TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63K photos
1.61K videos
216 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ህጻናት ፣ እናቶች፣ አሮጊቶች ፣ ሽማግሌዎች ተነስታ መሮጥ የማትችል አራስ እናት ሳትቀር ነው የተገደለችው " - ነዋሪዎች

በኦሮሚያ ክልል፣ ምስራቅ ሸዋ ዞን ከመቂ ከተማ 18 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ታጣቂዎች በርካታ ሰዎችን መግደላቸው ተሰምቷል።

በጉዳዩ ላይ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡ ነዋሪ ፥ " ድርጊቱ የተፈጻመው በሸኔ ታጣቂዎች ነው። እጅግ በጣም አሳዛኝ ልብን የሚሰብር ነገር ነው የተፈፀመው " ብለዋል።

ቦታው በኦሮሚያ ክልል፣ ምስራቅ ሸዋ ዞን ፣ ዱግዳ ወረዳ ኩሬ፣ ጋሌ፣ ቢቂሲ የሚባሉ ቀበሌዎች እንደሆነና ቦታው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ እንደሚዋሰን ጠቁመዋል።

" ድንገት ምሽት ላይ ነው ግድያው የተፈጸመው። በወቅቱ ከባድ ዝናብ ይዘብ ነበር " ብለዋል።

" ድንገተኛ ስለነበረ ማሳ ውስጥ ሲሮጥ በተባራሪ ጥይት የተመታ አለ ፤ በቆሎ ውስጥ ያልተነሳ ሬሳ አለ፣ ተቃጥሎ መለየት ያልተቻለ ሬሳ አለ ፤ እስካሁን ባለው 44 ሰው እንደሞተ ነው የሰማነው " ሲሉ ገልጸዋል።

" ግድያው ምሽት በድንገት ነው የተፈጸመው። ከሟቾቹ 80% የሚሆኑ ማምለጥ የማይችሉ ህጻናት፣ አሮጊቶች ፣ ሴቶች ፣ ሽማግሌዎች ናቸው " ብለዋል።

" ህጻናት ናቸው የተገደሉት ፣ አሮጊቶች ናቸው ፤ ተነስታ መሮጥ የማትችል አራስ እናት ሳትቀር ነው የተገደለችው " ሲሉ አክለዋል።

ግድያ ብቻ ሳይሆን ማቃጠልም ሲፈጽሙ ነበር።

" በወቅቱ የመንግሥት ኃይል አልነበረም። ከምሽት 2 ሰዓት አንስቶ እስከ ለሊት 8 ሰዓት ነው የዘለቀው። አብዛኛው የመንግስት ፀጥታ ኃይል መቂ ነው ያለው " ብለዋል።

ግድያ በተፈጸመባቸው ስፍራዎች ላይ በወቅዩ ግጭት እንዳልነበረም ጠቁመዋል።

" የአካባቢው ሰው በታጣቂዎች ጥቃት ብዙ ተሰቃይቷል። መጨረሻ ሲደክመው እነሱን (ታጣቂዎቹን) ማዳመጥ አቆመ ፤ ከዛም በጎጥ እየተደራጀ ሰፈሩን መጠበቅ ጀመረ ፤ ታጣቂዎቹ ከጠፉ ከ6 ወር በኃላ አዘናግተው ነው አሁን መጥተው ግድያው ያፈጸሙት " ብለዋል።

በአጋጣሚ ከባድ ዝናብ ስለነበር ሰውም ወጥቶ አካባቢውን የሚጠብቅበት ሁኔታ እንዳልነበርና (ቤት ውስጥ እንደበር) በዚህ መሃል ሰብረው ገብተው ግድያውን እንደፈጸሙ ተናግረዋል።

" ያለ ርህራሄ ፣ ያለ ልዩነት ሲገድሉ የነበረው ነዋሪውን ነው " ብለዋል።

በሌላ በኩል ፤ ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ቃላቸውን የሰጡ ተጎጂ አይን እማኞች ረቡዕ ከምሽት ጀምሮ እስከ ለሊት በዘለቀ ጥቃት ህጻናትን ጨምሮ እናቶች እና አረጋዊን በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል ብለዋል።

