TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.9K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ከቤት ኪራይ እና ከዕለት ፍጆታ ተርፎ ቤት ለማግኘት 25 በመቶ መቆጠብ አንችልም " - መምህራን

🔴 " ዘጠኝ እና አስር ዓመት የስራ ልምድ ያለው መምህር 10 ሺህ ብር ገደማ ደመወዝ ነው የሚከፈለው ! "

➡️ " መቆጥብ ለማይችሉት የኪራይ ቤት ገንብቶ ለመስጠት እየተሰራ ነው " - ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ


ከሰሞኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንግድ ባንክ ጋር መምህራንን ጨምሮ በከተማዋ የሚገኙ የመንግሥት ሠራተኞችን የቤት ተጠቃሚ ያደርጋል የተባለ ስምምነት ተፈራርመው ነበር።

ስምምነቱ በአነስተኛ የወለድ መጠን በ25/75 የብድር መርሐ ግብር የሚከናወን ሲሆን 25 በመቶውን መንግሥት ሰራተኛ ይቆጥባል 75 በመቶ የባንክ ብድር ይቀርባል። ብድሩ በ20 ዓመታት የሚከፈል ነው።

ንግድ ባንክ 120 ቢሊዮን ብድር እንደሚያቀርብም ተገልጾ ነበር። ፕሮጀክቱ 3  ዓመት የግንባታ ጊዜ አንድ አመት የብድር መክፈያ እፎይታ አለው ነው የተባለው።

ነገር ግን መምህራን ይህ የተባለውን 25 በመቶ ቁጠባ የመቆጠብ አቅም እንደሌላቸው ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ የመምህራን ስብሰባ ላይ የተገኙ መምህራን " የተፈራረመው የመምህራን የቤት ቁጠባና ብድር አገልግሎት ጥሩ ቢሆንም በስምምነቱ መሰረት 25 በመቶ ቁጠባ የመቆጠብ አቅም የለንም " ብለዋል።

መምህራኑ " በኑሮ ጫና ምክንያት 25 በመቶ መቆጠብ አንችልም " ሲሉ ተናግረዋል።

" ዘጠኝ እና አስር ዓመት የስራ ልምድ ያለው መምህር 10 ሺህ ብር ገደማ ደመወዝ ነው የሚከፈለው ፤ ከዚህ ደመወዝ ላይ ለቤት መሥሪያ የሚሆን 25 በመቶ ሊቆጥብ አይችልም ፤ ሌላ አማራጭ ሊዘረጋ ይገባል " ሲሉ ጠይቀዋል።

መምህራኑ ከቤት ኪራይና ከዕለት ፍጆታ ተርፎ  ቤት ለማግኘት 25 በመቶ የመቆጠብ አቅም እንደሌላቸው ገልጸው " ሌላ መፍትሄ ይፈለግልን " ብለዋ።

ለመምህራኑ ጥያቄ ምላሽ የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፥ " መምህራን ያነሷቸ የቤት ጥያቄዎች ትክክልና ተገቢ ናቸው " ብለዋል። 

" መምህራን ከዚህ በፊት በነበረ ስብሰባ ያነሱት ጥያቄ ' ለቤት ግንባታ የሚውል በነፃ መሬት ስጡን ' የሚል ነበር ፤ በተጨማሪም ' የብድር አገልግሎት አመቻቹልን ' የሚል ጥያቄ ነበር በዚህም ብድሩ ተመቻችቷል " ሲሉ አብራርተዋል።

" 25 በመቶ መቆጠብ የሚችሉ እንዲቆጥቡ እና 75 በመቶ የብድር አገልግሎት እንዲያገኙ የማድረግ ዕድል ተመቻችቷል " ያሉት ከንቲባዋ " መቆጥብ ለማይችሉት የኪራይ ቤት ገንብቶ ለመስጠት እየተሰራ ነው " ሲሉ ተናግረዋል። #ኢፕድ

#መምህራን

@tikvahethiopia
😭524168👏122😡61💔29🤔14🙏11😱10😢10🕊6🥰5