የዓመታት የቤት ጥያቄ ...
" ለልማት ተነሽዎች ለምን ቤት ተሰጣቸው አንልም ፤ ለረዥም ዓመታት ፍትሐዊነት በጎደለው መንገድ ለእኛ ሳይሰጥ መቅረቱ አሳዝኖናል " - ቅሬታ አቅራቢዎች
ለ21 ዓመታት ኮንዶሚኒየም ይደርሰናል ብለው ሲቆጥቡ የቆዩ የኮንዶሚኒየም ነባር ተመዝጋቢዎች ዕጣ ሳይወጣላቸው፣ ቤቶቹ ለልማት ተነሽዎች በመሰጠታቸው ቅሬታ አቀረቡ፡፡
ከ1997 ዓ.ም. ጀምሮ የኮንዶሚኒየም ቤቶችን በዕጣ ለማግኘት ሲጠባበቁ የቆዩ በርካታ ተመዝጋቢዎች እያሉ፣ ለልማት ተነሽዎች ቤቶች መሰጠታቸው ኢፍትሐዊ እንደሆነ ቅሬታ አቅራቢዎቹ ገልጸዋል፡፡
ይህን ቅሬታ ያቀረቡት ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጡት ቃል ነው።
" ለልማት ተነሽዎች ለምን ቤት ተሰጣቸው አንልም " ያሉት ቅሬታ አቅራቢዎች " ለረዥም ዓመታት ፍትሐዊነት በጎደለው መንገድ ለእኛ ሳይሰጠን መቅረቱ አሳዝኖናል " ብለዋል።
ለልማት ተብሎ ቤታቸው የፈረሰባው ዜጎች ቤት ሲሰጣቸው የ1997 እና የ2005 ዓ.ም. የኮንዶሚኒየም ቤቶች ተመዝጋቢዎች ጉዳይ በዝምታ መታለፉ ቅሬታ እንደፈጠረባቸው ገልጸዋል፡፡
የኮንዶሚኒየም ቤቶች ግንባታ እስኪያልቅ ድረስ ለምን በመንግሥት የተሠሩ ቤቶች አይሰጡንም ? ያሉት ተመዝጋቢዎቹ፣ ለሁለት አሠርት ዓመታት ቤት ለማግኘት በመጠበቃቸው በተለየ ሁኔታ በከተማ አስተዳደሩ ሊስተናገዱ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
በአሁኑ ጊዜ የቤት ኪራይና የልጆች ትምህርት ቤት ክፍያዎች ጣራ በመንካታቸው፣ ለችግር ተዳርገናል ያሉት ተመዝጋቢዎች፣ የኢትዮጵያ ዜጋ አይደለንም ወይ ሲሉም ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡
ለዓመታት ምላሽ በተነፈገው ጥያቄያቸው ምክንያት በመንግሥት ላይ ያላቸው እምነት መሟጠጡን ገልጸዋል፡፡
ተመዝጋቢዎቹ ለሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም፣ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን፣ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤትና ሌሎች ተቋማት ቅሬታቸውን ቢያሰሙም እስካሁን መፍትሔ እንዳላገኙ አክለዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ታምራት ምን ምላሽ ሰጡ ?
- አጠቃላይ የቤቶች ግንባታ ከሁለትና ከሦስት ዓመት ተኩል በኋላ የብድር አቅርቦት ችግር ተጨማሪ ግንባታ ማድረግ አላስቻለም፡፡
- ችግሩ እስኪፈታ ድረስ ግንባታ አይካሄድም ፤ ኮርፖሬሽኑ ያለበትን ውዝፍ ዕዳ እስኪከፈል ድረስም ሲያገኝ የነበረው ብድር ተከልክሏል።
- ኮርፖሬሽኑ ካለበት ዕዳ ውስጥ 36 ቢሊዮን ብር ተመላሽ አድርጓል ፤ ቀሪ 37.7 ቢሊዮን ብር ያልተከፈለ ውዝፍ ዕዳ አለበት ፤ ለመክፈልም የተለያዩ አማራጮችን እያጤንን ነው።
- በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብድር የሚሰጠው ለማጠናቀቂያ ሥራ ብቻ ነው። ለሰፊ የቤት ግንባታ ግን ተጨማሪ ብድር አይሰጥም።
- ለልማት ተነሽዎች ቅድሚያ መስጠትን መመርያው የሚያዝና የሚደግፈው ነው። ነገር ግን የኮንዶሚኒየም ዕጣ ጠባቂዎችን ወደ ጎን ከመግፋት ጋር መገናኘት የለበትም።
- የቤት አቅርቦት ጉዳይ የ1997 እና የ2005 ዓ.ም. የቤት ተመዝጋቢዎች ችግር ብቻ ሳይሆን፣ በአጠቃላይ በቤት አቅርቦቱ በአማራጭ የቤት ልማት ላይ እየተሠሩ ነው።
- ከተለመዱት 40/60 እና 20/80 ቤቶች በተጨማሪ በ70/30 ፕሮግራምና በማኅበር ቤቶች አቅም ያላቸው እንዲገነቡ የሚያስችል አሠራር ተዘርግቷል።
