ ያደርሳሉ።

ከፍጥነት ወሰን በላይ በማሽከርከር በሚደርሰው የትራፊክ አደጋ፣ በአብዛኛው ሕይወታቸውን የሚያጡት ወንዶች ናቸው። መገናኛ አካባቢ አደጋ ከደረሰባቸው 13 ሰዎች አብዛኞቹ ወንዶች መሞተዋል።

አደጋ የሚደርሰው ከቀኑ 6፡00 ሰዓት እስከ 8፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ሲሆን በተለይም ሰንበት ወይም የዕረፍት ቀናት ከመንገድ መጨናነቅ ነፃ ስለሚሆኑ፣ ተከትሎ በፍጥነት ማሽከርከር ምክንያት የሞት ምጣኔው ከፍተኛ ነው።

አደጋዎች የሚያሳዩት ተቆጣጣሪ ተቋማትም ሆኑ አደጋ አድራሾችና ተጎጂዎች የሚያደርጉት ጥንቃቄ ዝቅተኛ እንደሆነ ነው።

ከፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት ከባድ ተሽከርካሪዎች ናቸው። ከሌሎች የተሽከርካሪ ዓይነቶች አብላጫውን አደጋ የሚያደርሱትም እነሱ ናቸው።

በዓለም የጤና ድርጅት የትራፊክ አደጋ ሥጋት መንስዔዎች ተብለው የተለዩት በፍጥነት ማሽከርከር፣ ጠጥቶ ማሽከረከር፣ የደኅንነት ቀበቶ አለመጠቀምና የራስ ቅል መሸፈኛ አለመጠቀም ከፍተኛውን ቦታ ይይዛሉ።

43 በመቶ የሚሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ አሽከርካሪዎች ከፍጥነት ወሰን በላይ ያሽከረክራሉ። በዚህ ምክንያት ችግሩ ትኩረት ያሻዋል።

በየዓመቱ ከ400 የሚበልጡ ሰዎች በትራፊክ አደጋ ይሞታሉ። የጥናቶች የትኩረት አቅጣጫ የፍጥነት መገደቢያ መጠቀምና ሥር ነቀል የማኅበረሰብ ግንዛቤ ማስጨበጥ ያስገልጋል።   

(የአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ማኔጅመንት መረጃ)

#ሪፖርተርጋዜጣ

@tikvahethiopia
🙏437😭178173👏45🕊31😢22😱14🥰13😡13🤔11
" ' ነፍስ እናመጣለን ' ማለት የቀራቸው ማስታወቂያዎች፣ በጤናው ዘርፍ ላይ ከፍተኛ አደጋ ደቅነዋል " - ጤና ሚኒስቴር

በተለያዩ ሚዲያዎች የሚሠራጩ የተጋነኑና " ነፍስ እናመጣለን " ማለት የቀራቸው ማስታወቂያዎች፣ በጤናው ዘርፍ ላይ ከፍተኛ አደጋ መደቀናቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

አሳሳቢነታቸው እየጨመረ ያለውና ሕዝቡን የሚያደናግሩ የተጋነኑና እውነት ያልሆኑ ማስታወቂያዎች መንግሥት ባለበት አገር መቆጣጠር ካልተቻለ፣ በማኅበረሰቡ ላይ ከዚህ የባሰ ችግር መፍጠራቸው የማይቀር መሆኑን፣ በጤና ሚኒስቴር የጤናና ጤና ነክ ተቋማትና ባለሙያዎች ቁጥጥር መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ እንዳልካቸው ፀዳል ተናግረዋል።

በሐሰተኛ ማስታወቂያዎች " ነፍስ እናመጣለን " በቀረው ልፈፋ፣ ኅብረተሰቡ እየተጭበረበረና ገንዘቡን ጭምር እየተዘረፈ ነው ተብሏል።

አቶ እንዳልካቸው ፀዳል ምን አሉ ?

