TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.3K photos
1.62K videos
218 files
4.4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" የ18 ወራት የዱቲ ክፍያ አልተከፈለንም " - የዲላ ዙሪያ ወረዳ ጤና ባለሙያዎች

" መሠረታዊ ችግሩ የበጀት ችግር ነው፤ የካሽ እጥረት ነው ያለው " - የጌዴኦ ዞን ጤና መምሪያ

በጌዴኦ ዞን ዲላ ዙሪያ ወረዳ በ6 ጤና ጣቢያዎች የሚገኙ ጤና ባለሙያዎች የ18 ወራት የዱቲ ክፍያ እንዳልተከፈላቸው፣ እንዲከፈላቸው ቢጠይቁም መፍትሄ እንዳላገኙ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ጤና ባለሙያዎቹ በሰጡት ቃል፣ " እንዲከፈለን ጠይቀን ነበር። ‘#ገንዘብ የለንም እንከፍላለን’ እያሉ ነው የተበጀተ በጀት እያለ ገንዘቡን ለሌላ ጉዳይ እየተጠቀሙ ያቆዩት " ብለዋል።

- ጪጩ
- አንድዳ
- ስሶታ
- ወቸማ
- ኡዶ
- ቱምትቻ በተሰኙ የወረዳው 6 ጤና አጠባበቅ ጣቢያዎች ከ01/06/2015 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 01/09/2016 ዓ/ም ለ18 ወራት የዱቲ ክፍያ አልተከፈለም ነው ያሉት።

ያልተከፈላቸውን ገንዘብ መጠን ሲገልጹም አንዷ ቅሬታ አቅራቢ፣ " የእኔ ከ80,000 ብር በላይ ነው። ከእኔ በላይ ደመወዝ እርከን ላላቸው ደግሞ ይጨምራል። የአንድ ሰው ከዚህ በላይ ሲሆን፣ የ6ቱ ጤና ተቋም ብዙ ገንዘብ ነው " ሲሉ አስረድተዋል።

ለተነሳው ቅሬታ ምላሽ የጠየቅናቸው የጌዴኦ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አንዱዓለም ማሞ፣ " ጉዳዩ በእርግጥ ያለ ነው። መሠረታዊ ችግሩ የበጀት ችግር ነው፤ የካሽ እጥረት ነው ያለው። ያን ለመፍታት በጋራ እየሰራን ነው " ብለዋል።

ባለሙያዎቹ፣ 'የተበጀተ በጀት አለ ግን ለሌላ ጥቅም እያዋሉት ነው ያዘገዩብን' ላሉት ቅሬታ በሰጡት ምላሽ ኃላፊው፣ " እንደዛ አይደለም። በጀቱ ተይዟል እውነት ነው። ነገር ግን የጥሬ ገንዘብ እጥረት እንጂ ወረዳውም ለመክፈል ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቶ አይደለም " ሲሉ ተናግረዋል።

የዞኑ የብልጽግና ጽ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ አይደፈር ሽፈራው በበኩላቸው ፤ ችግሩ የጥሬ ገንዘብ እጥረት መሆኑን ገልጸው፣ ለ3 ዓመታት የዱቲ ክፍያ 6.4 ሚሊዮን ብር እንደተበጀተ፣ ገንዘቡን ለማፈላግለግ እየተሰራ እንደሆነና ዱቲ የሚከፈላቸው የባለሙያዎች ብዛት መረጃም እየተሰበሰበ መሆኑን አስረድተዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
🤔291127😢101😭65😡48🕊22🥰20🙏19😱17👏12