- ኮርፖሬሽኑ እስካሁን የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ሲገነባ የነበረው በቦንድ ግዥ ነበር፤ አሁን ግን የከተማ አስተዳደሩ ካለው በጀት ላይ እየመደበ ብድሩን እየከፈለና ለኪራይ የሚሆኑ ቤቶች እየገነባ ነው።
- ከዚህ በተጨማሪ መንግሥትና ባለሀብቶች ተቀናጅተው የሚገነቧቸው ቤቶች አሉ ፤ ለዝቅተኛ የኅብረተሰብ ክፍሎች እየተሰጡ ነው።
- የኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢዎችን በተመለከተ ቁጠባ ያቋረጡ አሉ። ነገር ግን አሁንም ኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢዎች የሉም ወይም ጨርሰን ሰጥተናል አላልንም።
- የኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢዎች ቅሬታ ትክክል ነው። ነገር ግን ከተማው ያለበትን የቤት አቅርቦት ችግር ሲፈታ የተመዝጋቢዎቹን ችግርም በዚያው ይፈታል።
- የነባሩ የዕጣ አወጣጥ ሒደት ቆሟል ወይም አልቆመም ብለን መናገር አንችልም፤ ምናልባት የባንክ ብድር ከተመለሰ እንደገና በሌላ ብድር ቤቶች ተገንብተው ለዕጣ ጠባቂዎች ለመስጠት ጥረት ይደረጋል።
- የተመዝጋቢዎች ዕጣ የማውጣት ሒደት ይቀጥላል ወይም አይቀጥልም የሚለው በቤት አቅርቦት ሁኔታው ይወሰናል።
- ከኮሪደር ልማት ተነሺዎች በአንድም በሌላም መንገድ ቢጣራ ተመዝጋቢዎች አሉ፡፡ ለኮሪደር ልማት ተነሽዎች የ40/60 እና የ20/80 ቤቶች ተሰጥተው አልቀው ወደ ኪራይ ቤት እየተገባ ነው።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የሕግና የአስተዳደር በደል ምርመራ መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ መንግሥቱ ቀና በበኩላቸው፣ በ1997 ዓ.ም. ኮንዶሚኒየም ለማግኘት ተመዝግበው ዕጣ ያልወጣላቸውን በተመለከተ ኮርፖሬሽኑ በደብዳቤ መጠየቁን ገልጸዋል፡፡
ይሁን እንጂ በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢቀርብም ምላሽ አለመገኘቱን አቶ መንግሥቱ ገልጸው፣ እንደገና በደብዳቤ ተጠይቆም ምላሽ ካልተገኘ ወደ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለማምራት መታቀዱን ተናግረዋል። #ሪፖርተርጋዜጣ
@tikvahethiopia

🤔958❤439😭220😢189👏179🙏145😡132🕊58🥰44😱37
#Ethiopia
የቻይና ባለሀብቶች በኢትዮጵያ እምነት የሚጣልበት ቢሮክራሲና በየጊዜው የማይለወጥ የኢንቨስትመንት ሕግ አተገባበር ተግባራዊ እንዲደረግ ጥያቄ አቅርበዋል።
የኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ምኅዳር ተገማች፣ የተረጋጋና ሥልጡን የሰው ኃይል የሚመራውና የውጭ ባለሀብቶች ሊተማመኑበት የሚያስችል ከባቢ እንዲፈጠር ቻይናውያን ባለሀብቶች አሳስበዋል፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ምኅዳር ውስጥ በፀጥታ ችግር፣ በቢሮክራሲ፣ በብልሹ አሠራርና በሙስና ምክንያት ሥራ መሥራት አልቻልንም የሚል ቅሬታ በብዛት እየተደመጠ መሆኑን ገልጸው፣ በኢትዮጵያ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ አፍስሰናል ያሉት የቻይና ባለሀብቶች ያሉት ችግሮች እንዲፈቱ ጠይቀዋል፡፡
ባለው የኢንቨስትመንት ማነቆ ላይ የፖሊሲ ምክክር በማድረግ በመንግሥትና በባለሀብቶቹ መካከል ድልድይ በመሆን ይሠራል የተባለለት " አፍሪካ – ቻይና ትሬድ ኤንድ ኢንቨስትመንት ፋሲልቴሽን " የተሰኘ አማካሪ ቡድን ይፋ ተደርጓል።
የአማካሪ ቡድኑ መሥራች ቻይናዊው ባለሀብት ጉዋን ሹ ምን አሉ ?