" በጤና ግብዓትም ሆነ አገልግሎት ላይ በአገር ደረጃ የሕግ ክፍተት የለም " ያሉ ሲሆን ነገር ግን በተለይ ወደ ታችኛው ማኅበረሰብ ሲኬድ የአፈጻጸም ችግሮች ጎልተው እንደሚታዩ ገልጸዋል።

ተቋማት በተሰጣቸው የሥልጣን ዕርከን ተገዥ ሆነው አለመሥራት አንዱ የቁጥጥር ክፍተት እንደሆነ አመልክተው " የተጋነኑና ከእውነት የራቁ ማስታወቂያዎች ከፍተኛ ችግር እየፈጠሩ ናቸው " ብለዋል።

አንዳንድ ባለሙያዎች በማኅበራዊ ሚዲያ " እኔ ነኝ የተሻልኩ " ብለው የሚያቀርቡት መረጃ በጤናው ዘርፍ ላይ ትልቅ ሥጋት ፈጥሯል ብለዋል።

ያለ ምንም ተጨባጭ ማስረጃ ሌሎች ባለሙያዎችን ማጥላላትና መሰል ችግሮች ማኅበረሰቡን መጉዳታቸው አይቀርም ሲሉም ገልጸዋል።

" ሚዲያው በእኛ ሥር ስላልሆነ ለቁጥጥርና ለክትትል አስቸግሮናል " ያሉት አቶ እንዳልካቸው ፤ ሚዲያውን የሚቆጣጠሩ አካላት የሚያሠራጯቸውን ማስታወቂያዎች በአግባቡ ሊከታተሉና ሊቆጣጠሩ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የጤና ሚኒስትር ደኤታ አየለ ተሾመ (ዶ/ር)  ምን አሉ ?

የመረጃ አቅርቦት አማራጮች በመበራከታቸው ምክንያት በግለሰቦችም ሆነ በተቋም ደረጃ የሚደርሱ መረጃዎች  ለማኅበረሰቡ መልካም ሆነው ሳለ፣ ነገር ግን የመረጃ ፍሰቱ የተለያዩ ተግዳሮቶችን ይዞ መምጣቱን ተናግረዋል።


በጤና ዘርፍ የሚቀርቡ መረጃዎች ብዙ ማስረጃዎችና የማጣሪያ ደረጃዎችን አልፈው መቅረብ ሲገባቸው ለማኅበረሰቡ ትክክል ያልሆኑ፣ ግራ የሚያጋቡና እርስ በርሳቸው የሚጋጩ መረጃዎችን እያደረሱ ነው ብለዋል።

የጤና መረጃ እንደ ሌላው የንግድ ሥርዓት ከቁጥጥር ውጪ ሆኖ ሊሄድ አይችልም ያሉ ሲሆን የሚሰጡት መረጃዎች አጠራጣሪ ከሆኑ ስህተት ስለሚፈጥሩ ከወዲሁ ሊታረሙ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

የሚዲያ ባለሙያዎችም የጤና መረጃዎችን ለማኅበረሰቡ ሲያቀርቡ የሚቀርበውንና የማይቀርበውን ከመለየት ባሻገር፣ ስለሚቀርበው መረጃ ከሚመለከተው አካላት ጋር በመሆን ተዓማኒነቱንና ትክክለኛነቱን ማረጋገጥ እንዳለባቸውና ሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

" መረጃዎችን ለማድረስ ባለሙያ መሆን ብቻ በቂ አይደለም " ብለው መረጃ ሰጪው ለሚፈጠረው ችግርም ኃላፊነትን መውሰድ የሚችል መሆን አለበት ብለዋል፡፡

የማይድኑ በሽታዎችን " እናድናለን፣ እንፈውሳለን " የሚሉ ራሳቸውን ከሌሎች የተለየ ብቃትና ክህሎት እንዳላቸው በማስመሰል በማኅበረሰቡ ውስጥ ውዥንብር የሚፈጥሩ አካላት ተበራክተዋል ያሉ ሲሆን ተገልጋዮችን ለአላስፈላጊ ወጪና ጉዳት የሚዳርጉ በመሆናቸው በሕግና በማዕቀፍ ሊመሩ እንደሚገባ አብራርተዋል፡፡

