TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.61K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#NationalExam " የኦንላይን ፈተናው አልቀረም። የሚሰራጨው ሀሰተኛ መረጃ ነው " - ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት ሚኒስቴር የ2016 ዓ.ም የ 12ተኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በበይነ መረብና በወረቀት እንደሚሰጥ መግለጹ ይታወቃል። ሆኖም በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ ገጾች የበይነ መረብ ፈተናው እንደቀረ ተደርጎ መረጃ እየተሰራጨ መሆኑን ገልጿል። ሚኒስቴሩ ይህ በፍጹም ከእውነት የራቀ ሃሰተኛ…
#ተጨማሪ #ብሔራዊ_ፈተና

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በኦንላይን ከሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ጋር በተያያዘ አንድ የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር አናግሯል።

አመራሩ ፥ " የኦንላይን ፈተናው አልቀረም " ሲሉ አስረግጠው ተናግረዋል።

በየማህበራዊ ሚዲያው " የኦንላይን ፈተና ቀርቷል ፤ ሁሉም ተፈታኝ ፈተናውን በወረቀት ይወስዳል " እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ ፍጹም ሀሰተኛ መረጃ እንደሆነም አረጋግጠዋል።

ተማሪዎች በሀሰተኛ መረጃ ሳይረበሹ ለፈተናው ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ተብሏል።

ከዚህ በተጨማሪ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት  ፥ የ2016 ዓ.ም የ12ተኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በኦንላንይ እና በወረቀት እንደሚሰጥ አረጋግጧል።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይ የበይነ መረብ ፈተናው እንደቀረ ተደርጎ እየቀረበ ያለው መረጃ  ሃሰተኛ ነው ብሏል።

ፈተናው በሁለቱም በወረቀት እንዲሁም በኦንላይን እንደሚሰጥ አሳውቋል።

@tikvahuniversity @tikvahethiopia
👏380😭234😡152108🤔57🙏34🕊25🥰20😢19😱13
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ 13 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈረደባቸው። የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፤ ባሳለፍነው ሳምንት በሁለት ክሶች ጥፋተኛ የተባሉት የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ ላይ 13 ዓመት ፅኑ እስራትና 21 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት ፍርድ ማሳለፉን የቲክቫህ ኢትዮጵያ ሀዋሳ ቤተሰብ አባል መረጃውን አድርሷል። ፍርድ ቤቱ የቀድሞዉ ከንቲባ ካቀረቡት…
#ተጨማሪ

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከዚህ ቀደም በዋለው ችሎት የሲዳማ ክልል ፍትህ ቢሮ አቃቤ ህግ በረ/ፕ ፀጋዬ ቱኬ ላይ በ488,000 ብር የቤት ቁሳቁስ የተገዛበት ብሎ ላቀረበባቸው ክስ ፍ/ቤቱ ነፃ ናቸው ብሏቸው ነበር።

ነገር ግን " ስልጣንን ያለአግባብ በመገልገል በአጠቃላይ 97, 088,965/ ዘጠና ሰባት ሚሊዮን ሰማኒያ ስምንት ሺህ ዘጠኝ መቶ ስልሳ አምስት/ ብር ያለአግባብ እንዲባክን አድርጓል " በሚል በክልሉ ዋና ኦዲት መስሪያ ቤት ግኝት መነሻ የቀረበባቸው ክስ በኦዲት እና በሰው ማስረጃ መረጋገጡን በመግለጽ በተጨማሪም ያልተገባ ጥቅም የማግኘት ወንጀል ክስ ቀርቦባቸው የጥፋተኝነት ውሳኔ አስተላልፎ ነበር።

ፍርድ ቤቱ ዛሬ በዋለው ችሎት ተከሳሽ ረ/ፕ ፀጋዬ ቱኬ ስልጣንን ያለአግባብ በመጠቀም በአጠቃላይ 97 ሚልዮን 88 ሺህ 965 ብር የመንግስት ገንዘብ እንዲባክን አድርገዋል እንዲሁም 260 ሺህ ብር ያልተገባ ጥቅም አግኝተዋል በሚል ለሁለቱም ወንጀል ክሶች ተከሰዉ ከታሰሩበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በድምሩ 13 ዓመት ጽኑ እስራት እና 21 ሺህ ብር ቅጣት ውሳኔ አስተላልፏል።

በተመሳሳይ አቶ ታርኩ ታመነ፣ አቶ ታፈሰ ቱናሻ ፣ አቶ ተሰማ ዳንጉሼ እና አቶ ሰይፉ ዴሊሳ የመንግስትን ሥራ በማያመች መንገድ በመምራት፣ በሙስና እንዲሁም በሌሎች ክሶች የጥፋተኝነት ውሳኔ ተላልፎባቸው የነበረ ሲሆን ለቀረበባቸው ክስ የቅጣት ውሳኔ ማቅለያ እንዲደረግላቸው ያቀረቡትን ዝርዝር ምክንያቶች መካከል ተቀባይነት ያገኙትን በመመልከት ፦
➡️ 2ኛ ተከሳሽ አቶ ተሰማ ዳንጉሼ በሙስና ወንጀል ክስ 3 ዓመት ጽኑ እስራትና 1 ሺህ ብር ቅጣት ተላልፎባቸው በሁለት ዓመት እንዲታገድ፣
➡️ በ3ኛው ተከሳሽ አቶ ታሪኩ ታመነ ተከሰዉ ከታሰሩበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 10 ዓመት ጽኑ እስራትና 41 ሺህ ብር ቅጣት፣
➡️ በ4ኛ ተከሳሽ አቶ ታፈሰ ቱናሻ ተከሰው ከታሰሩበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 8 ዓመት ጽኑ እስራትና 51 ሺህ ብር ቅጣት
➡️ በ5ኛ ተከሳሽ አቶ ሰይፉ ዴሊሳ ተከሰዉ ከታሰሩበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 8 ዓመትከ 5 ወር ጽኑ እስራትና 76 ሺህ ብር ቅጣት ውሳኔ በማሳለፍ የችሎት ዉሎን አጠናቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከፍርድ ቤቱ ነው ያገኘው።

@tikvahethiopia
😁561👏243185😢90😭85😡48🤔46🙏35🕊33😱20🥰11