TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
የኤርትራው ፕሬዝዳንት ምን አሉ ? 🔵 " ሕገ-መንግሥቱ ለውጥረት መንስዔ ከመሆኑም ባሻገር ሀገር ግንባታን የሚያስፋፋ አይደለም " - የኤርትራው ፕሬዝዳንት የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ትላንት ምሽት በመንግሥታቸው የቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርበው ስለወቅታዊ ጉዳዮች ቃለ-ምልልስ ሰጥተዋል። ፕሬዝደንቱ ሶማሊያ፣ ግብፅ እና ሀገራቸው ኤርትራ ስለገቡት ስምምነት፣ በኢትዮጵያ በተለይ በትግራይ ክልል ስላለው…
#ኤርትራ

🚨 " አምባገነኑ ኢሳያስ በህግ ለመተዳደር፣ ለህጋዊ ጉዳዮች፣ ለህገመንግስት ባዕድ ናቸው ! " - የፋና ቴሌቪዥን ዘገባ

🔴 " አምባገነንነትን አጥብቀው የሚወዱት ኢሳያስ ምርጫንም ሆነ የህግ የበላይነትን እምቢኝ እንዳሉ ወንበራቸው ላይ አርጅተዋል ! "


ፋና ቴሌቪዥን በኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ላይ " የአስመራው መንግሥት ነገር - የራሷ አሮባት " በሚል የሰራው ጠንከር ያለ ዘገባ መነጋገሪያ ሆኗል።

" የገዢውን ፓርቲ አቋም ያንጸባርቃል እንዲሁም የመንግሥት ልሳን ነው " እየተባለ የሚነገርለት ፋና ቴሌቪዥን ከዓመታት በፊት በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል የሰላም ስምምነት ከተፈረመ ወዲህ በዚህ ልክ ኢሳያስን እና አስተዳደራቸውን አምርሮ የሚተች ዘገባ አውጥቶ አያውቅም።

በትግራይ ጦርነት ወቅት እንኳን ስለ ኤርትራው ገዢ ኢሳያስ ብዙ ሲባል የነበረ ቢሆንም የሻዕቢያ ሰራዊት የሰራቸውን የግፍ ተግባራት በይፋ ተናግሮ አያውቅም ነበር።

በተለይ ከፕሪቶሪያው ስምምነት መፈረም እና ኢትዮጵያ የባህር በር ሊኖራት የግድ እንደሚገባ በግልጽ አቋሟን ይፋ ካደረገች በኃላ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል የነበረው ግንኙነት ሻክሯል በሚባልበት በዚህ ወቅት ጠንካራ እና ድፍረት የተሞላበት ዘገባ ሰርቶ ወጥቷል።

የዘገባው መነሻ ሰሞነኛው የኢሳያስ ቃለ ምልልስ ነው።

የፋና ዘገባ " በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ያለውን እጅግ የሻከረ ወቅታዊ ሁኔታ ያሳያል " ተብሏል።

ፋና በሰራው ዘገባ ስለ ፕሬዜዳንት ኢሳያስ ምን አለ ?

በቡዙ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ችግር ውስጥ የተዘፈቀችውን የራሳቸውን ሀገር ረስተው ስለ ሌሎች ሀገራት እና ስለ ኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ሲፈተፍቱ ነበር።

ኤርትራ በህገመንግስት መስተዳደር ብርቅ የሆናባት ሀገር ናት። ይህ ሆኖ እያለ ህገመንግስት ያላትን ኢትዮጵያን መተቸታቸው አስገራሚ ነው።

ላለፉት 30 ዓመታት በላይ ያለ ምንም ተቀናቃኝ ኤርትራን የገዙት ኢሳያስ መንግሥታቸው ህገመንግስት ፣ ምርጫ ፣ ነጻና ገለልተኛ የዴሞክራሲ ተቋማት የሚባል ነገር አያውቅም ፤ ፍላጎትም የላቸውም። ደግሞ አፋቸውን ሞልተው ይህንኑ ይናገራሉ።

ምርጫም ሆነ ተቀናቃኝ እንዳይኖር ለሶስት አስርት ዓመታት አፍነው እያስተዳደሩ ፣ በኢኮኖሚም ሆነ ፖለቲካም ከዓለም ስለራቀች ሀገራቸ
ኤርትራ ለመናገር ነውር አስመስለውታል።

ለቀጠናዊ ሰላም እና ትብብር ጆሮ የማይሰጡት ኢሳያስ በቀጠናው ሰላም መደፍረስ ጣታቸውን ኢትዮጵያ ላይ ቀስረዋል።

የህገመንግስት አስተዳደር የሌላቸው ኢሳያስ የኢትዮጵያን ህገመንግስት ለመተቸት ደፍረዋል።

ኤርትራ ህገመንግስት ካፀደቀች ሩብ ክፍለዘመን ቢሆናትም አምባገነንነትን አጥብቀው የሚወዱት ኢሳያስ ከመሳቢያቸው ስር ሽጉጠው ምርጫንም የህግ የበላይነትንም እምቢኝ እንዳሉ ወንበራቸው ላይ አርጅተዋል።

