TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.61K videos
217 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#አዲስ_አበባ 🚍 #ናይሮቢ

" ከናይሮቢ -
አዲስ አበባ ደርሶ መልስ የጉዞ ዋጋ 15 ሺህ የኬንያ ሽልንግ (16 ሺህ የኢትዮጵያ ብር ገደማ) ነው ! " - ሚካኤል ጄምስ ማቺዮ

➡️ " የመንገዱን ደኅንነት በተመለከተ ከሞያሌ መረጃ ወስደን ነው የምንሄደው። በኢትዮጵያ ድንበር ውስጥ በምሽት ጉዞ አናደርግም ቀን ብቻ ነው ባሱ የሚጓዘው !! "


" አቢሲኒያ ሌግዠሪ ኮች " የተሰኘ የትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢ ድርጅት ከኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ወደ አዲስ አበባ በአውቶብስ ተጓዦችን ማመላለስ መጀመሩን አስታወቀ።

ድርጅቱ ባለፈው ሳምንት እሁድ በይፋ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የድርጅቱ ዳይሬክተር ሚካኤል ጄምስ ማቺዮ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ዳይሬክተሩ ምን አሉ ?

" በአንድ ጉዞ 7 ሺህ 500 የኬንያ ሽልንግ ነው የምናስከፍለው። ለደርሶ መልስ ጉዞ ዋጋ 15 ሺህ የኬንያ ሽልንግ (16 ሺህ የኢትዮጵያ ብር ገደማ) ነው።

ከኛ በፊት 'ሮያል አላይድ' ተሰኘ ከናይሮቢ ሞያሌ እና ሞምባሳ የሕዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የተሰማራ ድርጅት አለ። ከአራት ዓመታት በፊት የተመሠረተው 'ሮያል አላይድ' እስከ ሞያሌ ብቻ ይሠራ ነበር።

በአውሮፕላን ቲኬት መወደድ ሳቢያ የአውቶብስ ትራንስፖርት ፍላጎት መኖሩን እና ይህንን ፍላጎት ሊያሟላ የሚችል አገልግሎት አቅራቢ አለመኖሩን በጊዜው ክፍተት ነበር።

ይህን ክፍተት ለመሙላት ነው ለምን ቀጥታ ከናይሮቢ- አዲስ አበባ ጉዞ አንጀምርም ብለን አቢሲኒያን የጀመርነው።

አሁን ላይ ስምንት ባስ ነው ያለን የእኛ ዕቅድ 16 መሆን አለበት የሚል ነው። ከ16ቱ ስድስት ባስ እዚያው ኢትዮጵያ እንዲሆኑ ነው የምንፈልገው እነሱን በጂቡቲ በኩል እናስገባለን።

በየቀኑ ወደ በናይሮቢ እና በአዲስ አበባ መካከል የሕዝብ ማመላለስ ሥራዎችን እንሰራለን።

ባለፈው ዕሁድ ሥራችንን በይፋ ስንጀምር 7 ተሳፋሪዎች ከናይሮቢ ወደ አዲስ አበባ ለመሄድ ትኬት ቆርጠው ነበር።

የእሁዱ የሙከራ ጉዞ ነበር፤ ነገር ግን በደንብ ማስታወቂያ ስላልተሠራ ቀጥታ የሚጓዙ ተሳፋሪዎች አልተገኙም።

ባሱ 46 ሰዎች የመያዝ አቅም ቢኖረውም ቀጥታ አዲስ አበባ የሚሄዱት ሰባት ሰዎች ብቻ ነበሩ። አብዛኞቹ ተሳፋሪዎች ሞያሌ ድረስ የሚሄዱ ነበጉ። ሰባቱን ሰዎች በሰላም ባስ ወደ አዲስ አበባ ሸኝተናቸዋል።

ሐሙስ ዕለት ወደ አዲስ አበባ የሚጓዘው አውቶብስ ግን ትኬት ተሽጦ አልቋል።

አውቶብሱ 46 ሰዎችን ብቻ እንዲጭን የተደረገበት ምክንያት ወንበሮች መካከል ክፍተት እንዲኖር እና ሰፋፊ ወንበሮችን ለመጠቀም ነው።

አውቶብሶቹ ፦
- አስተናጋጆች፣
- ራሳቸውን የቻሉ የሴቶችን እና የወንዶች መጸዳጃ፣
- በውስጣቸው የኢንተርኔት እና ስክሪንን ጨምሮ የመዝናኛ አግልግሎት አላቸው።

የጉዞ መስመር እና ሰዓትን በተመለከተ አውቶብሱ ከቀኑ 10 ሰዓት ከናይሮቢ ሚነሳ ሲሆን፣ በማግስቱ ጠዋት ሞያሌ ይደርሳል።

ኢሚግሬሽን እስከሚከፈት ተሳፋሪዎች ያርፋሉ። ኢሚግሬሽን ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ያልቃል። ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ተኩል ከሞያሌ፤ በያቤሎ፣ ቡሌ ሆራ፣ ዲላ፣ ሐዋሳ አድርጎ ከምሽቱ 1 ሰዓት ገደማ አዲስ አበባ ይገባል።

የፀጥታ ሁኔታውን በተመለከተ ዳይሬክተሩ ምን አሉ ?

" ይህ መስመር ከመጀመሩ በፊት በራሴ ከ10 ጊዜ በላይ ተመላልሻለሁ፤ በመንገዱ ላይ የፀጥታ ስጋት በእኔ ጉዞ አጋጥሞኝ አያውቅም።

ከዚህ በተጨማሪም የመንገዱን ደኅንነት በተመለከተ ከሞያሌ መረጃ ወስደን ነው የምንሄደው።

እንዲሁም በኢትዮጵያ ድንበር ውስጥ በምሽት ጉዞ አናደርግም ቀን ብቻ ነው የሚጓዘው። "

መረጃውን የወሰድነው ከቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት ነው።

#Ethiopia #Kenya
#AddisAbaba #Nairobi

@tikvahethiopia
2.2K👏404🙏59🕊39🥰29🤔27😢20😭20😱9😡9