➡ በአገር ውስጥ የተሰማራ አምራች ኩባንያ የሚያመርተው ምርት ብቻ ሳይሆን፣ የሚመረተውን የሚጠቀመው ማኅበረሰብ ለሚቀርብለት ምርት መተማመኛ ይፈልጋል ተብሏል፡፡ ለዚህ ደግሞ የተረጋጋ የፀጥታ ሁኔታና አስቻይ ፖሊሲ ያስፈልጋል።
➡ ግልጽ የሆኑ መመርያዎች፣ ሊተነበዩና ተግባራዊ መደረግ የሚችሉ የኢንቨስትመንት ሕጎች ያስፈልጋሉ። ሕጎቹ ኢንቨስተሮች ወደ አገር ውስጥ ሲገቡ ለአንድና ለሁለት ዓመት ብቻ ሳይሆን ረዘም ላለ ጊዜ መተማመን የሚፈጥር መልኩ ዋስትና መስጠት አለባቸው።
➡ የውጭ ኢንቨስተሮች ሀብታቸውን በሚያፈሱባቸው አካባቢዎች ባሉ አስተዳደሮች ለንብረታቸው የጥበቃ ከለላ ማድረግ አስፈላጊ ነው። ለንብረታቸው መተማመኛ ያላገኙና የሕጎች አተገባበር መለዋወጥ ያስቸገራቸው ባለሀብቶች ወደ ጎረቤት ኬንያ፣ ታንዛኒያና ኡጋንዳ ሲሄዱ አይተናል።
➡ በሥራ ላይ ያለው የኢንቨስትመንት ፖሊሲ ወይም ሕግ ተገማችነቱ በግልጽ መቀመጡ ለኢንቨስተሮች መተማመንን ይፈጥራል። መተማመን ሲፈጠር ባለሀብቶች ባሉበት የመቆየትና ኢንቨስትመንታቸውን የማስፋት አቅማቸው ይጨምራል።
➡ በኢትዮጵያ ያለው የግብር ሥርዓት የኩባንያዎቹን ቁመናና አፈጻጸም ግምት ውስጥ ያላስገባ ከመሆኑም በላይ አሠራሩና አወሳሰኑ ግልጽ አይደለም። በዚህም የተነሳ ኢንቨስተሮች እንዴት እምነት አድሮባቸው ሊሠሩ ይችላሉ ?
➡ መንግሥት በአንድ በኩል የውጭ ባለሀብቶችን ለመሳብ የኃይል አቅርቦትና መሠረት ልማት ለማሟላት ሀብት፣ እያፈሰሰ በሌላ በኩል የሚወጡ ሕጎች ይዘት ተገማችነትና አተገባበር፣ እንዲሁም አሠራሮች ከዓላማው ጋር በልኩ ካልተጣጣሙ ሒደቱ ወደኋላ ይጎትታል።
➡ የባለሙያዎቹ ቡድን የተቋቋመው በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች መዋዕለ ንዋይ ያፈሰሱና ለመሰማራት ፍላጎት ያላቸው ባለሀብቶች፣ በኢንቨስትመንታቸው የሚታየውን ክፍተት ለመሙላት ነው።
አንድ ቻይና ኤምባሲ ዲፕሎማት በኢትዮጵያ በርካታ የቻይና ኩባንያዎች መዋዕለ ንዋያቸውን እያፈሰሱ መሆናቸው የታመነበት ቢሆንም፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አንዳንድ ኩባንያዎች ከኢትዮጵያ እየለቀቁ ወደ ታንዛኒያ፣ ኡጋንዳና ሌሎች አገሮች እየተሰደዱ ናቸው ብለዋል፡፡
ይህ የሆነው ተገማች ያልሆኑ ሕጎችና ብልሹ አሠራሮች ከቢሮክራሲ ማነቆ ጋር በመደራረባቸው እንደሆነ ገልጸዋል።
ይህንን አሳሳቢ ችግር ለማስተካከል የምሁራን ቡድኑ ትልቅ ሚና ይጠበቅበታል ብለዋል።
በየካቲት 2016 ዓ.ም. ወደ ኢትዮጵያ ከመጡ ጀምሮ ባለሀብቶች ወደ ሌላ አገር እየተሻገሩ እንደሆነ መስማታቸውን ጠቅሰው፣ ይህ የምሁራን ስብስብ የቻይና ባለሀብቶችን ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያውያንንም ሊጠቅም ይገባል ብለዋል፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማካሪ ቡድኑ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አዳሌ ኦዳ ምን አሉ ፤ " የተማሰረተው ዕውቀትን መሠረት ያደረገ ውሳኔ ለማስተላለፍ ዕገዛ የሚያደርግ ቡድን ነው " ብለዋል።
