TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#IOM
አስከፊው የስደት ጉዞ የበርካቶችን ህይወት እየቀጠፈ ነው።
በቅርቡ በየመን አብያን ግዛት 154 ኢትዮጵያውን ስደተኞችን ጭና የነበረች ጀልባ በመስጠሟ የ68 ሰዎች ህይወት አልፎ አስክሬን መገኘቱ፣ 12 ሰዎች በህይወት መትረፋቸው የቀሩት 74 ሰዎች የደረሱበት እንደማይታወቅ ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) ማሳወቁ ይታወሳል።
ይህ አሰቃቂ አደጋ ከደረሰ በኃላ ደግሞ ከሶማሊያ ቦሳሶ 250 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን የጫነች ጀልባ ከትላንት በስቲያ ደቡብ የመን አርቃህ የተባለ ስፍራ ደርሳለች።
155ቱ ወንዶች እና 95ቱ ሴቶች ሲሆኑ ከነዚህ ውስጥ 82ቱ ህጻናት ናቸው።
ጀልባዋ በባህር ተጉዛ መድረስ የነበረባት በ24 ሰዓት እንደነበር ቢገመትም 7 ቀን ፍጅቶባታል። ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ጀልባዋ ባህር ላይ የሞተር ብልሽት ገጥሟት እንደሆነና አጠቃላይ ጉዞው በቀዘፋ እና ንፋስ ላይ የተንተራሰ እንዲሆን አድርጎታል።
በዚህ ፈታኝ እና አስፈሪ ጉዞ ላይ የ7 ሰዎች ህይወት በረሃብ እና ውሃ ጥም ጠፍቷል።
በህይወት ለተረፉት የምግብ እና የውሃ አቅርቦት እንዲሁም የህክምና ድጋፍ እንዳደረገ የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) አመልክቷል።
#YEMEN
#IOM
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia

😭2.32K❤872💔183😢94🙏58🕊42😱10👏8🤔5😡5🥰2