አንድ ተጎጂ በሶዶ ወረዳ አዋሳኝ የደረሰው አስከፊ ጉዳት እንደሆነ ገልጸዋል።

" ሰው መግደል ፣ ማቃጠል ነው። ' የኛን ሃሳብ ለምን አልተከተላችሁም ለምን ከመንግስት ጋር ትሆናላችሁ ' የሚል ነው። ገበሬው ሸኔ ከሚባለው ብዙ ጊዜ ጥቃት ስለደረሰበት እራሱን ለመከላከል እየተደራጀ ነበር። መሳሪያም ይዞ፣ መንግሥትም እያበረታው እራሱን ለመከላከል እንቅስቃሴ ያደርግ ነበር። እየወጣም ይጠብቅ ነበር። ያንን በመቃወም ነው ጥቃቱ " ብለዋል።

" ብዙ ጊዜ ሰው ይታገታል ገንዘብ ይጠየቃል፣ ብዙ ሰው ተሰቃይቶ ከስፍራው ለቋል ፣ መንገድም ዘግተው ቆይተዋል (ታጣቂዎቹ) " ሲሉ አክለዋል።

የአሁኑ ጥቅት ግን እጅግ በጣም የከፋና ከዚህ በፊት ያልታየ እንደሆነ አክለዋል።

" በብዙ አቅጣጫ ሆነው ይገባሉ ቤት ከውጭ ይዘጋሉ እሳት ይለኩሳሉ ለማምለጥ የሚሮጠውን በጥይት ነው ሲመቱ የነበረው የተቀበረው ብቻ 40 አካባቢ ነው ፤ 4 ፣ 5 ቤተሰብ ነው ሲቀበር የነበረው " ብለዋል።

ከሰው እልቂት ባለፈም እንስሳት ተቃጥለዋል ፤ በርካታ ንብረት ወድሟል።

ነዋሪው ሌላ ጥቃት እንዳይፈጸም በመስጋት ከቦታው እየወጣ እንደሆነ የአይን እማኙ ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።

#TikvahEthiopiaFamily #ዶቼቨለ

@tikavhethiopia
😭2.66K😡204158😢94🕊72🙏29😱25🥰13🤔5👏2
አንጋፋው ጋዜጠኛ ዜናነህ መኮንን ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

አንጋፋው ጋዜጠኛ ዜናነህ ፥ በኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቭዥን እንዲሁም በዴቼ ቬለ ሬድዮ ለረዥም ዓመታት አገልግሏል።

ጋዜጠኛ ዜናነህ ለረዥም ጊዜያት ባደረበት ህመም ህክምናውን ሲከታተል ከነበረበት እስራኤል ቴል አቪቭ ዛሬ ጠዋት ኣፏል።

በስልሳ ስምንት ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው አንጋፋው ጋዜጠኛ ዜናነህ አዘዞ ጎንደር ነው የተወለደው።

ከ1970ዎቹ እስከ ሰማኒያዎቹ አጋማሽ ድረስ በኢትዮጵያ ራዲዮ እና ቴሌቪዥን ድርጅት በተለይ በዜና አንባቢነት አገልግሏል።

በ1980ዎቹ አጋማሽ ወደ እስራኤል ያቀናው ዜናነህ በህመም ተዳክሞ ከሥራው እስኪርቅ ድረስ በኢየሩሳሌም የዶቼ ቬለ ራዲዮ ዘጋቢ በመሆን ሲያገለግል ቆይቷል።

" ይህ ዶቼ ቨለ ነው !! " ከሚለው የዲቼቬለ ሬድዮ ጣቢያ መለያ አንስቶ የተለያዩ ዝግጅቶች መክፈቻም የአንጋፋው ጋዜጠኛ ድምፅ ነው።

የዶቼ ቬለ አድማጮች ዜናነህን ከመካከለኛው ምስራቅ በእስራኤል አረብ ግጭት እና ጦርነቶች ብሎም በቀጣናው በሚነሱ ፖለቲካዊ ዘገባዎች ያውቁታል።

የዜናነህ መኮንን የቀብር ሰነ ስረዓት ቴል አቪቭ ውስጥ በሚገኝ ፓርክ ያኮም መካነ መቃብር እንደሚፈጸም ልጁ ቢታንያ ዜናነህ ገልጻለች።

ዜናነህ ባለትዳር እና የሶስት ሴቶች ልጆች አባት ነበር።

#ዶቼቨለ

@tikvahethiopia
😭1.68K237🕊222😢190🙏75👏42😱29🥰28😡17🤔16