" በቀጣይ ኢንቨስተሮች ሊያጋጥማቸው የሚችሉ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን በማመላከትና የፖሊሲ ማማከር ሥራ በማከናወን ቀጣይነት ያለው የቢዝነስና የንግድ ግንኙነት እንዲፈጠር ማድረግ ላይ ጥረት ይደረጋል " ሲሉ ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ የቻይና ባለሀብቶች ተወካይ ፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ በፋይናንስ እጥረትና በጦርነት፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ደግሞ በፀጥታ ችግር የግብር ሥርዓት አስቸጋሪ መሆኑን ገልጸዋል።
" አንድ ጊዜ ከገቢዎች ቢሮ ስልክ ከተደወለ ተኝቶ ማደር የለም " ሲሉ ተናግረዋል፡፡
" የገቢዎችና የጉምሩክ ሠራተኞች የሚጠቀሙበት ሲስተም በትክክል ለምን አይሠራም ብዬ ስጠይቃቸው አናውቅም ይላሉ፡፡ በዚህ ላይ ሠራተኞቹ የተረጋጉ አለመሆናቸው አሳሳቢ ነው " ብለዋል፡፡
" ምንም እንኳ ትርፍ ለማግኘት ኢትዮጵያ ብንመጣም አብረን ማደግ እንችላለን፣ በየተቋማቱ ያሉ አሠራሮች ግን ይስተካከሉ " ብለዋል።
የማይገመት አሠራርና ተለዋዋጭ የሕግ አተገባበር ትልቅ ማነቆ በመሆኑ መንግሥት ማስተካከያ ያድርግ ሲሉም አሳስበዋል፡፡ #ሪፖርተርጋዜጣ

❤499👏184😡37🤔24😭22🙏21🕊14😱8🥰6😢4
" ኢትዮ ቴሌኮም የሰነደ ሙዓለ ነዋዮች ግብይት አገናኝነት (broker) ፈቃድ አግኝቷል " - ብሩክ ታዬ (ዶ/ር)
ሙሉ በሙሉ በመንግሥት ባለቤትነት የተያዘው ኢትዮ ቴሌኮም ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች ለመሸጥ ያቀደውን 10 በመቶ ድርሻውን፣ የራሱን የቴሌብር መተግበሪያ በመጠቀም ራሱ እንዲያገበያይ እንደተፈቀደለት ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።
ከኢትዮ ቴሌኮም ጠቅላላ ሀብት ውስጥ አሥር በመቶ የሚሆነው በአክሲዮን ተከፋፍሎ በሚቀጥለው ሳምንት ከረቡዕ ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ለሽያጭ የሚያቀርብ ሲሆን፣ መንግሥት ቀደም ብሎ በወሰነው መሠረት የኩባንያው አክሲዮኖች ለአገር ውስጥ አክሲዮን ገዥዎች ይሸጣል።
የኢትዮጵያ ሙዓለ ነዋይ ገበያ የኢትዮ ቴሌኮምን አሥር በመቶ ድርሻ በማገበያየት አገልግሎቱን እንደሚጀምር ከዚህ ቀደም ተግልጾ የነበረ ቢሆንም፣ ይህ ዕቅድ ተቀይሮ ኢትዮ ቴሌኮም ራሱ ለሕዝብ የሚያቀርበውን ድርሻ በቴሌብር መተግበሪያው በመጠቀም እንዲያገበያይ እንደተፈቀደለት ለማወቅ ተችሏል።
ማክሰኞ መስከረም 28 ቀን 2016 ዓ.ም. በለንደን በተካሄደው የአፍሪካ ኢንቨስትመንት ኮንፈረንስ ላይ የተሳተፉት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብሩክ ታዬ (ዶ/ር)፣ በኢትዮጵያ ስላሉ የኢንቨስትመንት ዕድሎች ሲያብራሩ የኢትዮ ቴሌኮም አሥር በመቶ ድርሻ በቀጣዩ ሳምንት ለገበያ እንደሚቀርብ አረጋግጠዋል።
በኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ነዋዮች ገበያ በቀጣዩ ወር በይፋ ሥራ እንደሚጀምር የተናገሩት ብሩክ (ዶ/ር)፣ ኢትዮ ቴሌኮም እንዲሸጥ የተፈቀደለትን 10 በመቶ ድርሻውን በኢትዮጵያ የሰነደ መዋዕለ ነዋዮች ገበያ አማካይነት ሳይሆን የራሱን የቴሌብር መተግበሪያ በመጠቀም ለሽያጭ እንደሚያቀርብና የግብይት ሒደቱም በኩባንያው እንደሚፈጸም አስታውቀዋል።
የመጀመሪያ ዙር የሕዝብ አክሲዮን ሽያጭ (Initial Public Offering) ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ በመሆኑ፣ ይህ ሒደት ተዘሎ ኩባንያው ራሱ በቀጥታ አክሲዮኖቹን እንደሚሸጥ ገልጸዋል።
ኢትዮ ቴሌኮም የሰነደ ሙዓለ ነዋዮች ግብይት አገናኝነት (broker) ፈቃድ ከኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ያገኘ መሆኑን የጠቀሱት ብሩክ (ዶ/ር)፣ ይህም ኩባንያው የራሱን አሥር በመቶ ድርሻ በቀጥታ ለአገር ውስጥ ኢንቨስተሮች መሸጥ እንደሚያስችለው አስረድተዋል።
በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰነደ ሙዓለ ነዋዮችን ለማገበያየት የተቋቋመው የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ነዋዮች ገበያ፣ በሚቀጥለው ወር በይፋ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምርም ተናግረዋል።
የተመሠረተበትን 130ኛ ዓመት ዘንድሮ የሚያከብረው ኢትዮ ቴሌኮም በ2016 በጀት ዓመት 93 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን ያስታወቀ ሲሆን፣ ይህንን ገቢ በ2017 ዓ.ም. ወደ 163.7 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ዕቅድ ይዟል። #ሪፖርተርጋዜጣ

😡707❤292👏82😭51🥰47🤔44🙏35😱30😢27🕊19
በአዲስ አበባ ከፍጥነት ወሰን በላይ በማሽከርከር ለሞት የሚዳርጉ 5 መንገዶች የትኞቹ ናቸው ?
➡ በተደረገ የዳሰሳ ጥናት ከፍጥነት ወሰን በላይ በማሽከርከር ከፍተኛ የሞት አደጋ የሚያስከትሉ 5 መንገዶች ተለይተዋል።
➡ ከፍተኛ የሞት አደጋ ያስከትላሉ ተብለው የተለዩት ፦
° መገናኛ፣
° ኃይሌ ጋርመንት፣
° ቦሌ ሚካኤል፣
° ጦር ኃይሎች
° ቻይና ካምፕ መንገዶች ናቸው። በአማካይ በዓመት ከ6 እስከ 13 ዜጎች በእነዚህ መንገዶች በሚደርሱ የተሽከርካሪ አደጋቸው ሕይወታቸውን ያጣሉ።
➡ ከመንገዶቹ አንዳንዶቹ የእግረኛ መተላለፊያ የላቸውም ፤ አሽከርካሪዎች ይህን ግምት ውስጥ በማስገባት ከፍጥነት ወሰን በላይ እያሽከረክሩ አደጋ ያደርሳሉ።
➡ ከፍጥነት ወሰን በላይ በማሽከርከር በሚደርሰው የትራፊክ አደጋ፣ በአብዛኛው ሕይወታቸውን የሚያጡት ወንዶች ናቸው። መገናኛ አካባቢ አደጋ ከደረሰባቸው 13 ሰዎች አብዛኞቹ ወንዶች መሞተዋል።
➡ አደጋ የሚደርሰው ከቀኑ 6፡00 ሰዓት እስከ 8፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ሲሆን በተለይም ሰንበት ወይም የዕረፍት ቀናት ከመንገድ መጨናነቅ ነፃ ስለሚሆኑ፣ ተከትሎ በፍጥነት ማሽከርከር ምክንያት የሞት ምጣኔው ከፍተኛ ነው።
➡ አደጋዎች የሚያሳዩት ተቆጣጣሪ ተቋማትም ሆኑ አደጋ አድራሾችና ተጎጂዎች የሚያደርጉት ጥንቃቄ ዝቅተኛ እንደሆነ ነው።
