" አገሮች የአስተናጋጅ አገርን ሕግ አክብረው እንዲንቀሳቀሱ ይጠበቃል " - ገንዘብ ሚኒስቴር
ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላት ከአሁን በኃባ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ብቻ እንዲያስገቡ ማሳሰቢያ ተላልፏል።
ገንዘብ ሚኒስቴር ፥ የዲፕሎማሲና የቆንስላ አገልግሎት የሚሰጡ ቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ ተቋማት፣ ወደ አገር ውስጥ የሚያስገቧቸው ተሽከርካራች የኤሌክትሪክ ብቻ መሆን እንዳለባቸው አስታውቋል፡፡
ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመታገል በምታደርገው ቁርጠኝነት በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎችን ማስገባት የተከለከለ እንደሆነ ነው ሚኒስቴሩ ያሳውቀው።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ምን አሉ ?
" ይህንን ውሳኔ በርካታ የአውሮፓ አገሮች የሚደግፉት ሐሳብ ነው።
አገሮች የአስተናጋጅ አገርን ሕግ አክብረው እንዲንቀሳቀሱ ይጠበቃል።
ውሳኔው የዲፕሎማሲ ሥራን ለመሥራት የሚያውክና የአገሮችን ሉዓላዊነትን የሚጥስ ባለመሆኑ፣ እንደ እነዚህ ዓይነት ሕጎች ሲወጡ ዲፕሎማቶች ያንን ሕግ አክብረው መንቀሳቀስ ይጠበቅባቸዋል፡፡ "
ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ 38 የገቢ ንግድ ምርቶች ዕግድ እንዲነሳላቸው ባሳለፈው ውሳኔ ቢያሳውቅም የገንዘብ ሚኒስቴር ግን በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች ላይ ዕግዱ እንደማይነሳ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡ #EthiopianReporter
@tikvahethiopia

❤282🤔74😡59👏26🕊15😢11😱8🙏7😭4🥰3