TIKVAH-ETHIOPIA
#ወላይታዞን “ ከ1,000 በላይ መምህራንና የቢሮ ሠራተኞች የሐምሌ ደመዎዝ አልተከፈለንም ” - የወላይታ ዞን መምህራን “ በአራት ወረዳዎች ሙሉ ደመወዝም ሳይሆን የተወሰነ እየተከፈለ ነው ” - የዞኑ ትምህርት መምሪያ በወላይታ ዞን የሚገኙ መምህራን የሐምሌ 2016 ዓ/ም ደመወዝ እንዳልተከፈላቸው፣ በዚህም የትምህርት ሥራ ሙሉ ለሙሉ እንዳልተጀመረ መምህራኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። ክፍያ አለመፈጸሙን…
በወላይታ ዞን መምህራን በፖሊስ እየታሠሩ መሆኑን የታሳሪ ቤተሰቦች ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ገልጸዋል።
እስሩ የተፈፀመ ያለድ መምህራኑ ከደሞዝ ጥያቄ ጋር በተያያዘ ፊርማ በማሰባሰብ ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አቤቱታቸውን ለማስገባት መንቀሳቀሳቸውን ተከትሎ ነው ተብሏል።
ፖሊስ መምህራኑን የሚያስረው " አመፅ ለመቀስቀስ ተንቀሳቅሰዋል፤ የዞኑን ገጽታ አጥፍተዋል " በሚል መሆኑን የታሳሪ ቤተሰቦች ተናግረዋል።
መምህር ዳንኤል ፋልታሞ በዳሞት ወይዴ ወረዳ በከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ በእንግሊኛ ቋንቋ መምህርነት በማገልገል ላይ ይገኛሉ።
መምህሩ በዞኑ ፖሊስ አባላት እስከታሠሩበት እስካለፈው ሰኞ ድረስ የመምህራን ደሞዝ እንዲከፈል ለመጠየቅ ፊርማ በማሰባሰብ ላይ እንደነበሩ የሚያውቋቸው የስራ ባልደረቦቻቸው ገልጸዋል።
መምህሩን ሌሊት ፖሊሶች ከቤት ይዘዋቸው እንደሄዱ ነው የ3 ልጆች እናት የሆኑት ባለቤታቸው ለሬድዮ ጣቢያው የጠቆሙት።
ፖሊሶች ሌሊት 9 ሰዓት ላይ ወደ ቤት እንደመጡ የጠቀሱት የመምህሩ ባለቤት " በወቅቱ ምንም የተፈጠረ ነገር አልነበረም። ቤተሰቡ በሙሉ በእንቅልፍ ላይ ነበር። ቤቱን አስከፍተው ከገቡ በኋላ አልጋ እና ፍራሽ ሳይቀር ፈትሸው ምንም ሊያገኙ አልቻሉም። በመጨረሻም ግን ባለቤቴን ይዘውት ሄዱ " ብለዋል።
ለደህንነታችን ሲባል ስማችን አይጠቀስ ያሉ ሌላ ሁለት የዚሁ ወረዳ ነዋሪዎች ባሎቻቸው ደሞዝ ይሰጠን ብለው የዳቦ ጥያቄ በማንሳታቸው ብቻ ታሰረውብናል ብለዋል።
" ፖሊሶች ወደ ቤት ሲመጡ ምንም አይነት የፍርድ ቤት መያዣ ወረቀት አላሳዩም " ያሉት የመምህራኑ ቤተሰቦች " የተሳሳተ መረጃ አሰራጭታችኋል " በሚል መያዛቸውን ከአንድ ፖሊስ አባል መስማታቸውን ተናግረዋል።
" የመምህራን ደሞዝ ይከፈል " በሚል የፊርማ ማሰባሰብ ስራ ሲያከናውኑ ከነበሩት መካከል 3 በቅርብ የሚያውቋቸው መምህራን መታሰራቸው የተናገሩ አንድ የዳሞት ወይዴ ወረዳ መምህር አስተባባሪዎቹ ከመታሠራቸው በፊት " እረፉ " የሚል መልዕክት ከወረዳው አመራሮች ተልኮባቸው እንደነበር ጠቁመዋል።
የወረዳው እና የዞን ኃላፊዎች ለቀረበው ክስ ምላሽ አልሰጡም።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት ሰብሳቢ አቶ አማኑኤል ጳውሎስ ለሬድዮ ጣቢያው ፤ " መምህራን ደሞዝ የመጠየቅ መብት መንግሥትም የመክፈል ግዴታ አለበት። የደሞዝ ጥያቄ በማቅረባቸው እሥርና ማስፈራሪያ ደርሶባቸዋል የሚል መረጃ እስከአሁን እኛ አልደረሰንም። ነገር ግን ድርጊቱ ተፈጽሞ ከሆነ ትክክል አይደለም። እኛም የምንታገለው ይሆናል " ብለዋል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ነው።