➡ ከፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት ከባድ ተሽከርካሪዎች ናቸው። ከሌሎች የተሽከርካሪ ዓይነቶች አብላጫውን አደጋ የሚያደርሱትም እነሱ ናቸው።
➡ በዓለም የጤና ድርጅት የትራፊክ አደጋ ሥጋት መንስዔዎች ተብለው የተለዩት በፍጥነት ማሽከርከር፣ ጠጥቶ ማሽከረከር፣ የደኅንነት ቀበቶ አለመጠቀምና የራስ ቅል መሸፈኛ አለመጠቀም ከፍተኛውን ቦታ ይይዛሉ።
➡ 43 በመቶ የሚሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ አሽከርካሪዎች ከፍጥነት ወሰን በላይ ያሽከረክራሉ። በዚህ ምክንያት ችግሩ ትኩረት ያሻዋል።
➡ በየዓመቱ ከ400 የሚበልጡ ሰዎች በትራፊክ አደጋ ይሞታሉ። የጥናቶች የትኩረት አቅጣጫ የፍጥነት መገደቢያ መጠቀምና ሥር ነቀል የማኅበረሰብ ግንዛቤ ማስጨበጥ ያስገልጋል።
(የአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ማኔጅመንት መረጃ)
#ሪፖርተርጋዜጣ

🙏437😭178❤173👏45🕊31😢22😱14🥰13😡13🤔11
" ' ነፍስ እናመጣለን ' ማለት የቀራቸው ማስታወቂያዎች፣ በጤናው ዘርፍ ላይ ከፍተኛ አደጋ ደቅነዋል " - ጤና ሚኒስቴር
በተለያዩ ሚዲያዎች የሚሠራጩ የተጋነኑና " ነፍስ እናመጣለን " ማለት የቀራቸው ማስታወቂያዎች፣ በጤናው ዘርፍ ላይ ከፍተኛ አደጋ መደቀናቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
አሳሳቢነታቸው እየጨመረ ያለውና ሕዝቡን የሚያደናግሩ የተጋነኑና እውነት ያልሆኑ ማስታወቂያዎች መንግሥት ባለበት አገር መቆጣጠር ካልተቻለ፣ በማኅበረሰቡ ላይ ከዚህ የባሰ ችግር መፍጠራቸው የማይቀር መሆኑን፣ በጤና ሚኒስቴር የጤናና ጤና ነክ ተቋማትና ባለሙያዎች ቁጥጥር መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ እንዳልካቸው ፀዳል ተናግረዋል።
በሐሰተኛ ማስታወቂያዎች " ነፍስ እናመጣለን " በቀረው ልፈፋ፣ ኅብረተሰቡ እየተጭበረበረና ገንዘቡን ጭምር እየተዘረፈ ነው ተብሏል።
አቶ እንዳልካቸው ፀዳል ምን አሉ ?
" በጤና ግብዓትም ሆነ አገልግሎት ላይ በአገር ደረጃ የሕግ ክፍተት የለም " ያሉ ሲሆን ነገር ግን በተለይ ወደ ታችኛው ማኅበረሰብ ሲኬድ የአፈጻጸም ችግሮች ጎልተው እንደሚታዩ ገልጸዋል።
ተቋማት በተሰጣቸው የሥልጣን ዕርከን ተገዥ ሆነው አለመሥራት አንዱ የቁጥጥር ክፍተት እንደሆነ አመልክተው " የተጋነኑና ከእውነት የራቁ ማስታወቂያዎች ከፍተኛ ችግር እየፈጠሩ ናቸው " ብለዋል።
አንዳንድ ባለሙያዎች በማኅበራዊ ሚዲያ " እኔ ነኝ የተሻልኩ " ብለው የሚያቀርቡት መረጃ በጤናው ዘርፍ ላይ ትልቅ ሥጋት ፈጥሯል ብለዋል።
ያለ ምንም ተጨባጭ ማስረጃ ሌሎች ባለሙያዎችን ማጥላላትና መሰል ችግሮች ማኅበረሰቡን መጉዳታቸው አይቀርም ሲሉም ገልጸዋል።
" ሚዲያው በእኛ ሥር ስላልሆነ ለቁጥጥርና ለክትትል አስቸግሮናል " ያሉት አቶ እንዳልካቸው ፤ ሚዲያውን የሚቆጣጠሩ አካላት የሚያሠራጯቸውን ማስታወቂያዎች በአግባቡ ሊከታተሉና ሊቆጣጠሩ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የጤና ሚኒስትር ደኤታ አየለ ተሾመ (ዶ/ር) ምን አሉ ?
