" ጤፍን ከባዕድ ነገር ጋር ቀላቅለው እንጀራ ለገበያ ሲያቀርቡ የነበሩ 84 ግለሰቦች በቁጥጥ ሥር ውለዋል " - ሀዋሳ ፖሊስ
በሀዋሳ ከተማ ጤፍን ከባዕድ ነገር ጋር ቀላቅለው እንጀራ ጋግረው ለገበያ የሚያቀርቡ 84 ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የከተማው ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።
የመምሪያው ኃላፊ ኮማንደር መልካሙ አየለ በዋናነት ፦
- በታቦር ፣
- በቱላ
- በዳቶ ክፍለ ከተሞች ከዚህ ጋር በተያያዘ በ30 ቤቶች በተደረገ ፍተሻ ለጋገራ የተዘጋጀ ሊጥና ዱቄት ከተለያዩ ባዕድ ቁሶች ጋር መያዙን ገልጸዋል።
ግለሰቦቹ ፈቃድ ሳይሰጣቸው በማኅበር ራሳቸውን አደራጅተው ወደ ሥራ እንደገቡና ጤፍን ከባዕድ ነገር ጋር በመቀላቀል በሕገ ወጥ መንገድ እንጀራ ጋግረው #ለሆቴሎች ሲያቀርቡ እንደቆዩም ተናግረዋል።
የሲዳማ ክልል ጤናና ጤና ነክ አገልግሎት ግብዓት ጥበቃና ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ቡሪሶ ቡላሾ ፤ " ከተያዙት ግብዓቶች ውስጥ ለምርመራ ከተላኩ 7 ናሙናዎች 5ቱ በሰው ጤና ላይ ጉዳት የሚያስከትሉ ንጥረ ነገሮቸ እንደተገኘባቸው ተረጋግጧል " ብለዋል፡፡
#ኢዜአ
@tikvahethiopia

😭1.17K❤169👏122🙏77😡49💔43🤔31😱31🕊27😢19🥰15