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😡852😭216❤111😢34🤔23😱19👏13🕊12🥰11🙏4
" ከቤት ኪራይ እና ከዕለት ፍጆታ ተርፎ ቤት ለማግኘት 25 በመቶ መቆጠብ አንችልም " - መምህራን
🔴 " ዘጠኝ እና አስር ዓመት የስራ ልምድ ያለው መምህር 10 ሺህ ብር ገደማ ደመወዝ ነው የሚከፈለው ! "
➡️ " መቆጥብ ለማይችሉት የኪራይ ቤት ገንብቶ ለመስጠት እየተሰራ ነው " - ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ
ከሰሞኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንግድ ባንክ ጋር መምህራንን ጨምሮ በከተማዋ የሚገኙ የመንግሥት ሠራተኞችን የቤት ተጠቃሚ ያደርጋል የተባለ ስምምነት ተፈራርመው ነበር።
ስምምነቱ በአነስተኛ የወለድ መጠን በ25/75 የብድር መርሐ ግብር የሚከናወን ሲሆን 25 በመቶውን መንግሥት ሰራተኛ ይቆጥባል 75 በመቶ የባንክ ብድር ይቀርባል። ብድሩ በ20 ዓመታት የሚከፈል ነው።
ንግድ ባንክ 120 ቢሊዮን ብድር እንደሚያቀርብም ተገልጾ ነበር። ፕሮጀክቱ 3 ዓመት የግንባታ ጊዜ አንድ አመት የብድር መክፈያ እፎይታ አለው ነው የተባለው።
ነገር ግን መምህራን ይህ የተባለውን 25 በመቶ ቁጠባ የመቆጠብ አቅም እንደሌላቸው ተናግረዋል።
በአዲስ አበባ የመምህራን ስብሰባ ላይ የተገኙ መምህራን " የተፈራረመው የመምህራን የቤት ቁጠባና ብድር አገልግሎት ጥሩ ቢሆንም በስምምነቱ መሰረት 25 በመቶ ቁጠባ የመቆጠብ አቅም የለንም " ብለዋል።
መምህራኑ " በኑሮ ጫና ምክንያት 25 በመቶ መቆጠብ አንችልም " ሲሉ ተናግረዋል።
" ዘጠኝ እና አስር ዓመት የስራ ልምድ ያለው መምህር 10 ሺህ ብር ገደማ ደመወዝ ነው የሚከፈለው ፤ ከዚህ ደመወዝ ላይ ለቤት መሥሪያ የሚሆን 25 በመቶ ሊቆጥብ አይችልም ፤ ሌላ አማራጭ ሊዘረጋ ይገባል " ሲሉ ጠይቀዋል።
መምህራኑ ከቤት ኪራይና ከዕለት ፍጆታ ተርፎ ቤት ለማግኘት 25 በመቶ የመቆጠብ አቅም እንደሌላቸው ገልጸው " ሌላ መፍትሄ ይፈለግልን " ብለዋ።
ለመምህራኑ ጥያቄ ምላሽ የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፥ " መምህራን ያነሷቸ የቤት ጥያቄዎች ትክክልና ተገቢ ናቸው " ብለዋል።
" መምህራን ከዚህ በፊት በነበረ ስብሰባ ያነሱት ጥያቄ ' ለቤት ግንባታ የሚውል በነፃ መሬት ስጡን ' የሚል ነበር ፤ በተጨማሪም ' የብድር አገልግሎት አመቻቹልን ' የሚል ጥያቄ ነበር በዚህም ብድሩ ተመቻችቷል " ሲሉ አብራርተዋል።
" 25 በመቶ መቆጠብ የሚችሉ እንዲቆጥቡ እና 75 በመቶ የብድር አገልግሎት እንዲያገኙ የማድረግ ዕድል ተመቻችቷል " ያሉት ከንቲባዋ " መቆጥብ ለማይችሉት የኪራይ ቤት ገንብቶ ለመስጠት እየተሰራ ነው " ሲሉ ተናግረዋል። #ኢፕድ
#መምህራን

😭524❤168👏122😡61💔29🤔14🙏11😱10😢10🕊6🥰5