የመረጃ አቅርቦት አማራጮች በመበራከታቸው ምክንያት በግለሰቦችም ሆነ በተቋም ደረጃ የሚደርሱ መረጃዎች ለማኅበረሰቡ መልካም ሆነው ሳለ፣ ነገር ግን የመረጃ ፍሰቱ የተለያዩ ተግዳሮቶችን ይዞ መምጣቱን ተናግረዋል።
በጤና ዘርፍ የሚቀርቡ መረጃዎች ብዙ ማስረጃዎችና የማጣሪያ ደረጃዎችን አልፈው መቅረብ ሲገባቸው ለማኅበረሰቡ ትክክል ያልሆኑ፣ ግራ የሚያጋቡና እርስ በርሳቸው የሚጋጩ መረጃዎችን እያደረሱ ነው ብለዋል።
የጤና መረጃ እንደ ሌላው የንግድ ሥርዓት ከቁጥጥር ውጪ ሆኖ ሊሄድ አይችልም ያሉ ሲሆን የሚሰጡት መረጃዎች አጠራጣሪ ከሆኑ ስህተት ስለሚፈጥሩ ከወዲሁ ሊታረሙ እንደሚገባ ጠቁመዋል።
የሚዲያ ባለሙያዎችም የጤና መረጃዎችን ለማኅበረሰቡ ሲያቀርቡ የሚቀርበውንና የማይቀርበውን ከመለየት ባሻገር፣ ስለሚቀርበው መረጃ ከሚመለከተው አካላት ጋር በመሆን ተዓማኒነቱንና ትክክለኛነቱን ማረጋገጥ እንዳለባቸውና ሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
" መረጃዎችን ለማድረስ ባለሙያ መሆን ብቻ በቂ አይደለም " ብለው መረጃ ሰጪው ለሚፈጠረው ችግርም ኃላፊነትን መውሰድ የሚችል መሆን አለበት ብለዋል፡፡
የማይድኑ በሽታዎችን " እናድናለን፣ እንፈውሳለን " የሚሉ ራሳቸውን ከሌሎች የተለየ ብቃትና ክህሎት እንዳላቸው በማስመሰል በማኅበረሰቡ ውስጥ ውዥንብር የሚፈጥሩ አካላት ተበራክተዋል ያሉ ሲሆን ተገልጋዮችን ለአላስፈላጊ ወጪና ጉዳት የሚዳርጉ በመሆናቸው በሕግና በማዕቀፍ ሊመሩ እንደሚገባ አብራርተዋል፡፡
በተለይ ካለፉት ጥቂት ወራት ወዲህ ብዙ አዳዲስ ልምዶች መስተዋላቸውን ተናግረው ' ቲክቶክ ' በተባለው ማኅበራዊ የሚዲያ አውታር በርካታ ባለሙያዎች የተለያዩ መረጃዎችን ለማኅበረሰቡ እያደረሱ እንደሆነ ገልጸዋል።
የሚሰጡት መረጃ የተገልጋይን መብትና ግዴታ ያላከበረና ተገልጋዩን ለገበያ የሚያውሉ ሕገወጥ ተግባራትን የሚያባብሱ ልምዶች መሆናቸውን አሳውቀዋል።
በዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን በአንድ ጊዜ ለመቆጣጠር መሞከር ለጤናው ዘርፍ ከፍተኛ ፈተና የሚደቅን በመሆኑ፣ በሒደት በማስተማርና በማሻሻል ሚዛኑን የጠበቀ ቁጥጥር ለማድረግ የባለድርሻ አካላት ዕገዛ እንደሚያስፈልግ አክለዋል፡፡
ቀደም ሲል የጤና ሥርዓቱን እየፈተነው የነበረው የመረጃ እጥረት ነበር ገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅት ደግሞ መረጃዎች ከአቅም በላይ እየሆኑ ተዓማኒነታቸው ያልተረጋገጠ ስለሚሆን፣ በቀጣይ ችግሩን የሚቃኝና ከመረጃ ሥርዓቱ እስከ አገልግሎት አሰጣጡ የሚያሻሽል፣ እንዲሁም ተጠያቂነት የሚያሰፍን መመርያ እየተዘጋጀ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ግለሰቦች ሚዲያ በመጠቀም በባህላዊም ሆነ በሃይማኖታዊ መንገድ ታማሚዎች የጀመሩትን መድኃኒት እንዲያቆሙና እንዲሞቱ፣ እንዲሁም ቤተሰብ እንዲበተን እያደረጉ እንደሆነ ተናግረው ይህ ከባድ ወንጀል መሆኑን ማወቅ ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡
ከዚህ ባሻገር አንዳንድ የጤና ተቋማት የሌላቸውን የሕክምና መሣሪያ እንዳላቸው በማስመሰል ሚዲያውን ተጠቅመው ተገልጋዮችን የማታለልና የማጭበርበር ድርጊት እንደሚፈጽሙ ጠቁመዋል፡፡
ይህንንና መሰል ተግባራትን ሲያከናውኑ የተገኙ የጤና ተቋማት የማሸግና ከሥራ የማገድ ቅጣት እንደተጣለባቸው አሳውቀዋል።

👏460❤174🕊45🤔33🙏27😡22😢21🥰17😭17😱7