ህገመንግስት የሌላቸው ሰው የኢትዮጵያ ህገመንግስት ላይ አስተያየት መስጠታቸው ስላቅ ይሆናል።

አምባገነኑ ኢሳያስ በህግ ለመተዳደር፣ ለህጋዊ ጉዳዮች፣ ለህገመንግስት ባዕድ ናቸው።

አምባገነኑ ኢሳያስ  የጎረቤቶቻቸው በህግ መመራት የራሳቸውን ድካም የሚያጋልጥባቸው ይመስላቸዋል።

ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ የሚያደረጉ የጎረቤት ሀገራትን አይወዱም።

ኢሳያስ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠን መንግስት ለማወክ ከጀርባ ታጣቂ አሰልጥነው የሚልኩ መሆናቸውን ቴሌቪዥን ላይ ሲቀርቡ ይረሱታል።

እራሳቸውን የቀጠናው ጠበቃ የሀገራቱ ሰላም ወዳድ አድርገው የብልጣ ብልጥ ጨዋታ ይጫወታሉ።

ኤርትራን እንደ ሲንጋፖር አደርጋለሁ የሚለው ቅዠት ወደ ተግባር መለወጥ ሲያቅታቸው የናቋት ጎረቤታቸው ኢትዮጵያ በየአመቱ 8% በላይ እድገት እያስመዘገበች በኢኮኖሚ የቀጠናው ቁንጮ መሆኗ ቅናት ውስጥ ከቷቸዋል።

ኢትዮጵያ ዜጎቿን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ከማድረግ አልፋ ምስራቅ አፍሪካን በኃይል እያስተሳሰረች ከሰሃራ በታች ካሉ ሀገራት የአፍሪካን ሁለተኛ ኢኮኖሚ ገንብታለች።

ኢሳያስ ድፍን 30 ዓመታት የመሯት ሀገር ከ30 ዓመታት በፊት በተገነባ መሰረተ ልማት እየኖሩ ነው።

በኤርትራ ኢንተርኔት እና ስልክ በቤተሰብ ኮታ ነው የሚሰጠው። ገንዘብ በATM ማውጣት ብርቅ የሆነባት ሀገር ናት። ዜጎች ሰርግ እንኳን ለመከወን የሚያወጡት ወጪ ኦዲት የሚደረግባት ሀገር ናት።

ኤርትራውያን ነገን ያለ ተስፋ ኑሮን በጨለማ ለመግፋት ተገደዋል።

ጉባ ላይ በተለኮሰው የብርሃን ችቦ (GERD) ዜጎቿን ከጨለማ ወደ ብርሃን ለማሻገር እየተጣደፈችን ያለችውን ጎረቤታቸውን (ኢትዮጵያን) ለመተቸት አንደበታቸውን ሲያላቅቁ ምንም የመሸማቀቅ ስሜት አይታይባቸውም።

ኢሳያስ የሚመሩት መንግሥት የጀርባ እቅዱ ኢትዮጵያን አፈራርሶ ለመግዛት እንደነበር በተደጋጋሚ ከሚያሰሙት ንግግራቸው ተስተውሏል።

ከግብፅ እና ሶማሊያ መሪዎች ጋር ' ቀጠናዊ ሰላም ለማምጣት ' በሚል የዳቦ ስም በሰጡት መርዛማ ቀጠናውን የማተራመስ ሃሳብ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም ላይ ስጋት የደቀነ ስምምነት አስመራ ላይ ሲፈራረሙ ታይተዋል። ' ነገሩ ሆድ ሲያቅ .. ' መሆኑን ከ30 ዓመቷ ወጣት ሀገር መረዳት ይቻላል።

አንድ አምስተኛውን ህዝባቸውን ስደተኛ ያደረጉ ኢሳያስ በሰው ሀገር ጉዳይ በመፈትፈት የሚስተካከላቸው አይገኝም።

ኢሳያስ አምርረው የሚጠሉት ለኢትዮጵያውያን የሰንደቅ አላማ ፕሮጀክት የሆነው የህዳሴ ግድብ ሪቫን ሊቆረጥ መቅረቡ እረፍት ነስቷቸዋል።

ይህንን ዘገባ የተመለከቱ በርካቶች ዘገባው " ወቅታዊውን በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ያለውን ቁርሾ / ጤናማ ያልሆነ ግንኙነት ያሳያል " የሚል ሃሳባቸውን ሰጥተውበታል።

https://youtu.be/UdzP3vtR4DI?feature=shared

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
1🤔1.26K371😡215👏193🕊55😱53😭46🙏43😢22🥰13
አሜሪካ በኤርትራ ጨምሮ በሌሎችም ሀገራት ያሉ ኤምባሲዎቿን ልትዘጋ ነው።

አሜሪካ ወደ 30 የሚጠጉ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ዲፕሎማቲክ ጽሕፈት ቤቶቿን ልትዘጋ መሆኑን ሮይተርስ የአገሪቱን የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ሰነድን ጠቅሶ ዘገበ።

የፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳደር አብዛኞቹ በአፍሪካ እና በአውሮፓ የሚገኙ ቢያንስ 27 የአሜሪካ ኤምባሲዎች እና ቆንስላዎችን የሚዘጋ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ ጎረቤት ሀገር
#ኤርትራ አንዷ ናት።

በውሳኔው መሠረት ይዘጋሉ የተባሉት አስሩ የአሜሪካ ኤምባሲዎች ፦
- በኤርትራ፣
- በግሪናዳ፣
- በሌሶቶ፣
- በማዕካላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ፣
- በሉክዘንበርግ፣
- በሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ፣
- በጋምቢያ፣
- በደቡብ ሱዳን፣
- በማልታ እና በማልዲቭስ የሚገኙ መሆናቸውን ሮይተርስ የተመለከተው ሰነድ ያመለክታል።


ከሚዘጉት ኤምባሲዎች እና ቆንስላዎች ባሻገር ኤምባሲ እና በርካታ ቆንስላዎችን በመያዝ ግዙፍ የዲፕሎማቲክ ሥራ በሚከናወንባቸው እንዳ ጃፓን እና ካናዳ ያሉትን ተልዕኮዎች በማዋሃድ መጠናቸውን የመቀነስም ሐሳብ አለ።

ሰነዱ ከፍተኛ ወጪ በማስወጣት ውድ የዲፕሎማሲ ተልዕኮ የተመደበባቸው ናቸው ያላቸውን በሞቃዲሾ ሶማሊያ እና በኢራቅ ያሉ የዲፕሎማቲክ አባላትን መጠን የመቀነስ ሐሳብም መቅረቡን አመልክቷል።

ዶናልድ ትራምፕ ወደ ፕሬዝዳንትነት ከተመለሱ በኋላ የአሜሪካ መንግሥት በተለያዩ መስኮች ከአገሪቱ ፍላጎት ጋር አይጣጣሙም ያላቸውን ተቋማት በመዝጋት እና እርዳታዎችን በማቋረጥ ላይ ይገኛል።

የትራምፕ የቅርብ ሰው በመሆኑት ማርኮ ሩቢዮ የሚመራው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በጀት እስከ ግማሽ የሚደርሰውን እንደሚቀነስ ሮይተርስ የተመለከተውን የመሥሪያ ቤቱን ሰነድ ጠቅሶ አመልክቷል።

በዚህም ሳቢያ በበርካታ አገራት የሚገኙ የአሜሪካ ኤምባሲዎች እና ቆንስላዎችን የመዝጋት ሐሳብ ሀሳብ ነው ያለው።

የአሜሪካ መንግሥት ለውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ከሚያወጣው ገንዘብ ወደ 30 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ለመቀነስ አቅዶ የበጀት ጥያቄውን ለአገሪቱ ምክር ቤት ለማቅረብ እየተዘጋጀ ነው።

መረጃው የሮይተርስ እና ቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia
👏340128🤔57😢32😱23🕊21🙏16😭8😡8🥰7
" ስምምነቱን ተከትሎ ተሽከርካሪዎቹ ተለቀዋል " - የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ፅ/ቤት

ወደ ትግራይ ክልል ሲጓዙ አፋር ላይ ለቀናት ክልከላ የተደረገባቸው ተሽከርካሪዎች እንዲለቀቁ ተወሰነ።

ውሳኔውን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል ጋር መወያየታቸውን ተከትሎ ነው ተግባራዊ የሆነው።

ፕሬዚዳንት ሌ/ጄነራል ታደሰ ግንቦት 23/ 2017 ዓ/ም ከኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ጋር ውይይት አድርገዋል።

በዚህም ከግንቦት 18 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ በአፋር በኩል ወደ ትግራይ ሲጓዙ ክልከላ የተደረገባቸው የጭነት ተሽከርካሪዎች የተከለከሉበት ምክንያት የጫኑት የንግድ እቃ ከትግራይ አልፎ በኮንትሮባንድ መልክ ወደ #ኤርትራ ሊሻገር ይችላል ከሚል ጥርጣሬ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ተገልጿል።

ሁለቱም ኃላፊዎች በውይይታቸው የመረጃው እውነትነቱ ምን ድረስ እንደሆነ የሚያጣራ ከፌደራል ፖሊስ እና ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የተውጣጣ ኮሚቴ ጉዳዩን እንዲመረምረው ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

የኮሚቴው የምርመራ ውጤት መሰረት በማድረግ የቁጥጥር ስርአት እንዲዘረጋ እና ተጠያቂነት እንዲሰፍን ይህን የማከናወን ተግባርና ኃላፊነት ደግሞ በዋናነት የጋራ ኮሚቴው እንዲሆን ተወስኗል።

ስምምነቱን ተከትሎ ተሽከርካሪዎቹ ተለቀዋል።

በቀጣይም ተመሳሳይ ችግር እንዳያጋጥም ኃላፊዎቹ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤታ ያሰራጨው መረጃ አመልክቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
1.18K🕊90😡77🙏50😢31🤔23🥰13💔8👏6