TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#DV2026 የ2026 የአሜሪካ ዳይቨርሲቲ ቪዛ (DV) ማመልከቻ ከዛሬ ጀምሮ ክፍት ተደርጓል። ለ2026 DV ለማመልከት https://dvprogram.state.gov/ ይጠቀሙ። ለማመልከት ምንም አይነት ክፍያ አያስፈልግም። ማመልከቻው እስከ ህዳር 5 /2024 ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል። ከፍተኛ የመሙላት ፍላጎቶች ድረገጹ ላይ መዘግየቶችን ሊያስከትል ስለሚችል ለመሙላት እስከ የምዝገባው ጊዜ የመጨረሻ…
#DV2026

የአሜሪካ ዲቪ ሎተሪ (Diversity Visa) 2026 አሸናፊዎች ቅዳሜ ሚያዚያ 25/2017 ዓ/ም ይፋ ይደረጋሉ።

ለዲቪ (Diversity Visa) 2026 ማመልከቻ የሞሉ በ dvprogram.state.gov ብቻ የማረጋገጫ ቁጥራቸውን በማስገባት ውጤቱን ወይም ማሸነፍ አለማሸነፋቸውን መመልከት ይችላሉ።

NB. የማረጋገጫ ቁጥር ማመልከቻው ሲሞላ የተሰጠ ነው። ይህ ቁጥር የጠፋበት Forgot Confirmation Number በማለት አስፈለጊ መረጃ በመሙላት በኢሜል አዲስ ቁጥር ማግኘት ይቻላል።

ለ2026 የፊስካል ዓመት እስከ 55,000 የሚደርስ የዳይቨርሲቲ ቪዛ (DV) ተዘጋጅቷል። ይህ ቁጥር ብቁ የሆኑ ሀገራትን ሁሉ የሚጠቃልል ሲሆን #ኢትዮጵያም አንዷ ናት።

የዲቪ ሎተሪ መውጫ መድረሱን ተከትሎ " የዲቪ (DV) ሎተሪ አሸንፋችኋል ፣ ከአሜሪካ ኤምባሲ ነው ምንደውለው / ይህን ኢሜል / ቴክስት የምንልከው " በማለት የሚያጭበረብሩ አካላት ስለሚኖሩ አመልካቾች ሊጠነቀቁ ይገባል።

አንድ አመልካች ዲቪ 2026 ደርሶት እንደሆነ እና እንዳልሆነ ማወቅ የሚችልበት ብቸኛው መንገድ ከላይ የተጠቀሰው ድረገጽ ብቻ ነው።

አሜሪካ በየዓመቱ ከአፍሪካ (ኢትዮጵያ ጨምሮ) ፣ እስያ ፣ አውሮፓ፣ ሰሜን አሜሪካ፣ ደቡብ አሜሪካ እና አውስትራሊያ 55 ሺህ ሰዎችን በዲቪ (DV) ሎተሪ ወደ ሀገሯ ታስገባለች።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvaEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
2.25K🙏1.24K🕊144👏114😭67🥰57🤔47💔46😱34😡31😢23
TIKVAH-ETHIOPIA
#DV2026 የአሜሪካ ዲቪ ሎተሪ (Diversity Visa) 2026 አሸናፊዎች ቅዳሜ ሚያዚያ 25/2017 ዓ/ም ይፋ ይደረጋሉ። ለዲቪ (Diversity Visa) 2026 ማመልከቻ የሞሉ በ dvprogram.state.gov ብቻ የማረጋገጫ ቁጥራቸውን በማስገባት ውጤቱን ወይም ማሸነፍ አለማሸነፋቸውን መመልከት ይችላሉ። NB. የማረጋገጫ ቁጥር ማመልከቻው ሲሞላ የተሰጠ ነው። ይህ ቁጥር የጠፋበት Forgot…
#DV2026

የአሜሪካ ዳይቨርሲቲ ቪዛ (DV) 2026 አሸናፊዎች ይፋ ተደረጉ።

የ2026 ዲቪ (DV) ሎተሪ ዛሬ ምሽት ይፋ ተደርጓል።

ለዲቪ /DV/ 2026 ማመልከቻ የሞሉ በ https://dvprogram.state.gov/ESC ብቻ የማረጋገጫ ቁጥራቸውን በማስገባት ውጤቱን / ማሸነፍ አለማሸነፋቸውን መመልከት ይችላሉ።

የማረጋገጫ ቁጥር ማመልከቻው ሲሞላ የተሰጠ ቁጥር ሲሆን ይህ ቁጥር የጠፋበት Forgot Confirmation Number በማለት አስፈለጊ መረጃ በመሙላት በኢሜል አዲስ ቁጥር ማግኘት ይቻላል።

" የዲቪ (DV) ሎተሪ አሸንፋችኋል፣ ከአሜሪካ ኢምባሲ ነው እምንደውለው / ኢሜይል / ቴክስት የምንልከው "  በሚል የሚያጭበረብሩ አካላት ስለሚኖሩ አመልካቾች ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል።

አሜሪካ በየዓመቱ ከአፍሪካ (ኢትዮጵያን ጨምሮ) ፣ እስያ ፣ አውሮፓ፣ ሰሜን አሜሪካ፣ ደቡብ አሜሪካ እና አውስትራሊያ 50 ሺህ ሰዎችን በዲቪ (DV) ሎተሪ ወደ ሀገሯ ታስገባለች።

ለ2026 የፊስካል ዓመት እስከ 55,000 የሚደርስ የዳይቨርሲቲ ቪዛ (DV) ተዘጋጅቷል። ይህ ቁጥር ብቁ የሆኑ ሀገራትን ሁሉ የሚጠቃልል ሲሆን #ኢትዮጵያም አንዷ ናት።

@tikvahethiopia
👏1.31K🙏524346😭193😢154💔120😡102🕊66🥰62😱40🤔36