" ... የት እንኳን እንዳለ አላውቅም። #መገደሉን በተመለከተም ገድዬዋለሁ ያለውን መጠየቅ ነው የሚሻለው " - አባ ገዳ ጎበና ሆላ
የቱልማ አባ ገዳ ጎበና ሆላ ኢሬሶ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (OLA) አባል የሆነ ልጃቸው መገደሉን ከማኅበራዊ ሚዲያ መስማታቸውን ተናገሩ።
ከ1 ሳምንት በፊት በኦሮሚያ ክልል ፣ የምዕራብ አርሲ ዞን ኮሚዩኒኬሽን የ ‘ ሸኔ ’ ቡድን አባል ነው የተባለውን የአባ ገዳ ጎበና ልጅ " ሰላማዊ ሰዎችን ለመግደል ሲንቀሳቀስ እርምጃ ተወስዶበታል " ብሎ ነበር።
ኮሚኒኬሽኑ " የኦሮሞ ልጆችን ሕይወት ሲቀጥፍ የነበረው የአባ ገዳ ጎበና ሆላ ልጅ (ፎሌ ጎበና) ላይ በምዕራብ አርሲ ዞን ገደብ አሳሳ ወረዳ ውስጥ የሰላማዊ ሰዎችን ሕይወት ለመቅጠፍ ሲንቀሳቀስ እርምጃ ተወስዶበታል " ነው ብሎ የነበረው።
ይህንን ጉዳይ በተመለከተ አባ ገዳ ጎበና ሆላ ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ቃላቸውን ሰጥተው ነበር።
አባ ገዳ ጎበና ሆላ ምን አሉ ?
- የልጃቸውን የመገደል ዜና የሰሙት በማህበራዊ ሚዲያ እንደሆነ እና እስካሁን ምንም ማረጋገጫ እንዳላገኙ ገልጸዋል።
- የልጃቸውን ሞት ባያረጋግጡም በእርግጥ ልጃቸው መንግሥት ኦነግ-ሸኔ ብሎ የሚጠራው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂ ቡድን አባል መሆኑን #አረጋግጠዋል።
- ልጃቸው ፎሌ ጎበና ዕድሜው ወደ 33 ዓመት እየተጠጋ መሆኑን እና ከልጃቸው ጋር ከተያዩ 6 ዓመታት ማለፉን ገልጸዋል።
- " ከ6 ዓመታት በኋላ ነው ለመጀመሪያ ጊዜ ከቀናት በፊት ፎቶ ግራፉን ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ሲዘዋወር የተመለከትኩት " ብለዋል።
- " የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (OLA) ውስጥ እንዳለ አውቃለሁ ፤ ነገር ግን ምንም ግንኙነት የለንም። የት እንዳለም አላውቅም። መገደሉን በተመለከተም ገድዬዋለሁ ያለውን መጠየቅ ነው የሚሻለው " ብለዋል።
- ልጃቸው ሰላማዊ ሰዎች እየዞረ እንደሚገድል በመንግሥት የቀረበበትን ክስ በተመለከተ ፥ ምንም የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ገልጸዋል።
- " እኔ አባ ገዳ ነኝ አልዋሽም ፤ ከልጄ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የለኝም። ስልክ አንደዋወልም። ከ6 ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ፎቶግራፉን እንኳ የተመለከትኩት " ብለዋል።
የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባል የሆነው እና የአባ ገዳው 7ኛ ልጃቸው የሆነው ፎሌ ጎበና ከቤት የወጣው የ26 ዓመት ወጣት ሳለ እንደነበረ አባቱ ገልጸዋል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ አባ ገዳ ጎበና ልጃቸው ወደ ትጥቅ እንቅስቃሴ መግባቱን ተከትሎ ከዚህ ቀደም የመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች በተደጋጋሚ መኖሪያ ቤታቸው ላይ ብርበራ ማድረጋቸውን ሲናገሩ ነበር።
ከጥቂት ወራት በፊት አባ ገዳ ጎበና ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ቤታቸው ላይ ብርበራ በተደረገበት ወቅት ከወላጅ አባታቸው የወረሱት የጦር መሳሪያ መወሰዱን እና ክስተቱን ተከትሎ በቤተሰብ አባላት ላይ ከፍተኛ መደናገጥ መፈጠሩን ተናግረው ነበር።
መረጃው የቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ነው።
@tikvahethiopia

❤526😭166👏111🕊67🤔36😢24😡23😱21🥰14🙏9