በተለይ ካለፉት ጥቂት ወራት ወዲህ ብዙ አዳዲስ ልምዶች መስተዋላቸውን ተናግረው ' ቲክቶክ ' በተባለው ማኅበራዊ የሚዲያ አውታር በርካታ ባለሙያዎች የተለያዩ መረጃዎችን ለማኅበረሰቡ እያደረሱ እንደሆነ ገልጸዋል።

የሚሰጡት መረጃ የተገልጋይን መብትና ግዴታ ያላከበረና ተገልጋዩን ለገበያ የሚያውሉ ሕገወጥ ተግባራትን የሚያባብሱ ልምዶች መሆናቸውን አሳውቀዋል።

በዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን በአንድ ጊዜ ለመቆጣጠር መሞከር ለጤናው ዘርፍ ከፍተኛ ፈተና የሚደቅን በመሆኑ፣ በሒደት በማስተማርና በማሻሻል ሚዛኑን የጠበቀ ቁጥጥር ለማድረግ የባለድርሻ አካላት ዕገዛ እንደሚያስፈልግ አክለዋል፡፡

ቀደም ሲል የጤና ሥርዓቱን እየፈተነው የነበረው የመረጃ እጥረት ነበር ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት ደግሞ መረጃዎች ከአቅም በላይ እየሆኑ ተዓማኒነታቸው ያልተረጋገጠ ስለሚሆን፣ በቀጣይ ችግሩን የሚቃኝና ከመረጃ ሥርዓቱ እስከ አገልግሎት አሰጣጡ የሚያሻሽል፣ እንዲሁም ተጠያቂነት የሚያሰፍን መመርያ እየተዘጋጀ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ግለሰቦች ሚዲያ በመጠቀም በባህላዊም ሆነ በሃይማኖታዊ መንገድ ታማሚዎች የጀመሩትን መድኃኒት እንዲያቆሙና እንዲሞቱ፣ እንዲሁም ቤተሰብ እንዲበተን እያደረጉ እንደሆነ ተናግረው ይህ ከባድ ወንጀል መሆኑን ማወቅ ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡

ከዚህ ባሻገር አንዳንድ የጤና ተቋማት የሌላቸውን የሕክምና መሣሪያ እንዳላቸው በማስመሰል ሚዲያውን ተጠቅመው ተገልጋዮችን የማታለልና የማጭበርበር ድርጊት እንደሚፈጽሙ ጠቁመዋል፡፡

ይህንንና መሰል ተግባራትን ሲያከናውኑ የተገኙ የጤና ተቋማት የማሸግና ከሥራ የማገድ ቅጣት እንደተጣለባቸው አሳውቀዋል።

#ሪፖርተርጋዜጣ

@tikvahethiopia
👏460174🕊45🤔33🙏27😡22😢21🥰17😭17😱7
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ የገቢ ግብር ምጣኔ ላይ ማሻሻያ ለማድረግ መንግስት ረቂቅ አዋጅ ማዘጋጀቱን ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል። ሬድዮ ጣቢያው ከገንዘብ ሚኒስቴር አገኘሁት ባለው መረጃ በደመወዝተኛው ሆነ በንግድ የገቢ ግብር ምጣኔ ላይ ማሻሻያዎችን የያዘ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቷል። በመጭው ሰኞም በረቂቅ አዋጁ ላይ ከባለሙያዎች ጋር ለመመካከር ጥሪ ማድረጉ ተሰምቷል። የኢትዮጵያ ሰራተኞች ኮንፌዴሬሽንና…
#ኢትዮጵያ

የሠራተኞች መነሻ የደመወዝ ወለል 8,384 ብር እንዲሆን ተጠይቋል።

ወርኃዊ ደመወዛቸው እስከ 8,384 ብር የሆነ ሠራተኞች ከግብር ነፃ እንዲሆኑ የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) ለመንግሥት ጥያቄ ማቅረቡን ገለጸ፡፡

