TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" የሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነት መዘዙ ለአጎራባች ሃገራትም ተርፏል " - ካተሪን ፓቲሎ

የሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት በሱዳን ላይ ካስተለው ሰብአዊ እና ቁሳዊ ውድመት ባሻገር ኢትዮጵያን ጨምሮ በአጎራባች ሃገራት ላይ ብርቱ ኤኮኖሚያዊ ጉዳት ማድረሱን የዓለም የገንዘብ ድርጅት አስታወቀ።

በድርጅቱ የአፍሪቃ ጉዳዮች ምክትል ዳይሬክተር ካተሪን ፓቲሎ  " የሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነት መዘዙ ለአጎራባች ሃገራትም ተርፏል " ብለዋል።

" ቀድሞውኑ በራሳቸው የውስጥ ጉዳዮቻቸው ተይዘው የነበሩ የሱዳን ተጎራባቾች በስደተኞች መጥለቅለቅን ጨምሮ ሌሎች የደህንነት እና የንግድ ተግዳሮቶች አስከትሎባቸዋል " ሲሉ ገልጸዋል።

የዓለማቀፉ የገንዘብ ተቋም የትንበያ ሪፖርት እንደሚያመለክተው በጦርነቱ በተለይ በማዕከላዊ አፍሪቃ ፣ ቻድ ፣ ኤርትራ እና ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን ላይ ከፍተኛ ኤኮኖሚያዊ ጉዳት ሊደርስ ይችላል።

በተለይ ከገቢዋ አብዛኛውን ከነዳጅ ዘይት ሽያጭ የምታገኘው ደቡብ ሱዳን ባለፈው የካቲት ወር ሱዳን ውስጥ ከዋነኞቹ የነዳጅ ዘይት ማስተላለፊያዎች ቱቦዎች በአንዱ ላይ ጉዳት ከደረሰባት በኋላ ነገሮች አሳሳቢ መሆናቸውን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።

በተመሳሳይ በመካከለኛው ምስራቅ እና በዩክሬን እየተካሄዱ ያሉ ሌሎች " ውጫዊ ግጭቶች " እንደ የምግብ ዋጋ ፣ ማዳበሪያ እና የኃይል ወጪዎች ላይ ተጽዕኖ ማሳደራቸውን የዓለም የገንዘብ ድርጅት ገልጿል። #ዶቼቨለሬድዮ

@tikvahethiopia
🕊18685😭51🙏21😢19😱11🥰9😡8👏7