TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ95 ሺህ እስከ 80 ሺህ ያለአግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ያልመለሱ ግለሰቦችን ፎቶግራፍ አሰራጨ። ባንኩ አለግባብ የወሰዱትን ገንዘብ የማይመልሱ ግለሰቦችን ምስል ከተጨማሪ መረጃዎች ጋር ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ በተደጋጋሚ ማስጠንቀቁን አስታውሷል። በዚህም ለ2 ዙር የወሰዱትን ገንዘብ ያልመለሱ ገለሰቦችን ፎቶ ማሰራጨቱን አመልክቶ አሁን ደግሞ በ3ኛ ዙር ያልመለሱት የገንዘብ…
#ፎቶ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መጋቢት 6 ከባንኩ ገንዘብ " ያለአግባብ ወስደው አልመለሱልኝም " ያላቸውን ግለሰቦች ፎቶ ማሰራጨት ቀጥሏል።
ዛሬ ከ80 ሺ እስከ 70 ሺ ብር ወስደው ያልመለሱ ግለሰቦችን ፎቶግራፍ አሰራጭቷል።
ባንኩ ባለፉት ቀናት ለ3 ዙር ያህል ፎቶግራፍ ማሰራጨቱ ይታወሳል።
@tikvahethiopia

😱157😡129❤71👏54🤔45😭25🕊18😢12🙏12🥰6
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ፎቶ ⬆️ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዲስ አበባ ደረጃ እያካሄደው የሚገኘውን የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት 3ኛ ቀን መርሀ ግብር ዛሬ አከናውኗል።
ዛሬ በከተማ ደረጃ " #ታዋቂ ፣ #ተጽዕኖ_ፈጣሪ " ናቸው የተባሉ ግለሰቦች ተገኝተው በኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች ስለ ሂደቱ ገለጻ ተደርጎላቸዋል ተብሏል።
በተመሳሳይ በተለየ ቦታ ላይ ከ112 ወረዳዎች ከ11 የህብረተሰብ የተወጣጡ ተሳታፊዎች በየማኅበረሰብ ክፍላቸውን አጀንዳዎችን የለዩ ሲሆን የሚወክሏቸውን 121 ተሳታፊዎች መርጠዋል።
ነገ ጠቅላይ የሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አሕመድ ጨምሮ የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ተጋባዥ እንግዶችና ዛሬ የተመረጡ 121 ተሳታፊዎች ፤ መግለጫ የተሰጣቸው ተባባሪ አካላት በድምሩ ከ3 ሺ በላይ ተሳታፊዎች በተገኙበት ሀገራዊ የመክፈቻ መርሐ ግብር እንደሚካሄድ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰምቷል።

😡726❤208🕊46😭38🙏30🤔25👏14🥰9😱9😢8
#ፎቶ
አንጋፋው የአዲስ አበባ ስታዲዮም ከኮቪድ -19 ወረርሽኝ በኋላ እጅግ ከፍተኛ የተመልካች ቁጥር ተገኝቶበታል የተባለለትን የእግር ኳስ ፍልሚያ ዛሬ አስተናገደ።
ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ " #የኢትዮጵያ_ዋንጫ " የፍጻሜ ፍልሚያ ተደርጓል።
በዚህም ኢትዮጵያ ቡና ፥ ወላይታ ዲቻን በማሸነፍ ዋንጫውን አንስቷል።
የአዲስ አበባ ስታዲዮምም ከጫፍ እስከ ጫፍ በእግር ኳስ ተመልካች ተሞልቶ ነበር።
ስታዲዮሙ ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኋላ በዚህ ልክ እጅግ የበዛ ተመልካች አላስተናገደም ተብሏል።
ላለፉት ዓመታት እድሳት ሲደረግለትም ነበር።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ፤ ከእድሳቱ በኃላ ለህዝብ ክፍት ተደረጎ በተካሄደው በዛሬው የፍጻሜ ጨዋታ በደጋፊዎች የተወሰኑ ወንበሮች የተነቃቀሉ ሲሆን የተጠባባቂ ተጫዋጮች ወንበሮችም ላይም ጉዳት መድረሱ ተነግሯል።
ከቀናት በፊት ጨዋታውን አስመልክቶ በተዘጋጀ የጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ባህሩ ጥላሁን ፥ " ስታዲየም ውስጥ ያሉ ንብረቶች የህዝብ ሀብትና የመንግስት ንብረት ናቸው ፤ ከፍተኛ ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል ስሜታዊነት ባይጎላ " ሲሉ የአደራ መልዕክት አስተላልፈው ነበር።
More : @tikvahethsport

❤374😭186😡98👏42🤔29🙏25🕊24😢19🥰17😱11