የኢሠማኮ ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጡት ቃል ፥ " ወርኃዊ ደመወዛቸው እስከ 8,384 ብር የሆነ ተቀጣሪ ሠራተኞች ከግብር ነፃ እንዲደረጉ ለመንግሥት ጥያቄ አቅርበናል " ብለዋክ።

የገንዘብ ሚኒስቴር ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት በሥራ ላይ ቆይቷል የተባለውን የገቢ ግብር አዋጅ 979/2008ን ለማሻሻል ጉዳዩ ይመለከታቸዋል ከተባሉ ባለድርሻዎች ጋር ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ እስከ ሁለት ሺሕ ብር የሚከፈለቸው ሠራተኞች ከግብር ነፃ እንዲሆኑ ተደንግጓል፡፡

ኢሠማኮ እስከ 8,384 ብር ድረስ የሚከፈለቸው ተቀጣሪዎች ከግብር ነፃ እንዲሆኑ ለገንዘብ ሚኒስቴር በደብዳቤ እንደጠየቀ አስታውቋል፡፡

አቶ ካሳሁን በዓለም ባንክ መረጃ መሠረት ዕለታዊ ገቢው ከሦስት ዶላር በታች የሆነ ሰው ደሃ በመሆኑ፣ የመንግሥት የገቢ ግብር በዚህ ወለል ሥር ያሉ ተቀጣሪዎችን ታሳቢ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል፡፡

በማናቸውም ቀጣሪ ተቋማት የሚሠሩ ሠራተኞች በወር ከ8,384 ብር እስከ 22,974 ብር ደመወዝ የሚያገኙ ሠራተኞች፣ አሥር በመቶ ግብር እንዲጣልባቸው መንግሥትን መጠየቁን ኢሠማኮ ገልጿል፡፡

ከ22,975 እስከ 44,530 ብር ወርኃዊ ደመወዝ ተከፋዮች የ15 በመቶ፣ ከ44,531 እስከ 72,336 ብር የሚከፈለቸው ደግሞ 20 በመቶ፣ እንዲሁም ከ72,337 እስከ 107,449 ብር የ25 በመቶ ግብር እንዲጣልባቸው ኢሠማኮ በደብዳቤው አሳስቧል።

ከ107,450 እስከ 150,107 ብር ድረስ የሚከፈለቸው ሠራተኞች 30 በመቶ ግብር፣ እንዲሁም 150,108 ብር እና ከዚያ በላይ የሚከፈለቸው ተቀጣሪ ሠራተኞች ደግሞ 35 በመቶ ግብር እንዲከፍሉ ለመንግሥት ባቀረበው ደብዳቤ ኢሠማኮ መጠየቁን ገልጿል።

አሁን በሥራ ላይ ባለው የሠራተኞች የገቢ ግብ አዋጅ መሠረት እስከ 600 ብር ድረስ የሚከፈላቸው ሠራተኞች ከግብር ነፃ ሲሆኑ፣ ከ10,900 ብር ጀምሮ ደግሞ 35 በመቶ ግብር እንዲከፍሉ ይገደዳሉ፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴር ከአንድ ሳምንት በፊት ለውይይት ይፋ ባደረገው የገቢ ግብር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ 1,200 ብር፣ 1,600 ብር እና 2,000 ብር ወርኃዊ ደመወዝተኞች ከግብር ነፃ እንዲደረጉ ድንጋጌ መኖሩ ይታወሳል።

የመንግሥት የገቢ ግብር ማሻሻያው ሠራተኞች ያለባቸውን ወቅታዊ የኢኮኖሚ ሁኔታ ታሳቢ ያላደረገ እንደሆነ የተለያዩ የውይይት ተሳታፊዎች አስተያየት መስጠታቸው አይዘነጋም፡፡

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።

#ሪፖርተርጋዜጣ

@tikvahethiopia
3.78K👏674🙏169😭76😡47🕊45🥰36🤔36😱22😢11💔9