TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ዴሞክራሲ 👏 #ሶማሌላንድ

" የምርጫ ውጤቱን እንቀበላለን " - ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ

ባለፈው ሳምንት በራስ ገዟ ሶማሌላንድ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ መደረጉ ይታወሳል።

በከፍተኛ ብልጫም የተቃዋሚው ዋደኒ ፓርቲ መሪ አብዲራህማን ሞሐመድ አብዱላሂ " ኢሮ " ምርጫውን አሸንፈዋል።

በምርጫው የተሸነፉት ተሰናባቹ ፕሬዜዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ " የምርጫውን ውጤት እንቀበላለን " ብለዋል።

ተመራጩ ፕሬዜዳንትንም " እንኳን ደስ አልዎት ! " ብለዋቸዋል።

" ባስመዘገቡት ድል እንኳን ደስ አልዎት " ያሉት ፕሬዜዳንት ቢሂ " ሰላማዊና የተረጋጋ የስልጣን ሽግግር እንዲደረግ ለማድረግ የተሟላ ድጋፌን አደጋለሁ  " ሲሉ ቃል ገብተዋል።

" የአገልግሎት ዘመንዎ ሰላምን ፣ እድገትን እና ዘላቂ ስኬትን ለሀገራችን እንዲያመጣ እመኛለሁ " ብለዋል።

ተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ቢሂ ለህዝቡ ባስተላለፉት መልዕክት " ፕሬዝዳንታችሁ ሆኜ እንዳገለግላችሁ ዕድሉን ስለሰጣችሁኝ አመሰግናለሁ " ሲሉ ገልጸዋል።

" የስልጣን ዘመኔ ማብቂያ ላይ ሆኜ የምለው ነገር ለሀገራችን እድገት ያለኝ ቁርጠኝነት ጸኑ መሆኑን ነው " ሲሉ አክለዋል።

" በአንድነት እና በጋራ ተነስተን ለሶማሌላንድ ብልፅግና እንስራ " ብለዋል።

6ኛው የሶማሌላንድ ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡት አብዲራህማን ኢሮ " ማንም ተሸናፊ ማንም አሸናፊ የለም ያሸነፈው የሶማሌላንድ ህዝብ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

ሶማሌላንድ እራሷን እንደ ሉዓላዊ ሀገር ምትቆጥር ናት። ከሶማሊያ መንግሥት ጋርም ግንኙነት የላትም። ላለፉት በርካታ ዓመታት ራሷን በራሷ እያስተዳደረች ነው።

እጅግ ሰለማዊ ፣ የተረጋጋ ፣ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ በማድረግ እና ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር በማድረግ ትወደሳለች።

#TikvahEthiopia #ቲክቫህኢትዮጵያ
#Somaliland

@tikvahethiopia
👏2.06K210🙏60🕊52🥰20🤔17😱12😭9😡9😢5