TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#EMA
" የጉዳዩ አሳሳቢነት እየጨመረ በመምጣቱ የሚመለከተው አካል አፋጣኝ መፍትሔ ይስጥበት ! " - ማኅበሩ
የኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር ምን አለ ?
የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር ዛሬ መግለጫ አውጥቷል።
በዚህም መግለጫው በአሁን ሰዓት በተወሰኑ የጤና ተቋማት በከፊል የጤና አገልግሎት እየተስተጓጎለ መሆኑን እንደሰማ ገልጿል።
በመሆኑም ማህበሩ ትኩረት ይሻሉ ያላቸውን ጉዳዮች በመዘርዘር የሚመለከተዉ አካል ትኩረት እንዲሰጥበት ጥሪ አቅቧል።
1. ሃኪሞች በሚያነስዋቸው ጥያቄዎች ማለትም ፦
• የደመወዝ ማነስ፣
• የጥቅማጥቅም፣
• የስራ ቦታ ደህንነት እንደ ኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር ተገቢ መሆኑን እንደሚቀበልና ለረጅም ጊዜያት ለሚመለከተው ባለድርሻ አካል ጉዳዩን ሲያቀርብ እና ሲሰራበት እንደቆየ ገልጿል። በአሁኑ ሰዓት ግን የጉዳዩ አሳሳቢነት እየጨመረ በመምጣቱ የሚመለከተው አካል አፋጣኝ መፍትሔ እንዲሰጥበት ጥሪ አቅርቧል።
2. አሁን ያለዉ ሁኔታ ማለትም የጤና አገልግሎቱ እንዲሁም የመማር ማስተማር ሂደቱ በምንም አይነት ደረጃ ቢሆን መስተጓጎሉ ማህበረሰቡን፤ የጤና ባለሞያዉን እንዲሁም የጤና ስርአቱን እጅግ ሊጎዳ የሚችል በመሆኑ ይህ ጉዳይ ወደተባባሰ ደረጃ ከመድረሱ በፊት የጤና ሚኒስቴርና የሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት ከባለሙያዎች ጋር በመሆን አፋጣኝ የሆነ ሃገራዊ ዉይይት በየደረጃዉ እንዲያካሂዱ እና ችግሮቹ በዉይይት እንዲፈቱ እንዲደረግ ማኅበሩ ጥሪ አቅርቧል።
3. ሃኪሞች እንዲሁም የጤና ባለሙያዎች አሁን ካለው ሁኔታ ጋር ተያይዞ በተለያዩ ቦታዎች ለእስር እንደተዳረጉ መሆኑን በመግለጭ ባለሞያዎቹ ከእስር እንዲፈቱ እና ወደስራ ገበታቸዉ ተመልሰዉ ለማህበረሰቡ አገልግሎቱን እንዲሰጡ ቢደረግ የተሻለ እንደሆነ እና በዚህ ረገድ የሚመለከታቸዉ አካላት አስፈላጊዉን እገዛ እንዲያደርጉ አሳስቧል።
4. ማኅበሩ ችግሮችን ለመፍታት እና መፍትሄ ለመስጠት ከጤና ሚኒስቴርም ሆነ ባለድርሻ አካላት በሚያደርጓቸዉ ጥረቶች አብሮ ለመስራት እና ትብብሩን አጠናክሮ በመቀጠል የመፍትሄዉ አካል ለመሆን ፈቃደኛ እና ዝግጁ እንደሆነ አሳውቋል።
ኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር፥ በአገሪቱ ሃኪሞች እንዲሁም የጤና ባለሙያዎች የሚነሱ ጥያቄዎችን አስመልክቶ ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት የተለያዩ የሙያ ማህበራትን እና ስፔሻሊቲ ሶሳይቲዎችን በማስተባበር ዉይይት በማድረግ እንዲሁም ሙያ ማህበራቱ ከጤና ሚኒስቴር ጋር ተከታታይ ውይይቶች እንዲያደረጉ በማመቻቸት ጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጠዉና አስቸኳይ መፍትሄ እንዲቀመጥ ጥረት ሲያደርግ እንደቆየ አስታውሷል።
NB. ቲክቫህ ኢትዮጵያ የደብዳቤውን ትክክለኝነት ከማኅበሩ አረጋግጧል።
#EMA
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia

🙏911😡353❤163👏80😭28🕊26😢23🥰16😱14🤔3💔2