TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ከወራት በፊት በፀደቀው የህዝብ በዓላት እና የበዓላት አከባበርን ለመወሰን በወጣው አዋጅ በልማድ ሲከበር የቆየው " ግንቦት 20 " ብሔራዊ በዓልነቱ ቀርቷል። በመሆኑም በዚህ ዕለት የሚዘጋ መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልሆነ ተቋም አይኖርም / የሚዘጋ ስራ የለም። @tikvahethiopia
#ግንቦት20

የ " ግንቦት 20 " ከብሄራዊ በዓልነት ቢሰረዝም በትግራይ ስራ ተዘግቶ ተከብሯል።

ከወራት በፊት በፀደቀው የህዝብ በዓላት እና የበዓላት አከባበርን ለመወሰን በወጣው አዋጅ በልማድ ሲከበር የቆየው " ግንቦት 20 " ብሔራዊ በዓልነቱ ቀርቷል።

በመሆኑም በዚህ ዕለት የሚዘጋ መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልሆነ ተቋም አይኖርም / የሚዘጋ ስራ የለም።

ቢሆንም በትግራይ ክልል ዛሬ ግንቦት 20/2017 ዓ/ም ትምህርት ቤቶች ጨምሮ መላው የመንግስት መስሪያ ቤቶች ዝግ ሆነው ውለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ ቤተሰብ አባል በከተማው አስተዳደርና ከ15 በላይ መንግስታዊ ቢሮዎች በሚገኙበት የጋራ ህንፃ እንዲሁም በአንዳንድ የግልና የመንግስት መ/ቤቶች ባደረገው ምልከታ ሙሉ በሙሉ ዝግ ሆነው አጊኝቷቸዋል።

የመንግስትና የግል ባንኮች ሌሎች ደግሞ መዘጋት የማይችሉ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሰራተኞቻቸው በስራ ገበታ ላይ እንደሚገኙ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ትዝብቱ አጋርቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
👏1.19K202😡103🤔56😭27🕊14🙏12💔10😱9🥰3😢1