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ የገቢ ግብር ምጣኔ ላይ ማሻሻያ ለማድረግ መንግስት ረቂቅ አዋጅ ማዘጋጀቱን ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል። ሬድዮ ጣቢያው ከገንዘብ ሚኒስቴር አገኘሁት ባለው መረጃ በደመወዝተኛው ሆነ በንግድ የገቢ ግብር ምጣኔ ላይ ማሻሻያዎችን የያዘ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቷል። በመጭው ሰኞም በረቂቅ አዋጁ ላይ ከባለሙያዎች ጋር ለመመካከር ጥሪ ማድረጉ ተሰምቷል። የኢትዮጵያ ሰራተኞች ኮንፌዴሬሽንና…
#ኢትዮጵያ
የሠራተኞች መነሻ የደመወዝ ወለል 8,384 ብር እንዲሆን ተጠይቋል።
ወርኃዊ ደመወዛቸው እስከ 8,384 ብር የሆነ ሠራተኞች ከግብር ነፃ እንዲሆኑ የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) ለመንግሥት ጥያቄ ማቅረቡን ገለጸ፡፡
የኢሠማኮ ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጡት ቃል ፥ " ወርኃዊ ደመወዛቸው እስከ 8,384 ብር የሆነ ተቀጣሪ ሠራተኞች ከግብር ነፃ እንዲደረጉ ለመንግሥት ጥያቄ አቅርበናል " ብለዋክ።
የገንዘብ ሚኒስቴር ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት በሥራ ላይ ቆይቷል የተባለውን የገቢ ግብር አዋጅ 979/2008ን ለማሻሻል ጉዳዩ ይመለከታቸዋል ከተባሉ ባለድርሻዎች ጋር ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ እስከ ሁለት ሺሕ ብር የሚከፈለቸው ሠራተኞች ከግብር ነፃ እንዲሆኑ ተደንግጓል፡፡
ኢሠማኮ እስከ 8,384 ብር ድረስ የሚከፈለቸው ተቀጣሪዎች ከግብር ነፃ እንዲሆኑ ለገንዘብ ሚኒስቴር በደብዳቤ እንደጠየቀ አስታውቋል፡፡
አቶ ካሳሁን በዓለም ባንክ መረጃ መሠረት ዕለታዊ ገቢው ከሦስት ዶላር በታች የሆነ ሰው ደሃ በመሆኑ፣ የመንግሥት የገቢ ግብር በዚህ ወለል ሥር ያሉ ተቀጣሪዎችን ታሳቢ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል፡፡
በማናቸውም ቀጣሪ ተቋማት የሚሠሩ ሠራተኞች በወር ከ8,384 ብር እስከ 22,974 ብር ደመወዝ የሚያገኙ ሠራተኞች፣ አሥር በመቶ ግብር እንዲጣልባቸው መንግሥትን መጠየቁን ኢሠማኮ ገልጿል፡፡
ከ22,975 እስከ 44,530 ብር ወርኃዊ ደመወዝ ተከፋዮች የ15 በመቶ፣ ከ44,531 እስከ 72,336 ብር የሚከፈለቸው ደግሞ 20 በመቶ፣ እንዲሁም ከ72,337 እስከ 107,449 ብር የ25 በመቶ ግብር እንዲጣልባቸው ኢሠማኮ በደብዳቤው አሳስቧል።
ከ107,450 እስከ 150,107 ብር ድረስ የሚከፈለቸው ሠራተኞች 30 በመቶ ግብር፣ እንዲሁም 150,108 ብር እና ከዚያ በላይ የሚከፈለቸው ተቀጣሪ ሠራተኞች ደግሞ 35 በመቶ ግብር እንዲከፍሉ ለመንግሥት ባቀረበው ደብዳቤ ኢሠማኮ መጠየቁን ገልጿል።
አሁን በሥራ ላይ ባለው የሠራተኞች የገቢ ግብ አዋጅ መሠረት እስከ 600 ብር ድረስ የሚከፈላቸው ሠራተኞች ከግብር ነፃ ሲሆኑ፣ ከ10,900 ብር ጀምሮ ደግሞ 35 በመቶ ግብር እንዲከፍሉ ይገደዳሉ፡፡
የገንዘብ ሚኒስቴር ከአንድ ሳምንት በፊት ለውይይት ይፋ ባደረገው የገቢ ግብር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ 1,200 ብር፣ 1,600 ብር እና 2,000 ብር ወርኃዊ ደመወዝተኞች ከግብር ነፃ እንዲደረጉ ድንጋጌ መኖሩ ይታወሳል።
የመንግሥት የገቢ ግብር ማሻሻያው ሠራተኞች ያለባቸውን ወቅታዊ የኢኮኖሚ ሁኔታ ታሳቢ ያላደረገ እንደሆነ የተለያዩ የውይይት ተሳታፊዎች አስተያየት መስጠታቸው አይዘነጋም፡፡
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።

❤3.78K👏674🙏169😭76😡47🕊45🥰36🤔36😱22😢11💔9